advertisement
ቦርከና
ኅዳር 16 ፤ 2011 ዓ. ም.
ዛሬ በትግራይ ዘጠኝ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ እንደተካሄደ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በአድዋ፣ አክሱም፣ ኮረም፣ አዲ ሽሁ፣ አላማጣ፣ መኾኒ፣ ሰቲት ሁመራ፣ ዓብይ ዓዲ እና ራያ የተካሄዱት ሰልፎች የህግ የበላይነት እንዲከበር ፤ በሙስና ተጠርጥረው የተያዙ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ብቻ እንዲዳኝ ፤ እና መሰል ጥያቄዎች ተስተጋብተዋል -እንደ መንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘገባ።
በተጨማሪም የማንነት ጥያቄዎች (የወልዋይት እና የራያን የሚመለከት ነው) የማንነት ጥያቄዎች አይደሉም ፤ ህዝቡን አይወክሉም የሚሉ መፈክሮች በየከተሞቹ በነበሩት ሰልፎች ላይ ተስተጋብተው እንደነበር ለማወቅም ተችሏል።
በወልቃይት እና በራያ የማንነት ጥያቄ ለአመታት ሲስተጋባ መቆየቱ ይታወሳል። እነዚህ አካባቢዎች ወደ ትግራይ የተከለሉት የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ስልጣን መያዝን ተከትሎ መሆኑ ይታወቃል።
___
ወቅታዊ እና ሚዛናዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።