spot_img
Wednesday, November 29, 2023
Homeአበይት ዜናበአላማጣ ከተማ ሰባት ሰዎች በፀጥታ ሀይሎች መገደላቸዉ ተሰማ

በአላማጣ ከተማ ሰባት ሰዎች በፀጥታ ሀይሎች መገደላቸዉ ተሰማ

advertisement
Alamata_
ፎቶ: ከማህበራዊ ሚዲያ

ጥቅምት 12 ፤ 2011 ዓ.ም.

በትላንትናዉ ዕለት በደቡብ ትግራይ አላማጣ ከተማ ከራያ ህዝብ ማንነት ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ግጭት በጥቂቱ ሰባት ሰዎች በክልሉ የፀጥታ ሀይሎች ሲገደሉ በርካቶች ደግሞ መቁሰላቸዉን በስፍራዉ የነበሩ የአይን እማኞች ለቦርከና ገልፀዋል፡፡

የራያ ህዝብን የማንነት ጥያቄ በተመለከተ በተጠራዉ ሰልፍ ላይ በመገኘት ድምፃቸዉን ለማሰማት በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢዉ ነዋሪወች ረፋድ ላይ ወደ አደባባይ መዉጣታቸዉንና የትግራይ ክልል ልዩ ሀይሎች ተኩስ መክፈታቸዉንና ለሰዓታትም ከተማዋ በተኩስ ስትናጥ እንደዋለች ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

ከሆስፒታሎች የሚወጡ መረጃወች እንደሚያሳዩት ከሆነ ሰባት ሰዎች ህይወታቸዉ እንዳለፈና ከሀያ በላይ ሰዎች በፅኑ መቁሰላቸዉንና ወደ ጤና ተቋማት ተወስደዉ ህክምና እየተደረገላቸዉ እንደሆነም ለመረዳት ተችሏል፡፡

በትላንትናዉ ዕለት በማህበራዊ ሚዲያዉ የሚወጡ መረጃዎችና ፎቶዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ በርካታ ቁጥር ያላቸዉ ሰዎች በከተማዉ አዉራ መንገዶች ላይ እየተንቀሳቀሱ ተቃዉሞአቸዉን ሲያሰሙ እንደነበርና ከዚህም ጋ ተያይዞ በርከት ያሉ ወጣቶች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ለመረዳት ተችሏል፡፡

“በአላማጣ ከተማ በማንነት ስም በሚንቀሳቀሱ አካላት እና በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት የሶስት ሰዎች ህይወት አልፏል። በፀጥታ አካላት ላይም ጉዳት መድረሱን ገልጾ የህዝብን የማንነት ጥያቄ በማስመሰል ሌላ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እየተደረገ ያለው ሩጫ በማንኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው” በማለት ገልጧል ፤ የትግራይ ክልላዊ መንግስት፡፡

የራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄ ባለፉት አመታት በተለያየ መልኩ ሲነሳ የነበር ቢሆንም በሁለቱ ክልሎችም (በትግራይ ክልል እና በአማራ) ሆነ በፌደራል መንግስቱ ጣልቃ ገብነት የተወሰደ መፍትሄ ባለመኖሩ፤ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአካባቢዉ ተደጋጋሚ ግጭቶችና መፈናቀሎች ሲከሰቱ ቆይተዋል፡፡

በሰለሞን ይመር
ወቅታዊ እና ሚዛናዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here