spot_img
Monday, May 29, 2023
Homeነፃ አስተያየትመደመር ሲሉ መደመር ስንል (በሃገሬ አዲስ)

መደመር ሲሉ መደመር ስንል (በሃገሬ አዲስ)

- Advertisement -

(በሃገሬ አዲስ)
ለቦርከና
ሐምሌ 26 ቀን 20 10ዓም5

መደመር የሚሉት ቃል በጆሮ ሲሰማ መልካም ነው፤ስሜትን ይስባል።መደመር ከነጠላነት ወደ ብዙነት ፣ብዛት ደግሞ ከደካማነት ወደ ጠንካራነት መሸጋገር ማለት ነው። መደመር በሁሉም አቅጣጫ ለጋራ ውጤት ምክንያትና መሰረት ይሆናል።ለጥፋት የአጥፊዎች መደመር እንዳለ ሁሉ፣ ለልማትም የአልሚዎች መደመር ይኖራል። አንድ ቤት ለመስራት የብዙ የግንባታ መሳሪያዎች መደመርን ወይም ውህደትን ይጠይቃል።መልካምና አስተማማኝ ቤት ለመስራት የመሳሪያዎቹ ወይም የግንባታ ምርቶቹ ጥራትና ጥንካሬ ወሳኝ ነው።በማይረባ መሰረት
ላይ ጥራት የሌላቸውን ቁሳቁስ(material) አሰባስቦ ወይም ደማምሮ ግንባታ መጀመሩ ከድካሙ በላይ አደጋው ክፍተኛ ነው።

በምግብ በኩልም የተለያዩ ማዕድናትንና (ንጥረ ነገሮችን) የያዙ ለጤና የሚጠቅሙ የእህል ዘሮችን አቀላቅሎ በዘመኑ አባባል ደማምሮ ማዘጋጀቱ ትልቅ ጥቅም አለው።አንዱ የእህል ዘር የሌለው ቫይታሚንና ፕሮቲን ሌላው ስለሚኖረው ቢደመሩ ወይም ቢቀላቀሉ ለተመጋቢው የተሟላ ጥቅም ይኖረዋል።

በመደመር ወይም በመቀላቀል ስም መርዛማና ጎጂ ውጤት የሚኖረውን፣ እህልና እንክርዳዱን ወይም የነቀዘውን በአንድ ቅርጫት ውስጥ እናስቀምጥ ቢሉት የምግብነት ጥራቱ ይወርዳል፣ተመጋቢውን ለብዙ በሽታ ይዳርጋል። ከሚሰጠው የምግብነት ጥቅም ይልቅ መርዛማ ጉዳቱ ያመዝናል።ለዚያም ነው እህልን በንጽህና ለማዘጋጀትና የምግብነቱን ጥራት ለመጠበቅ ከመቀላቀሉ በፊት የሚለቀመውና በወንፊት የሚበጠረው። ቀጥሎም የቱ ከየትኛው ጋር ቢቀላቀል የሚኖረውን ጥቅምና ጉዳቱን በቅድሚያ መረዳት ያስፈልጋል።የተበጠረ እህል ከተበጠረ ሌላ የእህል ዘር ጋር ቢቀላቀል ጤናና ጉልበት ይሰጣል።በሽሬታው(በመጠኑም) ከፍ ስለሚልም ለረጅም ጊዜ ለብዙ ቤተሰብ ፍጆታ ብቃት ይኖረዋል,።

መደመርን ከግለሰቦች ወይም ማህበረሰቦች አኳያ ካዬነው በቅድሚያ የተደማሪዎቹን ማንነትና ምንነት ማወቁ ውጤቱን ይወስነዋል። በዚህ የመደመር ሂደት የሚደማመሩት አካሎች በምግባር፣በጸባይ፣በአቋምና በዓላማ የማይመሳሰሉ ከሆነ፣እንደመር ብለው ቢነሱ ውጤቱ መደመር በሚያመጣው መደናበር፣ ጉዳት፣ግጭትና ኪሳራ ውስጥ መነከር ይሆናል።
ሙሉውን በፒዲ ኤፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
____
ማስታወሻ:በዚህ ጽሁፍ ላይ የተንጸባረቁ ሳሃቦች የጸሃፊውን/የጸሃፊዋን እንጂ የድረገጹን አቋም አያንጸባርቁም።
ነጻ አስተያየት ወይንም ሃሳብ በዚህ ድረ ገጽ ለማውጣት ጽሁፍዎትን በeditor@borkena.com ወይንም በ info@borkena.com ይላኩልን።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,864FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here