spot_img
Tuesday, June 25, 2024
Homeነፃ አስተያየት.የ"፫ኛውን-እጅ-ሕውሃት"ን በ"ሌጌዎን"ነቱ፤አልሰሙም ብዬ አልዋሽም። (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ)

.የ”፫ኛውን-እጅ-ሕውሃት”ን በ”ሌጌዎን”ነቱ፤አልሰሙም ብዬ አልዋሽም። (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ)

ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ

የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት ለሠላም እና ለፍቅር ያለማንም ጣልቃ ገብ እየተደራደሩ ነው፤ ዳኛው ደግሞ ሕዝብ ብቻ ነው፤ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፤በፍቅር ልሳን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይዘው መጓዝ ከጀመሩ ማግሥት፤የ”ሶስተኛው-እጅ-ሕውሃት”ምን እያደረገ እንደሆነ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠንቅቆ ያውቃል። ለሕዝብ በንግግርዎ ላይ “ያለ-ይሉኝታ” ስላልተጋለጠ፤የኢትዮጵያ ሕዝብ አላስፈላጊ መስዋዕትነት በግድ እየከፈለ ይገኛል፤እርስዎ ግን የ”ዋህነት”አይሉት “ተላላነት፤” ቢያንስ በሕዝባዊ ንግግርዎት ውስጥ ማን እነዚያን ጥፋቶች ሁሉ እንደፈፀማቸው ያለ-ይሉኝታ በግልፅ የ “አንዳንዶቹ ቆሻሾቹ እና ተንኮለኞቹ የሕውሃት” አባላት መሆናቸውን አጋልጠው አያውቁም።ይህን ከባድ ኃላፊነት ለመሸከም፣ከእርስዎ የሚበልጥ ማን ባለሥልጣን ይችላል?በአሁኗ ውዷ ጊዜማ:-በመፈናቀል ላይ ያሉ ለስደት ሊዳረጉ የሚጠባበቁ በሚሉዮን ተቆጥረዋል፤ይህን ሐቅ ያውቃሉ ብዬ እመሰክራለሁ።ይሁን እንጂ ሥራዎትን በትኩረት እንዳያከናውኑና ከ”ሕውሃት”መካከል ቆሻሾቹ እና ተንኮለኞቹ ግን የራሳቸውን የልወደድ የ”ሞት-ሞት” ምኞት ተስፋ በመትከል እና ሕዝብን ለማዘናጊያ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ።

ይህን ክጀላ ከመንፈሳዊ ዓይነ-ልቡና አንፃር ስንመለከተው ደግሞ የ”ጌርጌሴኖኑን”እብድ ሰው ታሪክ እና የአጋንንቱን “ሌጌዎን”ን ታሪክ ከመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያስታውሰናል።ይህንን ተምሳሌት የመረጥኩት የሥጋዊ ጥፋቱ ያን ጊዜ በጠበል ከፓርላማ የተወገደ ቢሆንም ርኩስ መንፈሱ ግን በ”አንዳንዶቹ ቆሻሾቹ እና ተንኮለኞቹ የሕውሃት”አባል ላይ በመኖሩ ነው። በነገራችን ላይ አጋንንት የሚተነኩሉት በቡድን እና በአንድነት መሆኑን ማሳያ የጌርጌሴኖኑን እብድ ሰው ታሪክ በጣም ጥሩ ምሳሌነት አለው።(የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ቁ ፱)

