spot_img
Thursday, November 30, 2023
Homeነፃ አስተያየትየፖለቲካ ሸርኮች ሴራ!!! ከህወሓት ወደ ኦነግ የጦር አበጋዞች መንግስት!!! ‹‹ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር››

የፖለቲካ ሸርኮች ሴራ!!! ከህወሓት ወደ ኦነግ የጦር አበጋዞች መንግስት!!! ‹‹ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር››

advertisement

OLF war lords

የሰለጠነ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ሥልጣኔ ለመገንባት ለታገለው፣ ለመላው ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) መሪ ሃይሌ ፊዳ መታሰቢያ ትሁን!
‹‹ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር››
መስከረም 22 2011 ዓ.ም.

ዘመነ ጦር አበጋዝ፣ ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)የጦር አበጋዞች መንግስት ወደ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራያዊ ፓርቲ (ሶህዴፓ) የጦር አበጋዞች መንግስት በትረሥልጣኑን ለማራዘም ያሸጋገረበት የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነበር፡፡ ህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ተስፋ ባለመቁረጥ አሁን ደግሞ ከመቐሌ ምሽጉ ስፖንስር በሚያደርገው ገንዘብና መሣሪያ ለኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) የጦር አበጋዞች መንግስት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በተለይ በወለጋ፣ ጋምቤላና ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ወዘተ ትጥቅና ስንቅ በማቅረብ ሠላም በማደፍረስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ህወሓት የዶክተር አብይ አህመድን አዲሱን ለውጥ ለማደናቀፍና በመላ ሃገሪቱ የሽብር ሴራ በመዘርጋት የዴሞክራሲውን መንገድና ነፃነት በመፈታተን ላይ ይገኛል፡፡ የሰኔ 16 2011 ዓ/ም የቦንብ ፍንዳታ በኦነግና በህወሓት የተፈጸመ የመፈንቅለ መንግሥት ሴራ እንደነበረ ተረጋግጦል በዚህም ወንጀል እጃቸው ያለበት የደህንነቱ ሹም ጌታቸው አሰፋ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ዶክተር ተክለብርሃን ወልደአረጋይና ምክትላቸው ሻለቃ ቢንያም ተወልደ በእስር ላይ የሚገኙት የወንጀሉን በገንዘብና በጦር መሣሪያ አቀናባሪዎች እንደሆኑ ታውቆል፡፡ በ2008 ዓ/ም በእነ ጉርሜሳ አያናና በቀለ ገርባ የክስ ቻርጅ ተከሶ የነበረው ጌቱ ግርማ በድጋፍ ሰልፉ ቦንብ የማፈንዳት ወንጀል በወያኔና ኦነግ ከኬን ገነት ታምሩ ተልኮ ተሰጥቶት መሳተፉ የፖለቲከኛ ሻርኮች ለህዝብና ወገን ደንታ እንደሌላቸው ያሳያል፡፡ በሃገሪቱ የህግ ሉዓላዊነት እስካልተከበረ ድረስ መቐሌ ከመሸገው ወንጀለኛን ክልሉ አሳልፎ ካልሰጠ እርምጃ መወሰድ ግድ ይላል እንላለን፡፡ በክልሉ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የጦር አውሮፕላኖች፣ ታንኮች፣ የጦር ግምጃ ቤት ክምችት ወያኔን ለእብሪት ስራው ዳርጎታል በአፋጣኝ ወደነበረበት ቦታ መመለስ አለበት ፈርቶ ዝም ማለት ውሎ አድሮ ያስከፍላል፡፡ የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር በ1983 ዓ/ም የሽግግር መንግሥት ከወያኔ ጋር በመመሥረት በጊዜው በደኖ፣ አርባጉጉ፣ ወዘተ ህዝብ ላይ ያደረሰው የዘር ፍጅት ተጣርቶ ወንጀለኞቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ አለመደረጉ ዛሬ ኦነግ በሃገሪቱ ውስጥ ወንጀል ለመስራት የተላላኪ ሚናውን በመወጣት ላይ ይገኛል ስለዚህ ከሁሉ በፊት የህግ የበላይነት መከበር ይኖርበታል እንላለን፡፡ የኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ ሃላፊ ጁሃር መሃመድ የ43 ኦሮሞ ሞቶች የስም ሊስት በህግ መረጋገጥ ይኖርበታል፣ ይህ እብሪት በህግ ፊት በቃ ሊባል ይገባል፡፡ ህግ በሌለበት ሃገር የማፍያ ሥርዓት የሚያራምዱ ህገ ወጥ ወንጀለኞች ይፈለፈላሉ፣ የህዝቡን ሠላምና ጸጥታ ማስከበርና ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል መሆኑ ካልተረጋገጠ ሃገሪቱ በዘር የተገነባ የጦር አበጋዞች መንግስት ሥር ዳግም ትወድቃለች እንላለን፡፡ ህወሓት የሶህዴፓ አብዲ ዒሊ የጦር አበጋዝ መንግሥት ሽንፈት በሆላ አዲስ ያገኘው መጋዣ የኦነግ ዳውድ ኢብሳ የሚመራ የፊንፊኔ የጦር አበጋዝ መንግሥት ጋሻ ጃግሬነት የተሰባሰቡት የሥልጣን ሱሰኞች በአሳዛኙ በቀለ ገርባ አንደበት የኦሮሞንና የኢትዮጵያን ደሃ ህዝብ ደም በማፋሰስ ላይ ናቸው፡፡ በሃገሪቱ የህግ የበላይነት ስለሌለ፣ ትላንት የፈፀሙትን ወንጀል ዛሬ ደግመውታል፡፡ የፖለቲካ ድርጅቶች በህግ ተጠያቂ ከሆኑ፣ የህዝብ ግጭቶችን በእንጭጩ መቅጨት ይቻላል እንላለን፡፡ የጦር አበጋዝ ማለት በዘር ግንድ ላይ የተመሠረተ የግል ወታደራዊ ኃይል በማደራጀት፣ ህወሓት በትግራይ ህዝብ ስም፣ ኦነግ በኦሮሞ ህዝብ ስም፣ ኦብነግ በኦጋዴን ህዝብ ስም፣ ሲአን በሲዳማ ህዝብ ስም በዘር የተደራጀ ጦር በመገንባት ሌላውን ዘር በማግለል የራሳቸውን ግዛትና መንግሥት በሌላው ላይ ለመጫን የተደራጀ ኃይል ያቆቁማሉ፡፡ የጦር አበጋዝ ማለት ለግል ጥቅም ስልጣንና ኃብትን የሚያካብት ተዋናይ ሲሆን በአንድ ሃገር፣ ያለው መንግስትና መንግስታዊ መዋቅሮች ጠንካራ ባልሆነበት አካባቢ የሚፈለፈል ነጻ አውጪ፣ ንቅናቄ የጦር አበጋዝ ነው፡፡ (ማኪንሌይ፣2007)‘Warlord’ is a term which used to describe a specific period of China’s history but which has re-emerged as a label during the last three decades (MacKinlay, 2007). The definition of a warlord differ, but most authors agree that a Warlord is an actor who accumulate power and wealth for private means by using military force in an environment where the formal state has little or no control (Reno, 1998, MacKinlay, 2007). ‘’This word (warlord) comes from the German word „Kriegsherr“, that has similar meaning. Even Germans use nowadays the English term instead of their own. [1] ‘’

