- Advertisement -
ቦርከና
ሃምሌ 25, 2010 ዓ. ም
ሰሞኑን በሱማሌ ኢትዮጵያ ክልል እንዳዲስ ያገረሸ ሁከት መነሳቱን ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው እንዲሰማራ እንደተደረገ ታውቋል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዛሬ የመከላከያ ሚኒስቴርን በመጥቀስ ባወጣው ዘገባ በጂጂጋ አካባቢ የተፈጠረው ችግር ወደ ሌሎች አካባቢዎች መዛመቱን ገልጾ እየታየ ያለው ነገር በምንም አይነት ተቀባይነት እንደሌለው እና የመከላከያ ሰራዊቱ በተሰጠው ህገመንግስታዊ ሃላፊነት እና አገባብ ሁኔታውን እንደሚቆጣጠር የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቁርጥ ሃሳብ ማድረጉን ዘግቧል።
በሌሎች የዜና አውታሮች ዘገባ አንተደገለጸው ደሞ በጂጂጋ አስከፊ የሆነ ብሔር ተኮር ጥቃት እንደተነሳ እና መከላከያ ሰራዊት በጂጂጋ ከገባ በኋላ ከጉዳዮ ጋር በተያያዘ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በቁጥጥር ስር እንደዋሉም ተሰምቷል ፤ ሆኖም የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሁኔታውን የሚያረጋግጥ ዘገባ አላወጡም። በጂጂጋ የንግድ ቤቶችን ኢላማ ያደረገ የለየለት ዘረፋ እንደበረም ታውቋል ። ሆኖም እስካሁን በሰው ህይወት ላይ ስለደረሰው ጉዳት የታወቀ ነገር የለም።