spot_img
Wednesday, March 29, 2023
Homeአበይት ዜናኦህዴድ 9ኛ ድርጂታዊ ጉባዔውን ትላንት በጂማ ጀመረ

ኦህዴድ 9ኛ ድርጂታዊ ጉባዔውን ትላንት በጂማ ጀመረ

- Advertisement -
ኦህዴድ
አቶ ለማ መግርሳ እና ዶ/ር አብይ አህመድ በጉባዔው ላይ
ፎቶ ፥ ኢ ብ ኮ

ቦርከና
መስከረም 10 2011 ዓ.ም.

የኦሮሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጂት (ኦህዴድ) 9ኛ ድርጂታዊ ጉባዔውን በጂማ ጀምሯል። በጉባዔው አንድ ሺህ ስልሳ ስድስት ድምጽ በመስጠት የሚሳተፉ እና ሁለት መቶ ሃምሳ ተሳታፊዎች ደግሞ በታዛቢነት ታድመውበታል።

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢህአዴግ አባል ድርጂቶች ተወካዮች ተገኘተው ንግ ግር አድርገዋል። ብአዴንን ወክለው የተገኙት አቶ ንጉሱ ጥላሁን የኢትዮጵያን ህዝቦች በተለይም ኦሮሞን እና አማራን ለማጋጨት የሚተጉ ወገኖች አሉ፤ እንዳይሳካላቸው ማርከሻ ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል።

የደህዴን ተወካይ መሰረት መስቀሌም በበኩላቸው ድህዴን ከኦህዴድ ጎን በመቆም ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ህወሓትን ወክለው የተናገሩት ዶ/ር አብርሃም ተከስተ “ህወሃት እና የትግራይ ህዝብ ኦህዴድ ለኦሮሞ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ መብት ለከፈለው መስዋዕትነት አክብሮት አለው” ብለዋል።

የድርጂቱ ሊቀመንበር ዶ/ር አብይ አህመድ እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳም የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል ፤ ሁለቱም በንግ ግራቸው በኦሮሞ ድርጂቶች መካከል መኖር ስላለበት መቀራረብ አንስተዋል።
በተለይም ዶ/ር አብይ አህመድ ኦሮሞ ለኢትዮጵያ አንድነት የደከመ እና የደማ ነው ካሉ በኋላ አሁንም ለኢትዮጵያ አንድነት ኃላፊነት እንዳለበት ተናግረዋል።

ጉባዔው ሲጠናቀቅ የድርጂቱን አወቃቀር እና ስያሜ ጭምር የሚቀይር ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። ዛሬ ከድርጂቱ በወጣ መረጃ መሰረት አባ ዱላ ገመዳን ጨምሮ አስራ አራት ያህል ነባር የድርጂቱን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አሰናብቷል።
ወቅታዊ እና ሚዛናዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,465FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here