spot_img
Saturday, September 30, 2023
Homeዜናጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ የአዳማ ኢንዱስትሪል ፓርክን መርቀዉ ከፍተዋል

ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ የአዳማ ኢንዱስትሪል ፓርክን መርቀዉ ከፍተዋል

advertisement

Adama-Industrial-Park-1

ቦርከና
መስከረም 27 ፤ 2011 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በትላንትናዉ ዕለት ከአዲስ አበባ በ100 ኪሎ ሜትር ላይ በኦሮሚያ ክልል የሚገኘዉን የአዳማ ኢንዱስትሪያል ፓርክን መርቀዉ ከፍተዋል፡፡

በቅርቡ በአዲስ መልኩ ስራ ለጀመረዉ የኢትዮ-ጂቡቲ የምድር ባቡር መስመር ቅርበት እንዳለዉ የሚነገርለት የአዳማ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ግንባታዉ ከሁለት ዓመት በፊት የተጀመረ ሲሆን 140 የአሜሪካ ዶላር ወጭ ተደርጎበታል፡፡

በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድን (ዶ/ር) ጨምሮ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ፤ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸዉ፤ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) የወቅቱ ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፤ አቶ አርከበ እቁባይ፤ እንዲሁም ሌሎች በርካታ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡

ከሚፈጠረዉ የሥራ እድል በተጨማሪ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ለቴክኖሎጅ ሽግግር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረዉ ጠቅላይ ሚኒስተሩ በንግግራቸዉ ላይ ጠቁመዋል፡፡

ለፓርኩ ግንባታ መሥሪያ ቦታ የተወሰደባቸዉ ገበሬዎችና የመሬት ባለ ይዞታዎች ከልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚደረግብት መንገድ አንደሚመቻች መግለፃቸዉን ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠቅሶ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል፡፡

እንደዘገባዉ ከሆነ ለፓርኩ ግንባታ የዋለዉ 120 ሄክታር መሬት ቀደም ሲል በአካባቢዉ ይኖሩ በነበሩ አርሶ አደሮች ይዞታ ስር እንደነበረ ተገልጿል፡፡

ቀደም ሲል የኮሚሽኑ ሃላፊ የነበሩትና አሁን የጠቅላይ ሚኒስተር ፅ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸዉ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት መሰረት ይህ ተጨማሪ የኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ በርካታ የዉጭ ባለሃብቶችን ወደ ሀገር ዉስጥ ለመሳብ ከፍተኛ አስተዋኦ እንደሚኖረዉ ገልፀዉ እንዲህ ያለዉ ዉጤታማ ኢንቨስትመንት የሀገሪቱ የኢኮኖሚ መሰረት ከመሆኑም ባለፈ ቀጣይነት ያለዉ የስራ እድል በመፍጠሩ ረገድ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚኖረዉ ገልፀል፡፡

እንደ ኢትዮጲያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን መረጃ ግንባዉ የተጠናቀቀዉ የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በቀዳሚነት የጨርቃ ጨርቅ፤ የቆዳና የቆዳ ዉጦቶች፤ የፋርማሲዉቲካስ እና የግብርና ዉጤቶች የሚመረቱበት እንደሚሆን ታዉቋል፡፡

ይህ ፕሮጀክት ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የአምራች ኢንዱስትሪ መናገሻ ለማድረግ የተያዘዉ እቅድ አንዱ አካል መሆኑም ተዘግቧል፡፡

ባለፉት ዓመታት ኢትዮጲያ የቦሌ ለሚና የሀዋ ፓርኮችን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የኢንዱስትሪያል ፓርኮችን የገነባች ሲሆን የጥሬ ዕቃ አቅርቦት እጥረት፤ የመሰረተ ልማት ችግሮችና የሰለጠነ የሰዉ ሃይል እጥረት በተደጋጋሚ በባለሀብቶች የሚነሱ ችግሮች ናቸዉ፡፡

በሰለሞን ይመር
__
ወቅታዊ እና ሚዛናዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,705FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here