{1} ‹‹የፖለቲካ የማንነት ጥያቄ›› Identities Politics፣ በአፍሪካ የዘመነ-ጦር አበጋዞች ‹‹የማንነት ጥያቄ›› ዘውጌ ብሄረተኛነት ፅንሰ ሃሳብ ዋነኛና አንገብጋቢ ጥያቄ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ዘውጌ ብሄረተኛነት፣ ‹‹በማህበራዊ ጭብጦች ላይ ሳይሆን፣ በዝርያ፣ በወገን መመሳሰል ላይ የተመሠረተ ብሄርተኛነት››ነው፡፡(አንዳርጋቸው ፅጌ ገፅ 310) በዘመነ-ጦር አበጋዞች በጎሳ፣ በነገድ፣ በዘር፣ በዘውግ፣ በክልል (የደም ግንኙነት፣ የዘር ሃረግ፣ የቌንቌ፣ወዘተ) ላይ የተከለሉና የተመሠረቱ የጦር አበጋዞች አንድ ዘርን በውትድርና በመሠልጠን፣ በማደራጀትና ተዋጊዎች በመመልመልና በሌሎች ዘሮች ላይ በመነሳት፣ የማንነት ጥያቄን ሽሮ መብሊያቸው አደረጉት፡፡ ማርክሲዝም ሌኒኒዝም፣ ማኦይዝም ቀመስ የሆኑ የጦር አበጋዞች በስመ ሶሻሊዝም የብሄር ብሄረሰብን ጥያቄ በማራገብ ደቀ መዝሙር የነበሩ ጀሌውን ህሊና አጠቡት፡፡ የጦር አበጋዞቹ እልፍ አእላፍ ገበሬዎችን በወታደርነት በመመልመልና አንዱን ዘር በሌላው ዘር ላይ ጥላቻ በመቀስቀስ፣ የራሳቸውን ታማኝ ጦር ማደራጀት ቻሉ፡፡ የጦር አበጋዞቹ የማንነት ጥያቄ ኢንተርፕሬነር ፈላስፎች ሆኑ፡፡ በኢትዩጵያ ውስጥ በዘመነ-ጦር አበጋዞች ‹‹የማንነት ጥያቄ›› ዘውጌ ብሄረተኛነት በጉጠኛነት፣ በዘውገኛነትና በዘር ላይ የተመሠረቱ ድርጅቶች መኃል፤ ህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ (ህግሓኤ)፣ ኤርትራ አርነት ግንባር (ኤአግ)፣ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)፣ ግምባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ (ግገሓት)፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦሮሞ እስላማዊ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦእነግ)፣ ምዕራብ ሶማልያ ነፃ አውጭ ግንባር (ምሶነግ)፣ በሱማሌ (ኦኤንሌኤፍ)፣ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ)፣ በጋንቤላ ነፃ አውጪ ግንባር (ጋነግ)፣ የሲዳማ አርነት (ሲአን)፣ ቤኒ-ሻንጉል ነፃአውጪ ግንባር፣ አፋር ነፃ አውጭ ግንባር (አነግ) ወዘተ ማዕከላዊውን መንግስት በማዳከም የፖለቲካ ስልጣን የሚቆጣጠሩበት ስርዓት ሆነ፡፡ በዘመነ-ጦር አበጋዞች በነፃ አውጭ ስም፣ በአንድ ዘር ላይ የተመሠረተ የግላቸው ሎሌ ጦር ሰራዊት ለራሳቸው ጥቅምና ስልጣን በማደራጀትና በመመልመል በብሔራቸው ስም ስልጣን ለመያዥ ይታገላሉ፡፡ የጦር አበጋዞቹ በግለሰቦችና በተለያዩ ቡድኖች ላይ ጥላቻን በመፍጠር የራሳቸውን የጦር ሰራዊት በማቆቆም ጥቅማቸውን ያስጠብቃሉ፡፡ እንደ ቶማስ ገለፃ ከሆነ፣ የጦር አበጋዞቹ ሚና የማንነት መታወቂያ የሚሠጥ የንግድ ድርጅት ጋር ይወዳደራል፣ በዛም የዘርህ ግንድ ተጣርቶ መታወቂያ ይሰጥህና ውትድርና ትመለመላለህ ማለት ነው፡፡

