spot_img
Thursday, November 30, 2023
Homeዜናለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት 50 መገናኛ ብዙኃን ተመረጡ

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት 50 መገናኛ ብዙኃን ተመረጡ

advertisement

ቦርከና
ኅዳር 23, 2011 ዓ.ም.

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት 50 የሀገር ውስጥ እና የውጭ መገናኛ ብዙሀንን በኮሮስፖንዳንትነት እንዲሰሩ የመረጠ ሲሆን ሁለም የሚዲያ አካላት በጠቅላይ ሚኒስትሩና በሚመለከታቸው ባለስልጣናት የሚሠጡ መግለጫዎች በቀጥታ ስርጭት እንዲስተላልፉ ጽ/ቤቱ ያወጣውን መስፈርት አሟልተው በመገኘታቸው ከ ጽ/ቤቱ ፍቃድ አግኘኝተዋል፡፡

የብሮድካስት መገናኛ ብዙኃን በዋናነት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳዮችን በዜና እና ወቅታዊ ሁነቶች በመዘገብ፣ በወጥነት መስራትን በመስፈርትነት መጠቀሙ የተጠቆመ ሲሆን ለህትመት መገናኛ ብዙኃን ደግሞ የጋዜጣው ስርጭት ከ5 ሺህ ኮፒ በላይ መሆኑና ከአንድ ዓመት በላይ በስርጭት መቆየቱ እንዲሁም በስርጭት ቆይታው 1 ዓመት ባይሞላው እንኳ ከ8 ሺህ ኮፒ በላይ እያሳተመ መሆኑ መስፈርት ያስቀመጠ ሲሆን መስፈርቱን አማልተው ለተገኙ 50 መገኛና ብዙሀን ብቻ ፍቃድ መስጠቱን አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘግባል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ባወጣው መስፈርት መሰረት ከግልና ከመንግስት ህትመቶች ስምንት የተመረጡ ሲሆንበኮሮስፖንዳንትነት የተመረጡ መገናኛ ብዙኃን፤ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት በሚሰጡ መግለጫዎች ላይ በመገኘት ጥያቄ የማቅረብ እድል እንዲሁም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የሚሰጡ ዋና ዋና መግለጫዎችም በተለያዩ ቴሌቪዥኖች የቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍ ይችላሉ ተብሏል፡፡

በፍሬህይወት ዮሃንስ
_____
ወቅታዊ እና ሚዛናዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here