ለዚህም ነው፣በምሳሌነት ምንጊዜም የ”ሌጌዎንነት” ርኩስ መንፈስ የሚወሳው።”ሌጌዎን”ማለት የተደራጀ ርኩስ ቡድን ብዙ ሰዎች፣በርካታ ወይም መንጋ ማለት ነው።”ሌጌዎን”የሚለው ቃል ግን ስለአጋንንት ቡድናዊ አሰራር በሚገባ ስለሚያሳይ ለ”ሦስተኛው እጅ”እጅግ ገላጭ ነው።”ሌጌዎን” ሲባል የአንድ ወይም የሁለት አጋንንቶች ብቻ አይደለም፤ቢያንስ አጋንንቶቹ ከሁለት ሺህ ያላነሱ መሆናቸውን ከቅዱስ መጽሐፋችን ውስጥ እናነባለን።(እነዚያ ወጣቱን ዘቅዝቀው የሰቀሉት እና የገደሉት፣ በገጀራ የመንፈሳዊ አባቶችን እና ሕጻናትን አንገት ያረዱትን ልብ ይሏል)በአሁኑ ጊዜ ያለምንም ይሉኝታ በኢትዮጵያውያን ላይ ደባ እየተነኮለ ያለው”አንዳንዶቹ ቆሻሾቹ እና ተንኮለኞቹ የሕውሃት”አባል እንደሆነ ድፍን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠንቅቆ ያውቀዋል፤እርስዎም እንደሚያውቁ እርግጠኛ ነኝ።ቁም-ነገሩ “ስለ ዓለም ማወቁ ብቻ አይደለም፤ዓለምን መለወጡ ላይ ፈተናው የሚያበቃው፣”እንደሚባለው ነው።ለአፈፃፀም እንዲያመች በዝርዝር ፈታኙን ክስተት በመረጃ እንመልከተው፤

ባለፉት ጊዜያት በዚሁ ርዕሰ-ጉዳይ http://www.ethioreference.com/archives/14051 መረብ ላይ በሰው ልጅ ታሪክ ላይ የሶስተኛውን እጅ አመጣጥን ገልጫለሁ።ለምንስ ሦስተኛው እጅ ከሕውሃት የክፋት እጁን ዘርግቶና በጣልቃነት አስገብቶ:-በሕዝቡ ሁለት የሰላም እጆች መካከል ውስጥ ገብቶ ጥፋት ለመፈፀም እንደሚፈልግና በጥቅሉ ለግል ጥቅሙ የሚቆም ስለመሆኑ አስነብቤአለሁ።ልብ እንድንለው ብቻ ሳይሆን፤እባቡ ሕውሃት:-በባሕርይው ፣የተለሳለሰ፣ የሚሹለከለክ፣የሚመሳሰል፣የሚጠቀለል፣የሚዘረጋ፣የሚናደፍ፣የሚተጣጠፍ፣የሚወረወር ተናዳፊ ርጉም ፍጡር ነው።ችላ እንዳይባል!!!የሚያሳየውን ፀረ-ፍቅር እና ፀረ-ሰላም በሕቡዕ እያደረገ፤ሲብስም ድንገት የነካውን በመንደፍ አደጋውን እና መርዙን የሚተፋው አዘናግቶ በመሆኑ በዚሁ መረብ ላይ እባብነቱን አሳስቤአለሁ፤ እስከዛሬም በእርስዎ በኩል ግን በሚያምኑበት ምክንያት ትኩረት አልሰጡትም።

በተለይም ቅን እና አስተዋይነትዎን በሌላ ትርጉም በመውሰድ፤እርስዎ የሕውሃት ጉዳይ አስፈፃሚ እንደሆኑ በሕውሃት ካድሬዎቹ እያስነገረ ብቻ ሳይሆን፣በፀረ-መንግሥትነት ተግባር በሕቡዕ የሚፈፅሙትን ባለሥልጣናት የልብ ልብ እየሰጣቸው ጠቅላይ ሚኒስቴራችንንም ሆነ ሕዝቡን እየናቁት በትዕቢት”እኛ ነን ፕሮግራሙን ያወጣነው” እያሉ ሕዝቡን በትዕቢት ንቀው በአደባባይ ሲናገሩ፤በደም የተጨማለቀ እጃቸውን እነሱ ማየት ስለማይችሉ ሳያውቁት ያሳያሉ።ይህም የደባቸው-ሐቅ በየአንዳንዳችን ቢታወቅም፤የጋራ ለውጣችንን የምንደግፈው ሁሉ በሕዝብ የታወቀ ስለሆነ እየተበራታ ይገኛል።ፈተናችን ግን የሰላም እና የፍቅር ተስፋችንን ሦስተኛው እጅ በእርስዎ የይሉኝታም ይሁን፣የታጋሽነትዎ ባሕርይ፤ለሕውሃት ወያኔ ቡድን የተደጋገመ የጥፋት ዕድል ሰጥተውት ድንገት ተስፋችንን እንዳያጨልመው በየሰከንዷ ከመስጋት አልታቀብንም።