‹‹የማንነት መታወቂያ የሚሠጥ የንግድ ድርጅት አመሰራረቱ፣ በግለሰብና በቡድን የተደራጁ ግለሰቦች የግል ፍልጎታቸውንና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ የቡድን የማንነት ጥያቄን በማራገብ ዘውጌ ብሄርተኛነትን በህዝብ ላይ በኃይል የሚጭኑበት ስርአት ነው፡፡ የጦር አበጋዞቹ በተለይ ተለዋዋጭ ሁኔታዎቹን ሁሉ በመጠቀምና ያለውን ክፍተት፣ ልዩነትና ጥላቻን በማራገብና እንዲሁም አዲስ ልዩነቶችን በመፍጠር በኃይል በመጠቀም ዘውጌ ብሄርተኛነትን ይፈበርካሉ፡፡›› (ቶማስ 2005 ገፅ 79) Constructivism is a social theory that underlines the importance of studying the ideational dimension in international relations, such as norms and knowledge. The main ideas of Social Constructivism is that these collectively held ideas are socially constructed and are therefore able to change in different contexts. Identity is one of those concepts, which has been socially constructed and is therefore malleable in distinct situations. Warlords are often using identity as a means to mobilize and recruit fighters to their private armies, or to create hostility between different groups of individuals in order to advance their own interests. The warlord’s role can be compared to that of the identity entrepreneur’ as defined by Thomas et al.: “An identity entrepreneur is an individual or group of individuals who find it desirable, profitable or otherwise utilitarian to create and reinforce group identities. They will specifically seek to exploit such volatile situations and will do so by reinforcing existing cleavages or create new ones“ (Thomas et al. 2005, p. 79). One of the most efficient ways of creating new and enforcing existing identities is by confronting them to a real or made-up threat against the individuals of a certain group. This was the method used to reinforce the hostility between Hutus and Tutsis in Rwanda, before and after the genocide. By constructing a threat of extermination and nourishing it with speeches and symbols in the same direction, leaders of the Hutu extremists managed to reinforce existing cleavages in such a way that it could mobilize genocide.

