spot_img
Friday, June 21, 2024
Homeነፃ አስተያየትደሃ አዳኝ ሻርክ ባንኮች!!! የዲያስፖራ የሞርጌጅ ብድር አካውንት!!! ክፀ/ት ፂዩን ዘ/ማርያም (ከኢትዮጵያ...

ደሃ አዳኝ ሻርክ ባንኮች!!! የዲያስፖራ የሞርጌጅ ብድር አካውንት!!! ክፀ/ት ፂዩን ዘ/ማርያም (ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር)

ባንኮች
ባንኮች በወንጀል ተፀንሰው በሃጢኣት ይወለዳሉ!

ጥቅምት 7 ፤ 2011

ለአንድ አገር ጠንካራው የመሠረተ (ሃርድ ኢንፍራስትራክቸር ) ልማት እድገት (የመንገድ፣ የኃይል፣ የባቡር፣ የዓየር) ሲሆን ሌላው የማህበራዊ ለስላሳው መሠረተ ልማት (ሶፍት ኢንፍራስትራክቸር) (የጤና፣ የትምህርት፣ ውሃ፣) አገልግሎቶች ማስፋፋት መሆኑ እሙን ነው፣ እነዚህ መሠረተ ልማቶች እንደ ሰው አካላት በአጥንትና ሥጋ ሲመሰሉ የንዋይ መሠረተ ልማት ደግሞ እንደ ደምና የደም ስር በመሆን በመላ አከላት የሚሰራጭ ደም ስርዓተ ሰውነት፣ የአጥንትና ሥጋ መስተጋብርን የአምሮና የአካልን እድገትን ያሳልጣል፡፡ በህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት የ27 አመታት አገዛዝ የግሉ ዘርፍ ሚና በመንግስታዊው ዘርፍ ሚና በመተካቱ የአብዬታዊ ዴሞክራሲ ርእዬት ልማታዊ መንግስት የኢኮኖሚ እድገት አላመጣም፡፡ በሃገሪቱ የንዋይ መሠረተ ልማት የባንክና ኢንሹራንስ፣ የማይክሮ ፋይናንስ ተቆማት እድገት በሃገር በአህጉርና በዓለምአቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ተፎካካሪ ያልሆነ በእውቀት፣ በክህሎት፣ በቴክኖሎጅ ያልዘመነ ለመሆን ችሎል፡፡ የህወሓት/ ኢህአዴግ መንግሥት በቀደደው የፓርቲ የንግድ ኩባንያዎች የኦህዴድ/ ብአዴን ኢህአዴግ ደቀመዝሙሮች ያለአንዳቸ ለውጥ ቀጥለውበታል፡፡ የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች የህወኃት ኢፈርትና ሜቴክ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ አሽመድምደው በሙስናና ሌብነት ተጨማልቀው አዘቅት ውስጥ ከተው በእዳ ተብትበው የሄዱበትን የፖለቲካና ኢኮኖሚ እንዲሁም ማህበራዊ ጉዳይ ተከትሎ መጎዝ ‹‹አልነገርኩሽም ወይ በአጥር ተንጠልጥዬ፣ ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል ብዬ››› ሆኖል፡፡ በመቐሌ የመሽገው ህወሓት ኢኮኖሚውን እየተቆጣጠሩ የልማታዊ መንግሥት ኢኮኖሚና የአብዬታዊ ዴሞክራሲ ሳይሸራረፍ በዶክተር አብይ እየሾፈረው እንደሆነ በማረጋገጣቸው ድጋፋቸውን ቸረዋል፡፡ የኦህዴድ/ኦዴፓ የፓርቲ የንግድ ኩባንያ ዲንሾ በኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዬት የግል ዘርፉን እየገፋ በመንግሥታዊ ዘርፉን እያፋፋ ቀጥሎል፡፡ የብአዴን/አዴፓ የፖለቲካ የንግድ ኩባንያ ጥረት የካድሬዎቹን ሃብትና ንብረት ሆኖ እንደሚቀጥል ታውቆል፡፡ የደኢህዴን የኢኮኖሚ ኢንፓየር በወንዶ እንደቀጠለ ነው፡፡ በአጠቃላይ በሃገሪቱ የኢኮኖሚ ለውጥ አልተደረገም፣ እንዲያውም እርምት ሳይደረግ ሙሰኞችና ሌቦች ሳይጠየቁ የማርያም መንገድ ተሰጥቶቸው በክብር እንዲኖሩ ተደርጎል የህዝብ ሃብት አልተመለሰም፡፡ ሜቴክ የዘረፈው 77 ቢሊዮን ብር አልተመለሰም፣ በልማት ባንክ የተሰረቀው ብዙ ቢሊዮን ብር በህግ አልተጠየቁም፣ የእነዚህ የፓርቲ የንግድ ኩባንያዎች በህግ ታግደው ለህዝብ በአክሲዮን ተሸጠው በግል ዘርፉ የሚመራ በመንግሥታዊ ዘርፍ የሚታገዝ እስካልተተከለ ለውጥ የለም እንላለን፡፡ በአጠቃላይ የንዋይ መሰረተ ልማት በሃገሪቱ አዲስ የኢኮኖሚ ሥርአት የካፒታል ማርኬት የአክሲዬን ዘርፍ እስካልተስፋፋና ብሄራዊ ባንክ ከግል ባንኮች 27 በመቶ ከሚያበድሩት ገንዘብ ቀርቶ የግሉ ዘርፍ አቅምን እንዲዳብር ካልተደረገ ሃገሪቱ ኢኮኖሚ አያገግምም፡፡ መንግሥታዊው ዘርፍ ከባንኮች 27 በመቶ ገንዘቡን ወሰዶ ለተለያዩ የመንግሥት ፕሮጀክቶች በማዋል ውጤታቸው አመርቂ ሳይሆኑ በሙስናና ሌብነት ተዘርፈው እንደቀረ ከወያኔ ኢህአዴግ በላይ የሚያውቅ የለም አሳማን ሊፒስቲክ መቀባት ቆንጆ አያደርገውም፡፡

የአንድ ሃገር ሦስቱ ዋነኛ የመጨቆኛ ምሶሶዎች ቢሮክራሲ ዋነኛው የባንክ (ገንዘብ)፣ መከላከያ ሠራዊቱ (የጦር መሣሪያ፣ የስለላ ተቆም)፣ እስር ቤቶች ናቸው፡፡ ሦስቱን ማን ይቆጣጠራቸዋል ነው ጥያቄው? ሌላው በጌታው እንትን እንደሚኮራውና እንደሚፎክር ‹ባርያ› ዓይነት ነው፡፡ የቤቶችና ኮንስትራክሽን ባንክ ከስሮ ወደ ንግድ ባንክ መቀላቀል ዋነኛ ሚስጢር የህወሓት ኢፈርት፣ሜቴክ፣ ሜጋ ህንፃ መስሪያ ወዘተ፣ብድር አበድረው ሳይከፍሉ በተበላሸ ብድርነት እንዲሰረዝ በመደረጉ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ የተበላሸ ብድር 40 በመቶ መድረስ ዋና ምክንያት ውስጥ አይካ አዲስ ከፍተኛ ብድር፣ ለጋምቤላ መሬት ወራሪዎች ደን መንጣሪዎች ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ ማበደር፣ለቢ.ኤም.ኢ.ቲ ካንፓኒ 400 ሚሊዮን ብር ብድር በአሮጌ ማሽን መያዣ በማድረግ ብድር በመስጠት፣ ወዘተ የባንክ ፋይናንሻል ዘርፍ በከፍተኛ ድርጅታዊ መረብ ግንኙነት የተሳሰረ የሙስናና ሌብነት ድር ሃገሪቱን ለእዳ ይዳርጋታል ባንኮች ገንዘብ የሚያበድሩት በአድሎዊ የዘርና የክልል ላይ ያተኮረ በመሆኑ ያልተስተካከለ የክልል መንግሥቶች እድገት በሃገሪቱ ጎልቶ ይታያል፡፡ የአንድ ሃገር የሕግ አውጪ(ፓርላማ)፣ የሕግ ተርጎሚ (አቃቢ ህግ)፣ እና ሕግ አስፈፃሚ (ፍርድ ቤት) መንግሥታዊ መዋቅሮች ተናበው ካልሰሩ ህወሓት/ አኢህአዴግ ወደ ኦህዴድ/ኢህአዴግ አሳማን ሊፒስቲክ ቢቀቡት መልሦ አሣማ ነው፡፡ በሃገሪቱ የህግ በላነትን