ሳህለወርቅ ዘውዴ የመጀመሪያ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት በመሆን ቃለ መሃላ ፈጽመዋል

Sahle-Work-Zewde
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
ፎቶ ምንጭ : የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

ቦርከና
ጥቅምት 14 ፤ 2011 ዓ.ም.

በአፍሪካ ሕብረት የተባባሩት መንግስታት ተወካይ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ ዛሬ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና የፌደሬሽን ምክር ቤት አባላት ባደረጉት የጋራ ልዮ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ፌደራላዊት ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት በመሆን ተመርጠዋል።

ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ለምክር ቤቶቹ የመልቀቂያ ደብዳቤ አቅርበው ተቀባይነት ካገኘላቸው በኋላ ነበር ሳህለወርቅ ዘውዴ በፕሬዝዳንትነት እንዲያገለግሉ የተመረጡት።

በበርካታ የአፍሪካ የፈረንሳይኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሃገራት እና በፈረንሳይም ጭምር በኢትዮጵያ አምባሳደርነት ያገለገሉት ሳህለወርቅ ዘውዴ መመረጥ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች የተቀባበሉት ዜና ሆኗል።

በፕሬዝዳንትነት ለመስራት ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በኋላ ባደረጉት ንግግራቸው ስለ ሰላም እና የሴቶች ተሳትፎ ስለማሳደግ አጽኖት የሰጡ ሲሆን በኢትዮጵያ እየታየ ላለው ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ቀጣይነት እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።

ሰላም ለብልጽግና ቅድመ ሁኔታ ነው በማለትም አስታውሰዋል።
___
ወቅታዊ እና ሚዛናዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.