ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)
መስከረም 02 ፣ 2018
Human dignity is offended when persons are denied the opportunity to participate in their own development, when development “takes place over their heads.”( Yuengert M. Andrew, What is “Sustainabel Prosperity for all” in the Catholic Social Tradition ? in: The True Wealth of Nations- Catholic Social Thought and Economic Life.(Oxford, 2010)
መግቢያ
አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች ነፃነትን ከተቀዳጁ ከሃምሳ ዓመት በኋላ በድህነት ዓለምና በጥገኝነት ውስጥ የሚገኙ ናቸው። በአብዛኛዎቹ ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ የተትረፈረፈ የጥሬ ሀብትና እንዲሁም ለነዳጅ የሚሆን ዘይትና ጋዝ ቢኖርም ህዝቦቻቸው በድህነት ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ናቸው። መሬታቸው በጣም ለምለም የሆኑና ብዙ ውሃ ቢኖራቸውም ገበሬዎቹ ከእጅ ወደ አፍ በሚሆን የእርሻ ምርት ላይ የተሰማሩ ናቸው። በዚህም ምክንያት የተነሳ አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች ከውጭ ስንዴና ሌሎች ለምግብ የሚሆኑ የእርሻ ውጤቶችን ያስመጣሉ። ወደ ደቡቡ የአፍሪካ ክፍል ስንሄድ ደግሞ በአብዛኛዎቹ አገሮች ውስጥ፣ ሞዛምቢክ፣ አንጎላ፣ ዚምባብዌና ደቡብ አፍሪካ ዋናው ምግባቸው በቆሎ ነው። መሬታቸው፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ማሽላና ዘንጋዳ፣ እንዲሁም ሌሎች ሰብሎችንና ጥራጥሬዎችን አያበቅሉ ይመስል ህዝቦቹ በቆሎን ብቻ በማምርትና ዋናው ምግባቸው በማድረግ የተመጣጠነ ምግብ(Diet) እንዳያገኙ ሆነዋል። በተለይም የቅኝ ገዢዎች የእነዚህን አገሮች የአስተራረስና የአመጋገብ ዘዴ በማበላሸትና፣ መሬቱ በቆሎና ትምባሆ ብቻ እንዲያመርት በመደረጉ መሰረታዊ የእርሻ ባህል እንዳይስፋፋ ሆኗል። በዚህም ምክንያት የተነሳ አብዛኛው ህዝብ ዕውነተኛ የሆነ የአስተራረስ ባህል እንዳያዳብርና የተመጣጠነ የምግብ ዐይነት እንዳያገኝ ተደርጓል።
ሙሉውን ጽሁፉ በፒዲ ኤፍ ለማንበብ ይሄን ይጫኑ
__
ማስታወሻ:በዚህ ጽሁፍ ላይ የተንጸባረቁ ሳሃቦች የጸሃፊውን/የጸሃፊዋን እንጂ የድረገጹን አቋም አያንጸባርቁም።
ነጻ አስተያየት ወይንም ሃሳብ በዚህ ድረ ገጽ ለማውጣት ጽሁፍዎትን በ info@borkena.com ይላኩልን።