ማስተበቅ ያቃተው መከላከያ ሠራዊትና ፖሊስ ኃይል ደሞዝ የሚሰፍርለትና የሚቀልበው የኢትጵያ ህዝብ መሆኑን አውቆ በህግ እንዲጠየቅ፣ ዜጎች የሚታረዱበት፣ የሚፈናቀሉበትና የሚሰደዱበት ህግ አስፈፃሚው ሠራዊት ባቃት ማነስና ፀረለውጥ ኃይሎች ሰለሚመሩት አንድ ቀን በህግ እንደሚጠየቁና ገቡትን ቃል ኪዳን በመዘንጋት ከፀረ ለውት ኃይሎች ጋር በመወገናቸው ነው፡፡ የለውጡ ሰሞን በ16ቱ ባንኮች በሁለት ሳምንት ውስጥ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ መመንዘሩን፣ በአንድ ወር ውስጥ 4 ሚሊዮን ዶለር መሰብሰቡን ማለትም ዜጎች የውጭ ገንዘብ በእጃቸው ይዘው ባንክ ባለማስገባት የተጫወቱት ሚና ባንኩን ከሥራ ውጪ አድርጎት እንደነበረ፣ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ለመማሪያ እስካልተጠቀምንበት ድረስ ድርጊቱ ይደገማል እንላለን፡፡ የጥቁር ገበያውና መደበኛው የባንክ የምንዛሪ ተመን ያለው የዋጋ ልዩነት መጥበቡ ይታወቃል፡፡ የብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ አምስት መመሪያዎች መሻሻለቸው የዓለም አቀፍ የሐዋላ አገልግሎት፣ የውጪ ገንዘቦችና የውጭ ምንዛሪ አስተዳደርን ለማቆቆም ፣ ዲያፖራ በውጭ ምንዛሪ የሚከፍቶቸው የባንክ ተቀማጭ ሂሳቦች የሚደነግግ መመሪያ፣ ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርዶች የመቀበል፣የማተምና የማስተናገድ ሥርዓት በተመለከተ የወጣው መመሪያ በፋይናንስ ዘርፉና በንግዱ ህብረተሰብ ዘንድ የሚጠብቁትን ያህል ለውጥ ተደረገባቸው ሆነው አልተገኙም፡፡ ዲያስፖራው የመያስቀምጡት የውጭ ገንዘብ መጠን ከ50 ሥህ ዶላር መብለጥ የለበትም የሚለው ድንጋጌ መነሳቱ፣ የባንክ ሂሳብ ዝቅተኛው ተቀማጭ ገንዘብ 100 ዶላር፣ የጊዜ ገደብ የሚቀመጥ የውጭ ሂሳብ መጠን ከ5000 ዶላር ያላነሰ እንዲሆን ተደንግጎል፡፡

{1} የንግድ ባንክ የዲያስፖራ የሞርጌጅ ብድር አካውንት፣ ንግድ ባንክ ለዲያስፖራው የቤት መሥሪያ ብድር ማዘጋጀቱን አስታወቀ›መስከረም 22 ቀን 2011 ዓ/ም) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አማካኝነት ለትውልደ ኢትዮጵያውያን የተሰናዳ የውይይት መድረክ ባንኩ ለቤት መሥሪያና መግዣ የሚሆን የብድር አገልግሎት መስጠት እንደጀመረ ይፋ አድርጎል፡፡ የንግድ ባንክ ፕሬዜዳንት አቶ ባጫ ጊና ባንኩ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በውጭ ምንዛሪ የሚከፈቱየባንክ ሂሳቦችእንዲኖራቸው ሁኔታዎች ስለመመቻቸቱ አስታውቀዋል፡፡ በውጭ የሚኖሩና እድሜቸው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ዲያስፖራዎች የሞርጌጅ ብድር አካውንት በመክፈት ለቤት መሥሪያና መግዣ የሚሆን የብድር አገልግሎት የሚያገኙት ውስጥ፡ {ሀ} ዳያስፖራው ለቤት መሥራት ወይም መግዛት በሚፈልጉበት ወቅት የቤቱን ዋጋ 20 በመቶ በውጭ ምንዛሪ (በዶላር፣ ፓውንድና ዩሮ) ሲቆጥብ ፣80 በመቶ ባንኩ በብድር ለ20 አመታት የሚከልበትን አሠራር ያመቻቻል፡፡ ለተበደረው ገንዘብ የሚከፍለው የወለድ መጠን 10.5 በመቶ ይሆናል፡፡ {ለ} ዳያስፖራው ለቤት መሥራት ወይም መግዛት በሚፈልጉበት ወቅት የቤቱን ዋጋ 30 በመቶ በውጭ ምንዛሪ (በዶላር፣ ፓውንድና ዩሮ) ቅድሚያ ከፍሎ ፣70 በመቶ ባንኩ በብድር ለ20 አመታት የሚከልበትን አሠራር ያመቻቻል፡፡ ለተበደረው ገንዘብ የሚከፍለው የወለድ መጠን 9.5 በመቶ ይሆናል፡፡ {ሐ} ዳያስፖራው ለቤት መሥራት ወይም መግዛት በሚፈልጉበት ወቅት የቤቱን ዋጋ 40 በመቶ በውጭ ምንዛሪ (በዶላር፣ ፓውንድና ዩሮ) ሲቆጥብ ፣60 በመቶ ባንኩ በብድር ለ20 አመታት የሚከልበትን አሠራር ያመቻቻል፡፡ ለተበደረው ገንዘብ የሚከፍለው የወለድ መጠን 8.5 በመቶ ይሆናል፡፡ ባንኩ ለሃገር ውስጥ ዜጋ ለተበደሩት ገንዘብ የሚያስከፍለው የወለድ መጠን 7.5 በመቶ ነው፣ ስለዚህ በዲያስፖራው ወገን ላይ የተጣለው ከ8.5 እስከ 11.5 በመቶ የወለድ መጠን አያበረታታም እናም ተገቢ አይደለም እንላለን፡፡ ከዲያስፖራው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ማግኘት ለሃገርና ወገን ተጨማሪ ጥቅም ስላለው ዲያስፖራው ተጠቃሚ ሆኖ በተዘዋዋሪም ሃገሩን እንዲጠቅም በማድረግ ዲያስፖራው ወገን አድሎ ሊደረግባቸው አይገባም እንላለን፡፡ በኢትዮጵያ ከውጭ የተላከ ገንዘብ/ የውጭ ሐዋላ ከ2000 እስከ 2015 እኤአ በ2000 እኤአ 53 ሚሊዩን ዶለር የነበረው እያደገ መሄዱን የብሄራዊ ባንክ ገዥ ይፋ አድርረው ነበር፡፡ በግምት አንድ ሚሊዩን ከሚሆኑት ባህር ማዶ ሃገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኛች በ2012 እኤአ 2.4 ቢሊዩን ዶለር ከውጭ ሐዋላ ወደ ሀገር ውስጥ እንደገባ የብሄራዊ ባንክ ገልፆል፡፡ በዚህም መሠረት ከባህር ማዶ ከሚኖሩ ኢትዬጵያውያን ወደ ሃገር ውስጥ የተላከ ገንዘብ የዓለም ባንክ ባወጣው መረጃ፣ ከሠንጠረዡ ላይ መመልከት እንደሚቻለው ዝቅተኛ ከውጭ ሐዋላ የተገኘው ገቢ በ2001 እኤአ 18 ሚሊዩን ዶለር የነበረ ሲሆን ከፍተኛ 3 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር በ2013እኤአ እድረት እንዳሳየ መረዳት ይቻላል፡፡ እንዲሁም በ2015 እኤአ 4 ቢሊዩን ዶላር ወደ ሃገር ቤት ገንዘብ ልከዋል፡፡ የሃገራችን ዲያስፖራ ለአንድ ሶስተኛ ህዝብን ቀለብ ሠፋሪዎች በመሆናቸው፣ በሃዋላ ከሦስት እስከ አራት ቢሊዩን ዶላር በመላክ ሲሦ መንግስት በመሆናቸው ስለሃገራቸው ጉዳይ ከማንም በላይ ከወያኔ መንግሥት በላይ ያገባቸዋል፡፡ የ2010ዓ/ም የሃገሪቱ 14 ቢሊዮን ዶላር በጀት ጸደቆል፣ ከዲያስፖራ የተላከው 4 ቢሊዮን ዶላር ነበር ይሄ ማለት 350 በመቶ ሃገሪቱን በጀት ሊሸፍን የሚያስችል ገንዘብ ከዲያስፖራው ወገናችን ለሀገሪቱ አስተዋፆኦ ያደርጋል፡፡ በቀ.