
ፎቶ : ኤ ኤፍ ፒ በዮናስ ታደሰ
AFP
ቦርከና
ጳጉሜ 4 2010 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ መንግስት የትጥቅ ትግል ለሚያደርጉ ተቃዋሚዎች ሃገር ቤት ገብተው በሰላማዊ መንገድ እንዲታገሉ ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ ፤ የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ ለሰላማዊ ትግል እንደሚመች እና እንደማይመች የራሱን ግምገማ በማድረግ ፤ ከመንግስት አካላትም ጋር ድርድር በማድረግ ወደ ሃገር ቤት ለመግባት መወሰኑ የሚታወስ ነው።
በዚሁ መሰረት ዛሬ የድርጂቱ ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ጸሃፊው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አዲስ አበባ ገብተዋል። ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ እንደደረሱም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸውል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የድርጂቱ ደጋፊዎች በተገኙበት ደማቅ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌም በስታዲየሙ ለተሰበሰቡት ደጋፊዎቻቸው ንግግር አድርገዋል፤ የፖለቲካ መሪዎቹን ለመቀበል ከተደረገው ዝግጂት ጋር በተያያዘ አዲስ አበባ ቀደም ሲል መንግስት በአዋጂ የከለከለው ባንዲራ በከፍተኛ ሁኔታ ተውለብልቧል።
የአርበኞች ግንቦት 7 ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ሰላማዊ ትግል ለመታገል መወሰኑ ተዳክሞ የነበረውን የአንድነት ጎራ ያጠናክረዋል ሲሉ አስተያየታቸውን የሚሰጡ ኢትዮጵያውያን በርካታ ናቸው።
በ አዲስ አበባ ስታዲየም የነበረውን አቀባበል ዝግጂት ቪዲዮ ለማየት ይሄንን ይጫኑ
__
ወቅታዊ እና ሚዛናዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።