advertisement
ቦርከና
ኅዳር 25, 2011 ዓ.ም.
ከአዲስ አበባ ወደ ቻይና በሚጓዝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ በተደረገ ፍተሻ 6 ሺህ 170 ፓውንድ፣ 33 ሺህ 175 ዩሮ እና ከ1 ሚሊዮን 364 ሺህ ብር በላይ የሆነ ብር በህገ ወጥ መንገድ ከአገር ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።
ኢዜአ እንደዘገበው ገንዘቡ በቁጥጥር ስር የዋለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ የሆነ ግለሰብ ያለ መፈተሽ መብቱን ተጠቅሞ ወደ ቻይና ለምትጓዝ መንገደኛ ለማቀበል ባደረገው የሙከራ ጊዜ ሲሆን የአየር መንገዱ ሰራተኛ ወዲያው በቁጥጥር ስር ሲውል ወደ ቻይና የምትጓዘው መንገደኛ ደግሞ አውሮፕላኑ ከ3 ሰአታት በረራ በኋላ ተመልሶ እንዲያርፍ በማድረግ በቁጥጥር ስር ለማዋል ችላለች።የፌዴራል ፓሊስም ጉዳዩን እያጣራ መሆኑንም የገቢዎች ሚኒስቴር ገልፃል ፡፡
በፍሬህይወት ዮሃንስ
__
ወቅታዊ እና ሚዛናዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።