ኃ.ሥ ዘመን በ3 ሚሊዮን ብር የተገነባው ሞርጌጅ ባንክ ማንኛውም ሰው ከሚያገኘው ገቢ አንድ አራተኛውን ቆጥቦ ቤት እንዲሰራ ባንኩ ከ20 እስከ 30 አመታት ጊዜ ተከፍሎ በሚያልቅ ብድር በማመቻቸት አገልግሎት በግልፅ፣በእኩልነት ያለአንዳች ልዩነት አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ዓለም አቀፋዊ የሞርጌጅ ባንክ አሠራር ይከተል የነበረ ዘመናዊ ባንክ ነበር፡፡ በደርግ ዘመንም ‹‹የቤቶችና ቁጠባ ባንክ›› በሚል ያው አሰራር ቀጠለ፡፡ በህወኃት/ ኢህአዴግ የሌቦች ዘመን ‹‹የቤቶችና ኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ› በሚል በመቀጠል ብዙ ብድር ለወያኔ ኢፈርት ድርጅቶች ቢሮ መገንቢያ፣ ፎቆች መስሪያ ፣ ህንፃ መገንቢያ ሆኖ ባንኩ በግዳጅ እያበደረ እንዲከስር ተደረገ፡፡ ከዘም የተዘረፈውን ገንዘብ ደብዛውን ለማጥፋት ባንኩን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር አቀላቀሉት፡፡ ዳያስፖራው ለቤት መሥራት ወይም መግዛት በሚፈልጉበት ወቅት የሞርጌጅ ብድር አካውንት በመክፈት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ወይም በሚኖርበት አገር በሚገኝ የኢትዮጵያ ኢንባሲ በኩል ቀርበው የቁጠባ ሒሳብ በመክፈት መቆጠብ እንደሚችሉ ተጠቅሶል፡፡ ኢንባሲው ቅዳሜና እሁድ የባንክ ሥራ ይሰራል ወይ፣ በህግ አግባብ አለው ወይ፣ኢንባሲው እንደ ባንክ መሥራት ይችላል ወይ ለማለት ነው፡፡ አዲሱም የዶክተር አብይ መንግሥት የሞርጌጅ ባንክን ሥራ በማክበር፣ አዲሱም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ እጁን ታጥቦ ሞርጌጅ ባንክን ወደ ነበረበት አለም አቀፋዊ ባንክ አሰራሩ መመለስ ጊዜ አሁን ነው እንላለን፡፡ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ነሀሴ 5 ቀን 2010ዓ/ም ከዚህ በሆላ የመኖሪያ ቤት ግንባታዎች መንግሥት አያካሂድም፡፡ ህብረተሰቡ የመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚካሄድበትን ቦታ ከመምረጥ ጀምሮ በግንባታው በቀጥታ ተሳታፊ እንዲሆን ይደረጋል፡፡ ብለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2005 ዓ/ም ይፋ ባደረገው አራት የመኖሪያ ቤት ፕሮግራሞች የ10/90 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ አንድ ሚሊየን ነዋሪዎች ተመዝግበው ባንክ እየከፈሉ 7 አመታት አስቆጥረዋል፡፡ በ1996 ዓ/ም በተጀመረው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ግንባታ እስከ 2010ዓ/ም ድረስ ለተጠቃሚዎች የተላለፉ 175 ሽህ ቤቶች ብቻ ናቸው፡፡ የ40/60 ቤቶች ጨምሮ ከ132 ሽህ በላይ ቤቶች በግንባታ ላይ ይገኛሉ፡፡

