spot_img
Sunday, September 24, 2023
Homeነፃ አስተያየትዋና የሚችል ውሃ የማይፈራ ብቻ ነው፡፡ (ተኮላ መኮንን)

ዋና የሚችል ውሃ የማይፈራ ብቻ ነው፡፡ (ተኮላ መኮንን)

advertisement

ተኮላ መኮንን
ነሃሴ 17 2010 ዓ.ም.

“ዝምታም ድጋፍ ነው” እንዲሉ ዝም በማለታችን የሚወራውን ሁሉ የደገፍን እንዳይመስል ፈራን፡፡ “ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባበትም” ብለን ሰንበተን ቢሆነም ሁኔታው ግን ዝም የሚያሰኝ ሆኖ አልተገኘም፡ ለሰላም እንቁም በሚል መርህ ሰላም ለማደፍረስ የሚፈልጉ አስተያየቶችና ድምዳሜዎች ያዘሉ ጽሑፎች ማንበብ ተደጋገመ፡፡ በተለይም የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትራችን የጀመሩትን “የይቅርታና የፍቅር ጎዳና” ድልድዩን ለመስበር አስፋልቱን ለማበላሸት የሚደረጉ እርብርቦሽ እያሰጉ መጡ፡፡ አገራችን እድል ሆኖ ስንቀራረብ የሚደበት ስንራራቅ የሚደሰት ሞላባት መሰለኝ፡፡ ለነገሩ ከቋሚ ይልቅ የሙትን እሬሳ የምናከብር ከሠርግ ይልቅ ቀብር የማያመልጠን በደህና ቀን ከመተባበር ይልቅ ለቀብር በተቻለን ሁሉ የምንረዳዳ ሕዝቦች ነን፡፡ በዚህ አባባል የማይስማማ ካለ በእይታው ላይ እራሱ እየዋሸ ነው፡፡

ለዛሬ ጽሑፌ መነሻ የሆነኝ በ aigaforum ድሕረ ገጽ ላይ “የት ይደርሳል የተባለ ጥጃ ልኳንዳ ቤት ተገኘ እንደሚባለው የት ይደርሳል የተባለ “መደመር” የህዝብ ድጋፍና አመኔታ አጥቶ በ4-ወራት መሬት ላይ ዘጭ አለ” በሚል እርእስ የተለጠፈውን ጽሑፍ ካነበብኩ በኋላ ነው፡፡ ከአርስቱ ጀምሮ አስደነገጠኝ፡፡ ብዙ ሳላነበው መደምደሚያውን ማየት አስፈራኝ፡፡ ወይ እኔ እቶ በሸቀጥ እንዴት ያለ ሥም አለ ያለውን የቆየ ቀልድ አሰታወሰኝ፡፡ ግለሰቡ ይህንን ያለው ከማዶ ያለ ሰው ኧረ አቶ ግሞ ብሎ ሲጣራ ሰምቶ ነው፡፡ ቀልዱን እንዳለ በማቅረቤ ለቃላቱ ይቅርታ፡፡ ካለበለዚያ መልእክቱን ያጣል ብዬ ነው፡፡ ወንድሞቼ አገራችን ሰላም ይነግሥባት ይሆን? ያ ሊሆን የሚችለው በእኔ እምነት ሁላችንም ሰላምን ከፈለግን ብቻ ነው፡፡ ሁል ጊዜ “ለስርቆት” እንዲያመቸን ግርግር የምንመኝ ከሆነ ግርግሩ እኛንም እንዳያጠፋን ብንጠነቀቅ መልካም ነው፡፡ ጸሐፊው ግለሰብ ናቸው ብዬ ጀምሬ ሳነብ ቆይቼ መጨረሻው ላይ ጽሁፉ የቀረበው ከህዳሴ ኢትዮጵያ ነሓሴ 10፣ 2010 ዓ.ም. መሆኑን ስረዳ የድርጅት ጽሑፍ እንደሆነ ገባኝ፡፡ ያ ታዲያ ምሬቴን ጨመረው፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ይሄን ይጫኑ
_
ማስታወሻ:በዚህ ጽሁፍ ላይ የተንጸባረቁ ሳሃቦች የጸሃፊውን/የጸሃፊዋን እንጂ የድረገጹን አቋም አያንጸባርቁም።
ነጻ አስተያየት ወይንም ሃሳብ በዚህ ድረ ገጽ ለማውጣት ጽሁፍዎትን በ info@borkena.com ይላኩልን።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,682FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here