spot_img
Sunday, September 24, 2023
Homeነፃ አስተያየትህዝባዊ ይሁንታና ባለቤትነት ላለው የትምህርት ፖሊሲ (አየናቸው አሰፋ)

ህዝባዊ ይሁንታና ባለቤትነት ላለው የትምህርት ፖሊሲ (አየናቸው አሰፋ)

advertisement

አየናቸው አሰፋ
ነሃሴ 18 ፤2010 ዓ.ም.

እንደማህበረሰብ እና እንደሃገር የውድቀትና ትንሳኤያችን፣ የክስረትና ክብረታችን አንዱ ምናልባትም ዋናው መነሻ ትምህርት ነው። ስለሆነም ትምህርት የሁላችንም የጋራ ጉዳይ ነው። እያካሄድን ያለው ትምህርትን የማሻሻል ጥረትም በዚሁ መንገድ መታየት ያለበት ነው።

ውይይት እየተካሄደበት ያለው የትምህርት ፍኖተ-ካርታ በዝግጅት ረጅም ጊዜ እና ገንዘብ የወጣበት ብቻ ሳይሆን ባለፉት 50 እና 60 አመታት የሳትናቸውን ለማረም እና የወደፊቱን የተሻለ ለማድረግ በእጃችን ያለ ትልቅ እድል ነው። በመሆኑም በዚህ ጉዳይ ላይ ይመለከተኛል የምሰጠው ሃሳብ አለኝ የሚል ሁሉ እኩል እድሉን የሚያገኝበትን መንገድ መሻት ያስፈልጋል።

አሁን እየተካሄደ ካለው ውይይት በተጨማሪ በቀጣይ በየደረጃው መምህራን ውይይት የሚያደርጉበት መሆኑ በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ተገልጿል። ከትምህርት ባለሙያዎች እና ከመምህራን ጋር የሚካሄዱ ውይይቶች እውነተኛ በሆነ ገንቢ መንፈስ እና አካሄድ ከተከናወኑ እጅግ ጠቃሚ የሆነ ግብአት የሚያስገኙ መሆኑ አያጠራጥርም።

ነገር ግን ከዚህ ባለፈ ማንኛውም ዜጋ በጉዳዩ ላይ ሃሳቡን እንዲሰጥ ለማስቻል የስካሁኖቹ ሃሳቦች ተካተው የተሻሻለው ረቂቅ ሰነድ በትምህርት ሚኒስቴር ድረ-ገፅ እና ሌሎች አማራጮች ተደራሽ ቢደረግ፤ ሃሳብ መስጠት ይሚሻ ሁሉ የሚስተናገድበት መድረክ (platform) ቢሰናዳ ጠቃሚ ነው። ይህ በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ የትምህርት ባለሙያዎች፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ በትምህርት ላይ ጥናት ያደረጉ ተመራማሪዎች፣ በየዘርፉ ያሉ ሙያተኞች፣ ባለፉት ዘመናት በሙያና በሃላፊነት ምድቦች በትምህርት ዙሪያ የሰሩ ግለሰቦች፣ ቀጣሪ ድርጅቶች እንዲሁም ሌሎች ያገባኛል ባዮች ሁሉ ሃሳብ እንዲሰጡ ያስችላል። ይህም ረቂቁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ከመፅደቁ በፊት (አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ወዘተ ዙር ረቂቅ ቅጂ እየተባለ) መሆን ይኖርበታል።

እዚህ ላይ ሁለት ነገሮች ሊነሱ ይገባል። አንደኛ ትምህርት ሚኒቴር ከስከዛሬው አሰራሩ በተሻለ መልኩ በትምህርት ፍኖተ ካርታው ጉዳይ ላይ ግልፅ ለመሆን እየጣረ መሆኑ ይታያል። ይሁን እንጂ አሁንም አብዛኞቻችን የረቂቅ ሰነዱን ይዘት በሰሚ ሰሚ ቅብብሎሽ እንዲህ እና እንዲያ ይላል ክሚል ባለፈ ለማወቅ አልቻልንም። ሚኒስትር መስሪያ ቤቱም በፌስቡክ ገጹ ላይ በየቦታው በምትሰሙት ወሬ አትወናበዱ ገና በውይይት ላይ ያለ ረቂቅ ነው የሚል ጥሪ አቅርቧል። ለዚህ መፍትሄው ረቂቅ ሰነዱን (እንዲሁም በሰነዱ ላይ የሚካሄደውን ውይይት) ተደራሽ ማድረግ ብቻ ነው። (በነገራችን ላይ ጠ/ሚኒስትሩ ስለ ፍኖተ ካርታው ለህዝብ ካስታወቁ በኋላ ርቂቅ ሰነዱ ተደራሽ ቢሆን መልካም ነው የሚለውን ይህን ሃሳብ ለጠ/ሚኒስትር ቢሮም ለት/ት ሚኒስቴርም አቅርቤ ነበር)።

ሁለተኛ በዚህ በተባለው መልክ ሃሳብ መሰብሰብ ሊገኝ ከሚችለው መጠነ ሰፊ መረጃ የተነሳ ለአሰራር አስቸጋሪ ሊሆን መቻሉ እሙን ነው። ሆኖም ተለፍቶበት በህዝብ ይሁንታና ባለቤትነትን ያተረፈ ፖሊሲ ቢኖረንና በኋላ እንዲህ መሆን ነበረበት ወይም አልነበረበትም ይህ ለዚህኛው የማህበረሰብ ክፍል ጎጂ ነው ወይም አድሏዊ ነው የሚሉ ቅሬታዎችንና በአፈፃፀም ሂደት ለማረም የሚደረጉ መደነቃቀፎችን ስለሚያስቀር (ቢያንስ ስለሚቀንስ) ድካሙ የሚያስቆጭ አይሆንም። የሚሰበሰበውን መጠነ ሰፊ መረጃ ለመለየት፣ ለማጥራትና ለመተንተንም በጎፈቃደኛ ባለሙያዎችን መጠቀም ይቻላል (ይህን አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ የሆንን ብዙዎች እንደምንኖር አምናለሁ)።
__
ማስታወሻ:በዚህ ጽሁፍ ላይ የተንጸባረቁ ሳሃቦች የጸሃፊውን/የጸሃፊዋን እንጂ የድረገጹን አቋም አያንጸባርቁም።
ነጻ አስተያየት ወይንም ሃሳብ በዚህ ድረ ገጽ ለማውጣት ጽሁፍዎትን በ info@borkena.com ይላኩልን።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,682FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here