የቤቶችና ቁጠባ ባንክ ዓላማዎች፤ {1} ዝቅተኛ፣መካከለኛና ከፍተኛ ኑሮ ደረጃ ያላቸው ዜጎች በማህበር ተደራጅተው፣ ከገቢያቸው ፣በዝግ አካውንት በየወሩ ገንዘብ በመቆጠብ፣ በረዥም ጊዜ ሞርጌጅ ቤቶች እንዲገነቡ ማድረግ {2} ባንኩ ለቤት አልሚዎች ብርድ በማመቻቸት ለተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች እንደ ገቢአቸው መጠን የረዥም ጊዜ ብድር በማበደር ከተበደሩበት ዓመት እስከ ጡረታ ሊወጡ አንድ አመት እስኪቀራቸው ድረስ ማለትም በትንሹ ከ25 እስከ 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሚከፈል ብድር ያመቻች ነበር፡፡ የባንኩ ዋነኛ ዓለማ ህብረተሰቡ ካለው ገቢ ቆጥቦ ቤት እንዲሰራ ሁሉንም ነገር ማመጫቸት ነበር፡፡ {3} የባንኩ ተበዳሪ ማሳወቅ ያለበት ወርሃዊ ገቢውን የደሞዙን አንድ አራተኛ በወር እየከፈለ በቡዙ አመታት ውስጥ የሚከፈል ብድር ማመቻቸት ነው፡፡ የባንኩ ደንበኛ የህይወት ኢንሹራንስና የእሳት ኢንሹራንስ እንዲገባ ባንኩ ያደርጋል፡፡ የወለድ ምጣኔው 4 በመቶ ነበር፡፡ወያኔ ዛሬ 7.5 በመቶ የወለድ ምጣኔ ይጠይቃል፡፡ {4} መንግስት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ለመቅረፍ የፖሊሲና የስትራቴጂ ለውጥ ማድረግ ይጠበቅበታል ማለትም ሞርጌጅ ባንክን ማፍረስ አልነበረበትም፡፡ የቤቶችና ገንዘብ ቁጠባ ባንክ ከ15 እስ 30 ዓመታት ለሚደርስ ጊዜ በማበደር በአለማችን አሥራሩ ይታወቃል፡፡ የንግድ ባንክ ለንግድና ለማኑፋክቸሪንግ ሥራዎች ከ5 እስከ 10 ዓመታት ጊዜ የሚቆይ ብድር ለደንበኞቹ ያመቻቻል፡፡ {5} የቤት አልሚዎች መጠነ ሠፊ ተሳትፎ የነበራቸው በመሆኑ ግልፅ አሠራር፣ ተጠያቂነት፣ የባለቤትነት ስሜትና ከቤቱ ግንባታ ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በጋራ ቤቶች ግንባታ ሥራ ላይ ይሰማሩ ነበር፡፡ እንደዛሬው ግልፅ ያልሆነ ለአድሎ በር ከፋች የሆነ ሎተሪ ብሎ ጨዋታ የለም፡፡ ቤት ሠሪው ተጀምሮ እስከሚጨረስ መብትና ግዴታውን ያውቃል፡፡ {6} ሞርጌጅ ባንክ በሃገሪቱ ያለውን የቤት ልማት ችግርን ለመቅረፍ መልሶ ማቆቆም ብቸኛው ዋነኛ መፍትሄ ነው፡፡ ዲያስፖራው ወገናችንም የዚህ እድል ተጠቃሚ መሆን ይችላል፡፡

