spot_img
Thursday, May 30, 2024
Homeነፃ አስተያየትከብሄራዊ ምርጫ በፊት ህግመንግስቱን ማሻሻል ወይም መቀየር ይቅደም (ከሀቢቡ ታከለ)

ከብሄራዊ ምርጫ በፊት ህግመንግስቱን ማሻሻል ወይም መቀየር ይቅደም (ከሀቢቡ ታከለ)

ከሀቢቡ ታከለ
ነሃሴ 16 2010 ዓ.ም

ካአሁን በፊት አማራጭችን የወደፊት ተስፋቸን በሚለው ጽሁፌ (borkena.com)እንዳአማራጭ ትልቁ የፌዴረሽን አካል ክልል ከሚሆን በዞን ቢደራጅና ከየዞኑ ደግሞ ለሴነትነት ተወካይ የሚሆን በመምረጥ ሌላ ሁለተኛ የምክር ቤት መፍጠር በብሄር ከመከለል ያድነናል። የብሄር መንግስትም ስለሚቀር ካለነበት የብሄረሰብ መንግስት ጠንቅ ይገላግለናል የሚል ሃሳብ አስተናጀ ነበር። ይህ የዞን አስተዳደር በክልል ፈንታ የፌዳራሉ ዋናው ትንሹም ትልቁም አካል ይሆናል ማለት ነው።

ይህን ስል ግን መጀመሪ ይኖርል ወይም ይሆናል ብየ ካለው ሁኔታ ተንስቼ ያሰብኩዋቸውና ግን ያልጣፍኩዋቸው ሃሳቦች ነበሩ፣ እንዚህም ምርጫ ይኖራል። ምርጫውም ፍቱአዊ ይሆናል የሚሉ ናቸው። ከዚህ ድምዳሜ የደረስኩትም ክዶክተር አብይ አባባል ተነስቼ ነበር። እርግጠኛ ያልሆንኩበት ነገር ግን የህግመንግስት ለውጥ ከምርጫ በፊት እንደሚኖር ወይም እንደማይኖር ነው። ሁኔታዎች በግድ የህገመንግስት መቀየር ወይም መሻሻል እንደሚያስፈልግ ቢጠቁሙም።

ላብራራው፦

1፦ ከዶክትር አብይ አባባል ስነሳ ለትዮጵያዊነትንና ለኢትዮጵያዊን መቆማቸው አንድና ሁለት የማይባል ነገር ነው። አሁን መተንበይ የማይቻለው ግን፣ እንደ ኦህዴድ ባለ ክልላዊ ድርጅት ለሚያነሱት ኢትዮጵያዊነት እንዴት መቆም እንደሚችሉ ግራ ይገባኝና፤ ምን አልባት እኮ በግድ የገዥው ድርጅቶች፣ ኢሃአዴግም “አጋሮችም” ተስባስበው ወይም በክፊል፤ ህወሃትን (ወንጀለኛው ድርጅት)ሳይጨምር፣ አንድ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ፓሪቲ ፈጥረው ለምርጫ ይሄዳሉ የሚል ተስፋ አደርጋለሁ። ይህም ዶክተር አብይ፣ ኢትዮጵያ ከዚያም አልፈው ሰለምስራቅ አፍሪካ ያላቸውን እይታ፣ አሁን ህዝቡ በተቀበላቸው ሁኔታ ለመተርጎም ያስችላቸዋል። ይህንንም ለማድረግ በግድ የህገመንግስት መሻሻል ወይም ለውጥ ከምርጫ በፊት ያስፈልጋል። ይህም ከብሄርተኛንት ወደዜግነት የሚያሸጋግር ይሆናል

2፦ ሌላው ኢህአዴግ እንደ ኢህአዴግ ሊቀጥል የማይችልበት ትልቅ ምክንያት አለ።ኢህኣዴግ/ህወሃት እሳካሁን በሰራው ግፍ ህዝብ ተንገፍግፎ አመጥ አካሂዶ ኢትዮጵያዊነትን አንግቦ ተነስቷዋል፣ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ጠምቶቷል፣ ይህም ለዶክተር አብይ ድጋፍ በሚል ሰልፍ የአንዱ ሰልፍ ባንዴራ ከሌላው ሰልፍ ባንዴራ በመርዘም ውድድር በሚመስል መልክ ሕዝቡ ሆ ብሎ ተስልፏል። ይህ የሚያሳየው ዶክተር አብይ ሙጭጭ ብለው እንደኢሃአዴግ እንዲመሩን፣ ሳይሆን፣ ህዝቡ እንደ ኢትዮጵያአዊ መሪ እንደተቀበላቸው እንዲረዱት ያስፈልጋል። ለዚህም ምላሹ ኢሃአዴጋዊ ስይሆን ኢትዮጵያዊ መሆን ይኖርበታል። ይህም ከብሄራዊ ምርጫ በፊት የህገመንግስት መሻሻል ወይም ሙሉ በሙሉ መቀየር እንደሚያሻ የሚይሳይ ምልክት ነው

3፦ እንደድሮው የአራቱ ድርጅት ግንባር ይቀጥል ቢሉ እንኩዋ፣ “አጋር” ድርጅቶችስ የት ይድረሱ፥፤ በእኩል ድምፅ ይኑራቸው ወይስ ሌላ ድርጅት ይሁኑ፣ ይህን ሁሉ ሲነሳ በግድ የህገ መንግስት ለውጥ ከምርጫ በፊት ቢያንስ ደግሞ መሻሻል እንደሚያስፈልግ ግልጥ ነው።