በትግራይ ሕዝብ ጉያ ውስጥ ተሸሽጎ ያለው”አንዳንዶቹ ቆሻሾቹ እና ተንኮለኞቹ የሕውሃት”ሌጌዎን”አባል ቡድን፤አዲስ አበባ ተሽሎክልኮ፣ወደሐረር ተስፈንጥሮ፤በየዲፕሎማሲዎቹ ሥራዎች እየተለሳለሱ፤ ከሕዝብ ጋር እየተመሳሰሉ ማጭበርበር፤ ሲነቃባቸው ቀለሙን ቀይሮ መመሳሰል፤ከባሰ ግን ከመናደፍ አይመለስም።

እያንዳንዱን ትንኩልናዎች ከሰኔ ፲፮ የግድያ ሙከራ ጀምሮ:-የኢንጅነር ስመኘውን አሳላጭ ግድያ ጨምሮ፤የነበረውን ብንቆጥር ታሪኩን ደጋግሞ ከማውራት አያልፍምና ወደተግባር መጓዙን ወደድኩት፤ይህም ሁለተኛው ማሳሰቢያዬ ሆኖ ይቆጥርልኝ።”ብዬ ነበር” ለማለት ፈልጌ ሳይሆን የመፍትሄው አካል ነኝና:-በሃምሳሉ የፈጠረን እግዚአብሔር የሕሊና ዳኝነትንም ሰጥቶናልና በሰብዓዊነት ሳንዘገይ ሕሊና ዳኝነትም እንድንጠቀምበት ለማገናዘብ ነው።

ያለበለዚያ ሦስተኛው እጅ ራሱ “ሕውሃት”በግልፅ ትንኩልናው ከነብስ ግድያ አልፎ ወደ የመንግሥት ጠለፋ ከመሸጋገር አይመለስምና፣ከደብረዘይት የአየር ኃይል ክፍለጦሮች የ”ተዘረፉትን የጦር ማናቸውንም ነገር ወደ ማዕከላዊ መንግሥት እንዲመለስ ማድረግ ይገባል።ወደፊት የትግሬው ክልል በማስፈራሪያነት ያለአግባብ መአከላዊ መንግሥቱን ራቁቱን በማስቀረት ሕገወጥ ሥራዎችን ለመፈፀም ይችላል።የሚገርመው ደግሞ “ሕውሃት”የራሱ ካድሬዎች ትጥቃቸውን ሳይፈቱ፤ ኦነግ፣ጎንደር፣ጎጃም፣ጋምቤላ ሌሎቹንም እንደመንግሥት ሆኖ ፍቱ የሚል(ዓይነ-ደረቅ ሌባ፣ቃጭል ይዞ ይገባል እንደሚባል)ይሉኝታ-ቢስ የጥፋት ቡድን ነውና በትዕቢት ትዕዛዝ መስጠቱ በውስጡ ያለውን “ሌጌዎን”እንድናስተውል ያደርገናልና ሳይዘገዩ ርምጃ ሊወስዱ ይገባል።እናም ሕዝብ ጠንቅቆ እንዲያውቅ መንፈሳዊ ግዴታዎም ይሁንና ዛሬም የ”፫ኛውን-እጅ-ሕውሃት”በ”ሌጌዎን”ነቱ፤አልሰሙም ብዬ አልዋሽም።

ማስታወሻ:በዚህ ጽሁፍ ላይ የተንጸባረቁ ሳሃቦች የጸሃፊውን/የጸሃፊዋን እንጂ የድረገጹን አቋም አያንጸባርቁም።
ነጻ አስተያየት ወይንም ሃሳብ በዚህ ድረ ገጽ ለማውጣት ጽሁፍዎትን በ info@borkena.com ይላኩልን።

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here