{2} የዘር ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ(Divide and Rule of Ethnicities)፣ የጦር አበጋዞቹ የማንነት ጥያቄን በቅኝ ገዥዎች የፖለቲካ ታክቲክና ስትራቴጅ ፖሊሲን በመንደፍ፣ ከፋፍለህ ግዛ (Divide and Rule) ፖሊሲን በዘር ሃረግ ላይ የተመሠረተ የጥላቻ ፖለቲካን በማራገብና በመንዛት (አማራውን ከኦሮሞ፣ ኦሮሞውን ከሱማሌ፣ ትግራዩን ከአፋሩ፣ ሲዳማውን ከወላይታ ወዘተ) ጋር በማጋጨትና ደም በማቃባት የስልጣን ዘመናቸውን አራዝመዋል፡፡ በኢትዮጵያ የሚከፈቱ ዩኒቨርሲቲዎች በዘር ሃረግ ላይ የተመሠረቱ የትምህርት ተቆማት፣ወያኔ የጦር አበጋዞች የማንነት ጥያቄን ከዘር ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ጋር የተያያዘ መሆኑን ያስተውሉ፡፡ በዚህም ምክንያት በሃገሪቱ የትምህርት ጥራት ውድቀት ተከሰተ፡፡ ያንተ ዘር ከእኔ ዘር የበለጠ የተማረ ነው አይደለም፣ በሚል የጅል ውድድር የትምህርት ጥራት፣ የእውቀትና የሥራ ክህሎት አዘቅት ውስጥ ገባ፡፡ Another, even more intractable, aspect of teacher recruitment is associated with the establishment of over 30 universities in Ethiopia at a speed never seen in world history. The universal truth is that universities are not created; they evolve into maturity and climax. Universities are like an ecosystem. A climax is not reached suddenly. It has to go through stages of succession for many years until a complex self-sustaining system evolves into place. The universities so established have become de-jure Federal universities, but de-facto zonal universities.They are the results of the demands by local communities for universities to be established in their zones. The action of giving a “fair share” of universities to different regions and zones in Ethiopia is probably the only one is the world history of education. Unless this criterion for “opening” a university as a “positive” response to public demand is halted and sanity made to prevail it will go on to lower and lower administrative units in the Country. የባንክ ዘርፎች፣በኢትዮጵያ የሚከፈቱ ባንኮችም በዘር ሃረግ ላይ የተመሠረቱ ተቆማት፣ ወያኔ የጦር አበጋዞች የማንነት ጥያቄን ከዘር ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ጋር የተያያዘ መሆኑን ያስተውሉ፡፡ የወያኔ የጦር አበጋዞች ሃገሪቱን ወደ ዘመነ መሳፍንት ሊመልሶት እየተንገራገጩ ይመኛሉ፡፡ ወጋጋን ባንክ እናት ባንክ፣ አንበሣ ባንክ በትግርኛ ተናጋሪዎች የተመሠረተ፣ አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ኮኦፕሬቲቨ ባንክ ኦፍ ኦሮሚያና ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ በኦሮሞኛ ተናጋሪዎች የተመሠረተ፣ ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ደቡብ ግሎባል በደቡብ ህዝቦች ተናጋሪዎች የተመሠረተ፣ ባንክ አቢሲንያ፣ አባይ ባንክ በአማርኛ ተናጋሪዎች የተመሠረቱ ለመሆን ችለዋል፡፡ ከዚህ አደረጃጀት ውጪ ያሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ፣ በወያኔ የጦር አበጋዞች መንግሥት የተዘረፉ የህዝብ ባንኮች ናቸው፡፡ የግል ባንኮች ውስጥ ዳሽን ባንክ፣ ህብረት ባንክ፣ ንብ ኢንተርናሽናል፣ ላየን ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ዘመን ባንክ፣ ብርሃን ኢንተርናሽናል፣ አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ይገኛሉ፡፡

ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲቲውሽን፣በኢትዮጵያ የሚከፈቱ የብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን በዘር ሃረግ ላይ የተመሠረቱ ተቆማት፣ ወያኔ የጦር አበጋዞች የማንነት ጥያቄን ከዘር ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ጋር የተያያዘ መሆኑን ያስተውሉ፡፡ የአነስተኛና ጠቃቅን ማይክሮ ፋይናንስ ተቆማትም በዚሁ መልክ የተደራጁ ናቸው፡፡ በትግራይ ደደቢት ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን፣ በአማራ የአማራ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን፣ በኦሮሚያ ኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን፣ በደቡብ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲቲውሽን፣ አዲስ አበባ ኢዲስ ብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን፣ ድሬዳዋ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲቲውሽን፣ በቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ ቤኒሻንጉል ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲቲውሽን በሃራሪ ሃረር ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲቲውሽን የመሳሰሉት ይገኛሉ፡፡ እንግዲህ ባንኮችና የብድርና ቁጠባ ኢንስቲቲውሽን በዓለም አቀፍ ደረጃ ስራቸው ገንዘብ ለኢንቨስተሮች ማበደር፣ ገንዘብ ማስቀመጥና በማበደር የህዝባችን የኢኮኖሚ እድገት ያለአንዳች አድሎ ማሳደግ ነው፡፡ የፋይናንሻል ተቆማቱ፣ በዚህ ስራቸው ዘር፣ ጎሰኝነት፣ ክልላዊ ዘውጌ ብሄረተኝነት አያግዳቸውም፣ አይወስናቸውም አሊያም ገንዘብ ወሰን ድንበር የለውም፡፡ አዲሱ የዶክተር አብይ አህመድ መንግሥት ይሄን ባንኮች ፋይናንሻል ዘርፍ የዘር አደረጃጀት ማክሰም ይጠበቅበታል እንላለን፡፡ የእግር ኮስ ክለቦች፣በኢትዩጵያ የሚከፈቱ የእግር ካÿስ ቡድኖች በዘር ሃረግ ላይ የተመሠረቱ ተቆማት፣ ወያኔ የጦር አበጋዞች የማንነት ጥያቄን ከዘር ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ጋር የተያያዘ መሆኑን ያስተውሉ፡፡ በትግራይ የደደቢት ቡድን፣ በደቡብ ወላይታ ደቻ፣ ወዘተ የቴሌቨዥንና የሬዲዬ ፕሮግራሞች የአማራ፣የኦሮሚያ፣ የትግራይ፣ የደቡብ፣ የሶማሌ፣ ወዘተ የመኪና መለያ ታርጋዎች የአማራ፣ የኦሮሚያ፣ የትግራይ፣ የደቡብ፣ የሶማሌ፣ ወዘተ የየክልሎች ህገ መንግስት፣ ባንዲራ፣ ክልላዊ መዝሙር ወዴት እየሄድን እንደሆነ ያመላክታል፡፡ በአዲሱ ለውጥ በአፋጣኝ መልስ ሊሰጥባቸው ይገባል እንላለን፡፡

{3} የሥነ-ልቦና መላሸቅ (Identity crisis)፣ የጦር አበጋዞቹ ኢትዮጵያዊ ብሄርተኛነትን በማዋረድ የማንነት ጥያቄ በሥነ-ልቦና በማላሸቅ (Identity crisis) ኢትዮጵያዊ ባህል፣ ኢትዮጵያዊ ታሪክ፣ ብሄራዊ መዝሙር፣ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ፣ ብሄራዊ ቅርስ፣ ብሄራዊ ቌንቌ ወዘተ ጥላሸት በመቀባት የራሳቸውን ዘውግ በትግራይ ህዝብ ስም በመነገድ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር የማጋጨት እኩይ ተግባር ይፈፅማሉ፡፡ ‹‹ምላስ አጥንት የላትም፣ አጥንት ግን ትሰብራለች!!!›› ‹‹ባንዲራ ጨርቅ ነው!!!›› ‹‹የዓይን ቀለማቸው ካላማረን እናባርራቸዋለን!!!›› ‹‹የአክሱም ሃውልት፤ ለወላይታው ምኑ ነው!!!›› ‹‹እንኳን ከእናንተ ተወለድኩ!!!›› ‹‹ጣታችሁ ይቆረጣል!!!›› ‹‹የአስቸኳይ ግዜ ታውጆል፤ የመከላከያ ሠራዊት እርምጃ እንዲወስድ አዝዤለሁ!!!››

