
ጥቅምት 12 ፤ 2011 ዓ.ም.
ለረጂም አመታት በትጥቅ ትግል ላይ የነበረዉ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ማስታወቃቸዉን ፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት ዘግቧል።
እንደዘገባዉ ከሆን የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባርና የኢትዮጵያ መንግስት በትላንትናዉ ዕለት በአስመራ ባደረጉት ድርድር ነዉ ከስምምነት ላይ የደረሱት።
በስምምነቱም የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጪ ግንባር ወደ ሀገር ቤት ተመልሶ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ስምምነት ላይ መድረሱን እንደተገለፀ ዘገባዉ ያመላክታል፤ ሆኖም ግን ሌሎች የስምምነቱ ዝርዝር ነጥቦች አላተካተቱም።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ያቀረቡትን የሰላም ጥሪ ተከትሎ ኦነግ፣ አርበኞች ግንቦት 7 እንዲሁም የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደምህት) የትጥቅ ትግል በማቆም ወደ ሀገር ቤት መግባታቸው ይታወቃል።
ሆኖም ግን መንግስት በትጥቅ ትግል ሲያደርጉ ከነበሩ ድርጅቶች ጋር ያደረጋቸዉ ዝርዝር ስምንነቶች በዉል ባለመገለፃቸዉ ምክኒያት የተለያዩ እሰጣ እገባዎች ሲፈጠሩ ታይተዋል፡፡
ለአብን ያክል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የትጥቅ ትግል በማቆም ወደ ሀገር ቤት መግባቱን ቢነገርም የኦነግ ታጣቂዎች ነን የሚሉ ሀይሎች በተለያዩ ቦታዎ ች ትጥቅ ሳይፈቱ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ታዉቋል፡፡
የኦነግ አመራሮችም ትጥቅ ለመፍታት ተስማምተን አልመጣንም በማለት ለመገናኛ ብዙሀን ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡
በሰለሞን ይመር