4፦ ያአራቱ ድርጅቶች ግንባርም፣ ግንባር ሳይሆን፤ በተለይ የህወሃትና የአማራው ድርጅት ብአዴን፣ የገዥና የተገዥ በመሆኑ፣ አብረው በአንድ ግንባር መሰለፍ የለባቸውም። እስካአሁንም የአራቱ ድርጅት ግንባር ሳይሆን የነበረው የህውሃት ገዝነት ነበር። እንደገና ተመልሶ ህወሃት በግንባር ስም አብሮ እንዲገዛ መፈቀድ የለበትም። አሁን ስሞኑን እንኩዋ የህወሃት ወታደር በኮረም ማን አለብኝ ብሎ ህዝብ ይጭፈጭፋል ያስራል። ይህ እየሆነ ብአዴን ዝም ማለት የለበትም። እንኩዋንስ በግንባር አብሮ መግዛት ይቀርና ፣ አጠቃላይ ግንኙነት ማቆም ይኖርብታል፤ ይህም የትራንስፖርትን ግንኙንትን ጨምሮ።

ኦህዴድም ቢሆን ህወሃት፣ በሶማሌ ክልል ላደረገው ወንጀል ሁሉ ተጠያቂ ማደርግ ይኖርበታል። ደቡብ ክልልም ጭምር። ህወሃት እንደታች አምናው እኔ የበላይ ካልሆንኩ ብሎ በየቦታው ብጥብጥ በመፍጠር ሊቀጥል መቻል የለበትም። በመሆኑም የወደፊቱ የድርጅቶች ግንኙነት ሆነ የኢትዮጵያን እጣ ፈንታ በግድ ብህገመንግስት መደንገድ ይኖርበታል። ለዚህም ያለው የብሄር ተኮር ህገመንግስት የኢትዮጵያዊያንን ዜግነት በሚያረጋግጥ መልኩ መሻሻል ወይም መለወጥ ያስፈልገዋል።

5፦ አሁን በተለይ ያለው ሁለት ችግር አንዱ የትግራይ ባአማራ መሬት ላይ ያለው ቅኝ ገዥነት ሲሆን ሁለተኛው የህወሃት እድሜ ለማራዘም ያለምንም ጥናት በየቦታው የተፈጠረው የብሄረሰብ መንግስት ነው። በማያባራ ግብ ግብና መፈናቀል፣ ለስላም ጠንቅ መሆኑ በኦሮሞ፣ ሶማሌና በደቡብ ክልል እየታየ ያለ የማያቇርጥ ችግር ከዚሁ ፓሊሲ የመጣ ነው። ይህንም ችግር ለሁለት አመት በብሄራዊ ምርጫ ይፈታል ብሎ መተው የሚቻልበት ሁኔታ የለም። አሁኑን እስካአሁን በተሾሙት ባለስልጣናት በብሄራዊ ልዩ ፖሊስ ስም በተቁዋቁሙ የህወሃት ተቁዋሞች እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል። በሶማሌ ትናንት የተነሳው ነግ በአፋር፣ ወይም በጋምቤላ አይደገምም ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። በስድስት ወር ውስጥ 3 ሚሊዮን የሚጠጋ ሰው ተፋናቅሏል። ዝም ብሎ ሊታይ የሚገባው አይመስለኝም። ከየቦታው ላለ መፈናቀል መፍትሄው በኢህኣዴግ/ህወሃት የተመለመሉና የተሾሙ ባለስልጣናት ስለሆኑ ከብሄራዊ ምርጫ በፊት እስክዞን ድረስ ህዝቡ በተሳትፎ አሁኑን መምረጥና የራሱን አስተዳደር መመስረት ይኖርበታል። ትናንት በሱማሌ ጉዳይ ያገባናል መፍትሄ ይፈለግለት ብለው ተስብስበው የነበሩ ሰዎች፣ የራሳቸውን እድል በምርጫ ለመምራት የሚችሉ ይመስልኛል። ጌዶዎችም፣ ለሎችም—-እንደዚሁ።

ሁለተኛው የትግራይ ቆዳ ስፋት ችግር፣ ህጋዊ እንዳልሆነ ታወቆ፣ ትግራይ ወደድሮው ግዛት ትመለስ ተብሎ መታወጅ ይኖርበታል። የወልቃይት፣ የጠለምት፣ የራያ ህዝብ ሁለተኛ ዜጋ አይደለም። ይህ በወሮበልነት ከህግ በላይ ክልተገዛችሁ ተብሉ ጭፍጨፋ የሚካሄደው መቆም አለበት። ህግ ለሁሉም ኢጥዮጵያዊ እኩል ከሆነ።

5፦ ከላይ በጠቀስኯቸው በሁሉም ወይም ባአንዱ ወይም በሌላ ምክንያት በግድ ከምርጫ በፊት የህግ መንግስት ለውጥ ወይም መሻሻል ያስፈልገናል። ይህ የሚሆን ከሆነ ደግሞ፤ በነካ እጃችን ህግመንግስቱን ከመቀየር ወይም ከማሻሻል ጋር አብሮ፤ የሁሉም ተሳትፎ ያለበት ኮንፈርንስ እንዲሆን ማድረግ ያሻል።
___
ማስታወሻ:በዚህ ጽሁፍ ላይ የተንጸባረቁ ሳሃቦች የጸሃፊውን/የጸሃፊዋን እንጂ የድረገጹን አቋም አያንጸባርቁም።
ነጻ አስተያየት ወይንም ሃሳብ በዚህ ድረ ገጽ ለማውጣት ጽሁፍዎትን በ info@borkena.com ይላኩልን።

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here