{4} የጦር አበጋዞች ክልል የማስፋፋት ፖሊሰ፣ በኢትዮጵያ የክልል መንግሥት ድንበሮች/ ወሰኞች፣ (Regional state borders) የኦሮሚያ ክልል 9 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የአማራ ከልል 5 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የትግራይ ክልል 4 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የአፋር ከልል 6 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የሱማሌ ከልል 5 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የደቡብ ከልል 4 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከልል 3 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የጋምቤላ ከልል 3 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የሃረሪ ከልል 3 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉዋቸው፡፡ የጦር አበጋዞች ክልል የማስፋፋት ፖሊሰ፣ ሃገሪቱን ወደ ማያባራ የድንበርና የወሰን ግጭት እንደሚዳርጋት ነብይ መሆን አይጠይቅም፡፡ የወያነ ጦር አበጋዞች የኢኮኖሚ ዘርፍ ግንባታ በብሄራዊ የኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ያተኮረ ሳይሆን በትግራይ ጠባብ ብሄርተኝነት ላይ ያተኮረ ክልላዊ የጦር አበጋዞች ምጣኔ ኃብት ( The economics of warlordism) የተንሸዋረረ የኢኮኖሚ ግንባታ ነው፡፡ ህወሓት ለዓመታት በትግራይ ህዝብ ላይ በጫነው የአማራ የጥላቻ ፖለቲካ የትግራይን ህዝብን ከአማራ፣ ከአፋር፣ ከኤርትራ፤ ከሱማሌ፣ ከኦሮሞ፣ ከጋምቤላ ወዘተ ህዝብ ጋር ደም አቃብቶታል፡፡ የህወሓት ጦር አበጋዞች ክልል በማስፋፋት ድንበር በመግፋት አንዱ ዘር በአንዱ ዘር ላይ ጦር እንዲሰብቅና የጎሪጥ እንዲተያይ የማድረግ ለሥልጣንህን መንበር ለማስጠበቅ ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ አራምደዋል፡፡ የመለስ ዜናዊ ቅርስና ውርስ (የህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት የኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ጭስኛ በማድረግ የገጠርና የከተማ መሬት ሃብትን በሞኖፖል ይዞል፡፡ ይህውም የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ውርስ የሆነውን ልማታዊ መንግስት በሚል ፈሊጥ በመላ ኢትዬጵያ መሬት የመንግስት ሃብት እንደሆነ መለስ ዜናዊ የኮነሬል መንግስቱ ኃይለማርያም አዋጅን አሳውጆል፡፡ መንግስት የገጠርና የከተማ መሬትን በመሸጥ ሲራራ ነጋዴ መንግስት ሆኖል፡፡ ህገመንግስቱና የኢትዮጵያ ህዝብ ያልመከረበት ይሁንታውን ያልሰጠበት ውክልና በኃይል ተጭኖል፡፡ ይህ የመሬት ጥያቄ ሕዝበ ውሳኔ (referendum) ያልተደረገበት የደርግ አልጋ ወራሾች የጫኑብን አንባገነናዊ የኢኮኖሚ አገዛዝ ስልት ነው፡፡ሌላው የመለስ ዜናዊ ቅርስና ውርስ፣ የትግራይ መሬት 65,900 ኪሎ ሜትር ስኮይር ወደ 85,366.53 ኪ.ሜ ስኮይር ያደረሰው ከአማራ ክልል ከወሎና ከጎንደር እንዲሁም ከአፋር ክልል በአጠቃላይ 19,466.53Km2 ኪሎ ሜትር ስኮይር መሬትና የራስ ዳሽን ተራራንም ወደ ትግራይ ለመከለል እቅድ ሲኖራቸው በአጠቃላይ ወደ ትግራይ ክልል የተከለለው ቦታ የጦር አበጋዞች ክልል የማስፋፋት ፖሊሰ ውጤት ነው፡፡ የጦር አበጋዞች ክልል የማስፋፋት ፖሊሰ በነ ዶክተር ገብረአብ በርናባስ ጠባብ ዘረኝነት ስሜት ከጎንደር፣ ከወሎ፣ ከአፋር ህዝብ ለም መሬት በመንጠቅ ወደ ትግራይ ክልል በማካተት የትግራይን ህዝብ ከሌሎች ደሃ ወንድሞቹና እህቶቹ የማለያየት ፖሊሲ ውጤት ነው፡፡ ከጎንደር መሬት ሁመራ፣ ወልቃይት ወዘተ የሠሊጥ ለም መሬት ላይ የትግራይ የጦር ጉዳተኛችን በማስፈር፣ የአገሬውን መሬት በግፍ በመንጠቅ የተቃወመውን ህዝብ በመግደል፣ በማሰር እንዲሰደድ በማድረግ ኃብቱን ተቆጣጥረዋል፡፡ በ2006 እኤአ 51776 ቶን ሠሊጥ ወደ ውጪ በመላክ 50 ሚሊዩን ዶላር ገቢ ተገኝቶል፡፡በ 2008እኤአ ከተመረተው 1.3 ሚሊዩን ኩንታል ሠሊጥ 900000 ኩንታል ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ በፖርት ሱዳን በኩል በማውጣት 121.5 ሚሊዩን ዶላር የውጪ ምንዛሪ የትግራይ ክልል እንዳገኘ የትግራይ ክልል እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዶክመንት ይገልጸል፡፡ በተመሳሳይ ከአፋር የጨው ማዕድናት ፋብሪካዎች በመትከል አብዛኛዎቹን የሚቆጣጠሩት የትግራይ ጦር አበጋዞች ናቸው፡፡ እንዲሁም በአፋር የተገኘውን የፖታሽ ማዕድን አምርቶ ለመሸጥ በአፋር በኩል በትግራይ አርጎ ጅቡቲ የሚገባ የባቡር መስመር ዝርጋታ የጦር አበጋዞቹ የኃብት ቅርምትና የመስፋፋት ፖሊሲ ስትራቴጂ ውጤት ነው፡፡ ምክንያቱም ኢኮኖሚውን እስከተቆጣጠርን ድረስ፣ የመከላከያና የደህንነት አፋኝ መንግስታዊ መዋቅር በመገንባት የኢትዮጵያን ህዝብ በልማታዊ መንግስት ስም ለዘመናት ለመግዛት እንችላለን የሚል የጦር አበጋዞቹ የአናሳ ዘውጌ የስነልቦና ቀውስ ሰለባዎች ናቸው፡፡ ከሌሎች ክልሎች የተነጠቁ መሬቶች፣ ሳይውል ሳያድር ወደ ተነጠቁት ክልሎች የመሬት ይዞታ እንደሚገባ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ የትግራይ ሕዝብና ምሁርም ይህን ኢፍህታዊ የመሬት ነጠቃ ማውገዝ ይጠበቅበታል፡፡ የዘውጌ ጦር አበጋዞች ለስልጣናቸው፣ ለዝናቸውና ለገንዘብ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሚሊዩን ህዝብ መስዋት ቢሆን፣ ምድር ቢቃጠል፣ ንብረት ቢጠፋ ደንታ የላቸውም፡፡ warlords are “people who are driven overwhelmingly by personal power, glory, and monetary gain and who are ready to sacrifice thousands of lives, land, and property for that power.”12 Lezhnev claims that the central motivation of the warlord, in addition to monetary resources, is the quest for “wealth, power, and fame.”13 This thesis accepts the idea that warlords share two main characteristics: they have military legitimacy, and they are motivated by political power, wealth, and fame.