ሞርጌጅ ባንክ፣-አቅም ላላቸው የአገር ውስጥ ሥራ ተቆራጮችና አማካሪ ድርጅቶችን ሙሉ ለሙሉ ኮንትራት ሰጥቶ እየተከታተለ ቤቱ እንዲገነባ ማድረግ ይቻላል፡፡ ሞርጌጅ ባንክ በኩል መንግሥት ለሪል እስቴት አልሚዎች መሬት በዝቅተኛ የሊዝ ዋጋ በማቅረብና፣ መሠረተ ልማት መንገድ መብራት፣ውኃ የመሳሰሉትን በማሞላት፣ከሞርጌጅ ባንክ ጋር ትስስር መፍጠር ይችላል፡፡እንዲሁም ሞርጌጅ ባንክ፣ የአገር ውስጥና የውጭ ተቆራጮችና የሪል እስቴት አልሚዎች በተናጥል ወይም በሽርክና እንዲሠሩ መጋበዝ ይችላል፡፡ በተመሳሳይ በመንግሥት ሥር የሚገኙ 17 ሽህ ቤቶች ለግሉ ዘርፍ በግልፅ ጨረታ ተሸጠው ገንዘቡን ለወጣቶች የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ ፕሮጀክቶች በሃገር አቀፍ ደረጃ በባለሙያዎች ተቀርፀው መተግበር ያስፈልጋል፡፡ በፊዴራል ደረጃ ካሉ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መካከል 77 ቢሮዎች፣ የራሳቸው ቢሮዎች/ህንፃ የሌላቸው ስለሆነ የግለሰብ ህንፃን ተከራይተው 380 ሚሊዩን ብር በዓመት ይከፍላሉ፡፡

{2} በኢፈዴሪ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲና የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ፣ በየካቲት ወር 2009 ዓ/ም እንደ አዲስ በድጋሚ የተቆቆመው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ በ33 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ካፒታል የተቆቆመ ድርጅት ሲሆን፣ በማስተር ፕላኑ ዞን 3 እና 4 ውስጥ እስከ 10 ፎቅ የሆኑ በአጠቃላይ 16 ሽህ ቤቶችን ለመገንባት እቅድ አውጥቶል፡፡ ቤቶቹ ለመንግስት ተሸሚዎች፣ ለሠራተኞችና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በኪራይ ለማስተላለፍ ነው፡፡ በመንግሥት በጀት፣ ለመንግስት ተሸሚዎችና፣ ሠራተኞች የቤት ግንባታ ማድረግ የጥቅም ግጭት፣ መጠቃቀምና፣ የአድልኦ አስራርን በሃገሪቱ ያሰፍናል፡፡ የ10/90 እና 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ከ20 እሰከ 30 ቢሊዮን ብር ቁጠባ ሂሳብ አስቀምተው ሰባት አመት ቤት ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡መንግሥት የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ ለሹማምንቶቹ 33 ቢሊዮን ብር መመደቡ ሌብነት ነው እንላለን፡፡ የንግድ ባንክ የዲያስፖራ የሞርጌጅ ብድር አካውንት፣ በግልፀነትና ታማኝነት ካልተሠራ ገንዘባችሁ ይዘረፋል ተጠንቀቁ!!!

__
ማስታወሻ:በዚህ ጽሁፍ ላይ የተንጸባረቁ ሳሃቦች የጸሃፊውን/የጸሃፊዋን እንጂ የድረገጹን አቋም አያንጸባርቁም።
ነጻ አስተያየት ወይንም ሃሳብ በዚህ ድረ ገጽ ለማውጣት ጽሁፍዎትን በ info@borkena.com ይላኩልን።

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here