በአዲስ አበባ ከተማ ህገ ወጥ የመሬት ወረራ መበራከቱን ፖሊስ አስታወቀ

Ethiopian News and Opinion

ቦርከና
ጥቅምት 9 ፤ 2011 ዓ.ም.

በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ወረራን ጨምሮ ህገ ወጥ ተግባራት እየተበራከቱ መምጣታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ማስታወቁ ተዘገበ።

እንደ ፋና ብሮድካስቲንግ ዘገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን እና ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት አመራሮች እና ባለ ድርሻ አካላት በትላንትናዉ ዕለት ውይይት ባደረጉበት ወቅት የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሜጀር ጄኔራል ደግፌ በዲ፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማዋ ህገ ወጥ የመሬት ወረራና ተግባር እየተበራከተ መምጣቱን መናገራቸዉ ታቋል።

ኮሚሽነሩ ከመሬት ወረራው ባሻገርም የኮንትሮ ባንድ ንግድ እና ህገ ወጥ የመንገድ ላይ ንግድ መበራከቱንም ተናግረዉ ይህን ለመከላከልና የህግ የበላይነትን ለማስፈንም ህብረተሰቡን በማሳተፍ ውጤታማ ስራ ሊያሰራ የሚያስችል እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር መግባት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

ለወንጀሉ መስፋፋት መንስኤ በሆኑ ጫት ማስቃሚያ፣ ሺሻ ማስጨሻ እና ቁማር ማጫወቻዎች ላይ ልዩ ትኩረት ይሰጣል ያሉት ኮሚሽነሩ፥ የተደራጁ ወንጀለኞች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃም ተጠናክሮ ይቀጥላልማለታቸዉን ዘገባዉ አስፍሯል።

በሰለሞን ይመር

ወቅታዊ እና ሚዛናዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።

Published
Categorized as ዜና

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *