spot_img
Wednesday, June 7, 2023
Homeአበይት ዜናየህዝብ ተወካዮች ምክርት ቤት መዓዛ አሸናፊን የፌደራል ጠቅላይ ፍ ቤት ፕሬዝዳንት...

የህዝብ ተወካዮች ምክርት ቤት መዓዛ አሸናፊን የፌደራል ጠቅላይ ፍ ቤት ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾመ

- Advertisement -
መዓዛ አሸናፊ
መዓዛ አሸናፊ
ምንጭ : ኢዜአ

ቦርከና
ጥቅምት 22 ፤ 2011 ዓ.ም.

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በነበረው ውሎው መዓዛ አሸናፊን የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟቸዋል።

ከሶስት ቀናት የአውሮፖ የስራ ጉብኝት የተመለሱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለፓርላማው ለማጸደቅ ካቀረቧቸው በኋላ ነበር በሙሉ ድምጽ የተመረጡት።

ከተመረጡ በኋላ ባደረጉት ንግግር የፍትህ ተቋማት በህብረተሰቡ ውስጥ ያጡትን ተዓማኒነት መመለስ ተቀዳሚ ተግራባቸው እንደሚሆን ተናግረዋል።

ከፋና ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ደሞ ሴቶች እየተሾሙ ያሉት ሴት በመሆናቸው ሳይሆን በብቃት እንደሆነ አስረግጠው በመናገር ፤ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትነት ስራቸውን በሚጀምሩባቸው በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራቶች ፍርድ ቤቱን እንደተቋም በማጥናት ያሉበትን ችግሮች ነቅሶ በማውጣት ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ውሳኔ በማሳለፍ የማስተካከያ ርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረዋል።

መዓዛ አሸናፊ ማናቸው?

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ወ/ሮ መዓዛ የተወለዱት አሁን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ተብሎ በሚታወቀው ክልል በአሶሳ ከተማ ሲሆን ፤ በአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ በፍርድ ቤት ዳኛነት ለሶስት ዓመታት ያህል አገልግለዋል።

አሁን በስራ ላይ ያለው ህገ መንግስት ሲረቀቅ በአማካሪነት እንደተሳተፉም የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በዘገባቸው ጠቁመዋል።
በዓለማ ዓቀፍ ግንኙነት ከኬንታኪ ዮኒቨርስቲ የማስትሬት ዲግሪ እንደያዙም ለማወቅ ተችሏል።

ከዚያም በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሴት ጠበቆች የሙያ ማህበር በማቋቋም ለአስርት ዓመታት ያህል መርተዋል ፤ ለሴቶች መብት (ያለክፍያም ጭምር) ጥብቅና በመቆም ይታወቃሉ።

በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ደሞ የእናት ባንክ መስራች አና የቦርዱ ሊቀመንበር በመሆን ሰርተዋል ፤ ባንኩንም ስኬታማ እንዳደረጉት ይነገርላቸዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጂት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የሴቶች መብት አማካሪ ሆነው በመስራት ላይ እያሉ አሁን ለያዙ የኃላፊነት ቦታ የተሾሙት።

ወቅታዊ እና ሚዛናዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,879FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here