{5} የጦር አበጋዞች ምጣኔ ኃብት፤(The economics of warlordism)፣ የጦር አበጋዞች ምጣኔ ኃብት በሃገሪቱ የኢኮኖሚ ዘርፎች ውስጥ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት በማድረግ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ በመቆጣጠር ለብዙ አመታት ለመግዛት እሳቤ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ዋነኛ የገንዘብ ምንጫቸው ደግሞ 1ኛ/ የባንክና ኢንሹራንስ ዘረፋ 2ኛ/ ከረድኤት ድርጅቶች በርሃብተኛ ምፅዋት እህል በመሸጥ 3ኛ/ ከህዝብ ላይ ግብር በመሰብሰብ 4ኛ/ በህገወጥ መንገድ በሚካሄድ ንግድ የጦር መሳሪያዎች ሽያጪ፣ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ንግድ 5ኛ/የባህር ማዶ እርዳታ ከዲያስፖራና ከውጭ ሀገር መንግስታት ድጋፍ 6ኛ/ በሙስና መሬት በመሸጥ እንዲሁም የፓርቲ ድርጅቶች የንግድ ድርጅቶች በመፈልፈል የኢኮኖሚ ዘርፍ አውታር መቆጣጠር ዋነኛ ስልታቸው ውስጥ ያገኛል፡፡ ወያኔ በሌሎች ክልሎች ውስጥ የሚገኝ የማዕድን ኃብቶችና ለም መሬቶች ለመቆጣጠር የሚደረግ ስግብግብነት ህዝቡን በጦርነት ውስጥ እንደዘፈቀው መረዳት ያሻል፡፡ Scholars have emphasized the study of economic factors in civil wars and failed states.52 The general proposition is that revenues or sources of wealth are directly related to how conducive an environment is to warlordism. Revenues include anything that a warlord can control with his army and transform into wealth, power or fame. There are four general types of revenues. The first includes natural resources such as oil, natural gas, timber, diamonds and industrial minerals. A second type is revenue generated from taxing the populace and levying customs fees on travel. The third type comes from illegal activities such as weapons sales, drug harvesting and trafficking, or the trafficking of human beings. The fourth source of wealth is assistance from international donors, which includes aid from developmental organizations like the World Bank, reconstruction dollars and training from states like the U.S., and supplies and volunteers from nongovernmental organization (NGOs) such as the Red Cross. A warlord might profit from all these revenue sources, including the last, which is often donated in order to help a state eliminate unruly warlord activities.

