ቦርከና
ጥቅምት 1 ፤ 2011 ዓ.ም
በትላንትናው እለት ቁጥራቸው 240 የሚሆኑ የመንግስት ወታደሮች ከነትጥቃቸው ወደ ቤተ መንግስት መግባታቸው ተሰምቷል። ወታደሮቹ የመከላከያ ልዮ ሰራዊት አባል ሲሆኑ ቀደም ሲል በቡራዩ ተፈጥሮ በነበረው ችግር ምክንያት በዚያው ተሰማርተው ሁኔውን ሲያረጋጉ የቆዮ መሆናቸው ከመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ታውቋል።
ወታደሮቹ ወደ ቤተመንግስት የመጡበት ምክንያት የደሞዝ እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስሩን እናነጋግራለን በሚል እንደሆም ታውቋል ፤ እንደ መንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘገባ።
ምንም እንኳን ያለ ቀጠሮ ዘው ብለው ወደ ቤተመንግስት ቢገቡም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንዳናገሯቸው እና አለን ያሉትን ችግር በመስማት በጥናት ላይ የተመሰረተ ማስተካከያ እንደሚደረግ እንደነገሯቸው ታውቋል።
ውይይታቸውን እንደጨረሱ ከወታደሮቹ ጋር “ፑሽ አፕ” ሰርተው ሁኔታውን የተለሳለሰ እንደነበር ለማሳየት ሞክረዋል – ጠቅላይ ሚኒስትሩ ።
በጉዳዮ ላይ በማህበራዊ ሚዲያ የተለያዮ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው ፤ አብዛኞው ኢትዮጵያዊ ወታደሮቹ የዲሲፕሊን ጥሰት አንደፈጸሙ እና ከበስከጀርባቸው ሌላ ኃይል ሊኖር ይቻላል በሚል ግምት ሁኔታው እንዲጣራ እየጠየቁ ነው ።
__
ወቅታዊ እና ሚዛናዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።