ቦርከና
መስከረም 22 2011 ዓ.ም.
በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ወሎ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል በመጠጥ ሀይል ተገፋፍቶ በባልደረቦቹ ላይ ጥቃት መፈፀሙ ተነግሯል።
ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑን ጠቅሶ እንደዘገበዉ የፌደራል ፖሊስ አባሉ በባልደረቦቹ ላይ በፈፀመው ጥቃትም ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት ህይወት አልፏል።
ፖሊስ ጥቃቱን ለማስቆም በወሰደው እርምጃም ጥቃቱን የፈፀመው የፌደራል ፖሊስ አባል ህይወቱ ማለፉን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል አስታውቀዋል።
ቦርከና ያነጋገራቸዉ የአካባቢዉ ነዋሪወች ከሌሊቱ አካባቢ ጀምሮ በሥፍዉ ተኩስ ድማፅ ይሰማ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
ጥቃቱ የተፈፀመዉ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሸዋ ሱፐር ማርኬት እየተባለ በሚጠራዉ ሥፍራ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሚኖሩበት ህንፃ አቅራቢያ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡
ሆኖም በተኩስ ልዉዉጡ ወቅት ከተገደሉት ዉጭ ጉዳት የደረሰበት የፖሊስ አባል ወይም ሌላ ግለሰብ ስለመኖሩ ለማረጋገጥ አልተቻለም፡፡
በአሁኑ ወቅም በስፍራው ተስተጓጉሎ የነበረው የትራፊክ እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ወደ መደበኛ ሁኔታቸው መመለሳቸውን ገልፀዋል።
ግድያዉ በተፈፀመበት አካባቢ እስከ ጠዋቱ 2፡30 መንገድ ዝግ እንደነበርና የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ መስተጓጎል ተፈጥሮ እደነበረ በአካባቢዉ የሚሰራ ግለሰብ ለቦርከና ተናግሯል፡፡
በሰለሞን ይመር
___
ወቅታዊ እና ሚዛናዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።