{6} የኢንቨስትመንት እድገት (Investment development)፣ በኢትዩጵያ በህወሃት የብሄር ብሄረስብ ያልተስተካከለ የክልሎች የኢካኖሚ እድገት ፖሊሲ የተነሳ፤ ከሌሎች ክልሎች ይልቅ የትግራይ ክልል ባገኘው የኢንቨስትመንት እድገት ተጨባጭ ሁኔታ መሠረት በ2005 እኤአ 815 ፕሮጀክቶች ፍቃድ ተሠጥቶቸዋል፤ በ2009 እኤአ የፕሮጀክቶች ቁጥር በመጨመር 2,215 ደርሶል፡፡ የኢንቨስትመንት ዘርፉ 132% እድገት አሳይቶል፡፡ አዲሶቹ ፕሮጀክቶች ተጨማሪ 12.8 ቢሊዩን ካፒታል የኢንቨስትመንት እና አጠቃላይ 19.4 ቢሊዩን ብር ካፒታል የኢንቨስትመንት እንዳደገ ተገልፆል፡፡ በዚህም መሠረት 53,894 ዜጎች ቆሚ የስራ እድል አግኝተዋል እንዲሁም 154,842 ዜጎች ግዚያዊ የስራ እድል አግኝተዋል፡፡ የሌሎች ክልሎች በዚህ መልክ አላደጉም፡፡ ‹‹ In addition to the 815 projects licensed in 2005, additional 1,400 new projects were licensed in 2009 and the number of projects has grown into 2,215. Thus, the sector has registered an overall growth of 132%. These new projects have added a 12.8 billion capital investment and the sum of capital investment has grown to 19.4 billion birr. As a result, around 53,894 citizens have already been employed permanently and 154,842 citizens are temporarily employed.›› (Page 18)

{7} አብዛኛው ዘውግ የሚያስተዳድርበትና የአናሳ ዘውግ መብቱ የሚጠበቅበት ስርዓት፣(Majority Rule minority Right)፣ የጦር አበጋዞቹ የማንነት ጥያቄና ዘውጌ ብሄርተኛነትን ፋብሪካ መንስኤው የዘውጋቸው በቁጥር አናሳ መሆን ስጋት ያስከተለባቸው፣ የስነልቦና ቀውስ ዋነኛ ምክንያት ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ህዝብ ስድስት በመቶ የሆነው የትግራይ ህዝብን በስሙ በመነገድ ወክሎ የሥልጣን መንበሩን ተቆጣጥሮ ለሃያ ሰባት አመታት በግፍ ገዝቶል፡፡ ቡዙ የህዝብ ቁጥር ያላቸው የኦሮሞና የአማራ ህዝብ በአንባገነን አገዛዝ ስርዓት ቀንበር ስር ወድቀዋል፡፡ የጦር አበጋዞቹ የማንነት ጥያቄ ከዴሞክራሲያዊ ስርዓት ጋር የተፃረረ በመሆኑ የብዙኃኑ ዘውግ አገር የሚያስተዳድርበትና (Majority Rule) የአናሳ ዘውግ መብቱ የሚጠበቅበት (minority Right) ራሳቸውን የማስተዳደር ዴሞክራሲያዊ የአገዛዝ ስርዓት በመንደፍ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ የአሥተዳደር ሥርዓት ከመዘርጋት ሌላ አማራጭ የለም እንላለን፡፡ የወያኔ የጦር አበጋዞች አንባገነናዊ ስርዓት መቐሌ ምሽግ ፀረ-ዴሞክራሲ ኃይል መፍረስ ሌላ አማራጭ የለም፡፡

በኢትዮጵያ እስከ 3 ሚሊዮን ህዝብ ከቀየው ተፈናቅሎ ይገኛል፣ በዘር ላይ የተመሰረተ የጦር አበጋዞች መንግሥታዊ አደረጃጀትና የወሰንና ድንበር አከላለል በህገ መንግሥቱ እስካልተሰረዘ ድረስ ችግሩ ሁሉ ‹ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ›› ይሆናል እንላለን፡፡ በባንዲራ ጥያቄ፣ በአዲስ አበባ ጥያቄና በህገመንግስት ጥያቄ እነዚህ የፖለቲካ ሸርኮች ደም ማፈሰስ ስለሚፈልጉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለህዝቡ ሴራውን ማጋለጥ ይጠበቅባችሆል እንላለን!!! ከህወሓት ወደ ኦነግ የጦር አበጋዞች መንግስት ሴራው ተሸጋግሮል!!!

ምንጭ፣ 1.Journal of Peace Research March 2010 vol. 47 no. 2 217-229 African peacekeeping in Africa: Warlord politics, defense economics, and state legitimacy Jonah Victor United States Department of Defense, jonahv@gmail.com 2.Tigray Regional State: five Years(2010/11- 20/15) Growth & Transformation Plan 3. Source: USAID- COMPARATIVE ASSESSMENT OF DECENTRALIZATION IN AFRICA: ETHIOPIA DESK STUDY, July 2010 4. Source: USA, USAID-Ethiopia

ማስታወሻ:በዚህ ጽሁፍ ላይ የተንጸባረቁ ሳሃቦች የጸሃፊውን/የጸሃፊዋን እንጂ የድረገጹን አቋም አያንጸባርቁም።
ነጻ አስተያየት ወይንም ሃሳብ በዚህ ድረ ገጽ ለማውጣት ጽሁፍዎትን በ info@borkena.com ይላኩልን።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here