spot_img
Tuesday, October 3, 2023
Homeአበይት ዜናየሰኔ 16ቱን የቦምብ ጥቃት በመሩና በገንዘብ የደገፉ ግለሰቦች ላይ ምርመራ ተጠናቀቀ

የሰኔ 16ቱን የቦምብ ጥቃት በመሩና በገንዘብ የደገፉ ግለሰቦች ላይ ምርመራ ተጠናቀቀ

advertisement
Berhanu Tsegaye
Attorney General Berhanu Tsegaye

ቦርከና
መስከረም 22 2011 ዓ.ም.

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ትላንት ባወጣዉ መረጃ መሠረት ሰኔ 16 ቀን ጠ/ሚ አብይ አሕመድ ድጋፍ ለመግለጽ በመስቀል አደባባይ በተጠራ ሰልፍ ላይ የተፈጸመውን የቦምብ ጥቃት በመሩ፣ ባቀነባበሩና የፋይናንስ ድጋፍ ባደረጉ ግለሰቦች ላይ ሲያካሂድ የቆየውን ምርመራ ማጠናቀቁን ገልጿል።

በዚህም መሰረት ጥቃቱን በማቀነባበር፣ በመምራትና በፋይናንስ በመደገፍ የተሳተፉ ግለሰቦች ማንነትና የምርመራ ውጤቱን አስመልክቶ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በሚቀጥለው ሳምንት መግለጫ እንደሚሰጥ መስሪያ ቤቱ በትላንትናዉ ዕለት በፌስ ቡክ ገፁ ላይ ያሰፈረዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ድጋፍ ለመስጠት ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተዘጋጀ ሰልፍ ላይ ቦምብ በማፈንዳት የተጠረጠሩ ግለሰቦች ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ተረኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ክሳቸው ተነቦላቸዋል፡፡

ከቀናት በፊት የፌደራል ዐቃቤ ህግ በድጋፍ ሰልፉ ላይ ቦምብ በማፈንዳት በተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች ላይ በፀረ ሽብር ህሩን በመተላለፍ ወንጀል ክስ መመስረቱ ይታወቃል፡፡

አራቱ ተከሳሾች ማለትም ጌቱ ግርማ ፣ ብርሃኑ ጃፋር፣ ጥላሁን ጌታቸው እና ባህሩ ቶላ ቶሌራ እና የተባሉ ግለሰቦች ጠቅላይ ሚንስትሩ በኦሮሞ ህዝብ ተቀባይነት ስለሌላቸዉ እሳቸዉ ሚመሩት መንግስት መቀጠል የለበትም ይልቁንም ሀገሪቱ መመራት ያለባት በኦነግ ነዉ በሚል ዓላማ ጠቅልይ ሚንስትሩን ለመግደል ጥቃት ፈፅመዋል በሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸዉን ተከትሎ ላከናወኗቸዉ ሥዎች ብሎም በሀገሪቱ የታዩትን የለዉጥ ጅምሮች ለመደገፍ ሰኔ 16 ቀን በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ ላይ በተወረወረ የእጅ ቦንብ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ከ 150 በላይ ደግሞ ቆስለዋል፡፡
በዕለቱም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥቃቱን ተከትሎ በደቂቃወች ዉስጥ በቀጥታ ቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልዕክት ጥቃቱ በሙያ የታገዘና በደንብ የተደራጀና የተቀነባበረ የግድያ ሙከራ መሆኑን ገልፀዉ ነበር፡፡

በሰለሞን ይመር
__
ወቅታዊ እና ሚዛናዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,723FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here