ሀቢቡ ታከለ
ታህሳስ 19 ፤ 2011 ዓ.ም.
ዛሬ ጡአት ተነሳሁና ደግሞ ነጋ ብየ እንደሁለ ቀኑ ከኢትዮጵያ የሚኖሩ ዜናዎችን ከደሀረገፅ ድሀረገፅ ሳገላብፅ ዶከተር አብይ ሰለታክስ ሲናገሩ ሰማሁአቸው። ከአንድ ወር በፊት ጎንደር እያለሁ አንድ ሰለታክስ የሰማሁትንና ያዶክተር አብይ “እዳ” ያልኩብትን ታርክ አጫረብኝ።
በዚሁ ቆይታየ አንዳንዴ አፍ አካፋች ስፈልግ በሚሌነም ጎንደር ፕሮጀክት ጊዜ ወደአገሩ ገብቶ ሆቴል ከከፈተ ጉዋደኛየ ብቅ እላለሁ። አንድ ቀን ወደዚህ ልመጣ ሰሞን ወደ ሆቴሉ ጎራ አልኩና ልንጫወት ከጠረጴዛው ዙሪያ ከበን ቁጭ ብለን ማውራት ጀመርንና “ነገ ወደባህርዳር ስለምሄድ አብረን እንሂድ አለና” ጠየቀኝ “ምን ጉዳይ አለህ?” አልኩና መልሼ ጠየቅሁት። እሱም አንዱ የከተማው ታክስ ስብሳቢ መጣና ካምስት አመት በፊት ያልከፈልከው 500000 ብር እዳ አለብህ ይልዋል።”
ጉዋደኛየም “ከፈያለሁ” በመቀጠልም “አካውንታንቴን አናግራለሁ” አለውና በዚህ ለዚያን ቀን ተለያየን አለኝ ። በነገታው አንድ ሰው ከዚህው መስሪያ ቤት ይመጣና ያገኛዋል።
ከዚያም ከትውውቅ በሁዋላ “እኔ ስራ አቀላጣፊ ደላላ ነኝ፣ የብዙ ሶዎችን እንዳንተ የቆየ ታክስ ይሁን ወይም አሁን የሚከፈል ታክስ እንደገና እንዲታይና በትክክል እንዲከፈል ማድረግ እችላልሁ” አለና በመቀጠል፣ ለምሳሌ “አንዱ እንዳንተ አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺ ብር ታክስ መክፈል ያለበትን እኛ ካየን በሗላ 400000 ብር እንዲከፈል ሆነና ለኛ አገልግሎት ሁለት መቶ ሺ ብር ከፈለን። ያንተንም እንደሁ ካየን በሁዋላ የምትከፍለውን ታክስ ቀንስህ እንድትከፍል እናረግና ለኛ አገልግሉት የሚገባነን ትከፈለናለህ አለው።”
እና “ምን አልከው” አልኩት
ጉዋደኛየም “ባህርዳር ሄጄ ይግባኝ እላለሁ ብየ አሰናበትኩት” አለኝ
በጣም ገረመኝ። ይህ ነገር አሁን በለውጥ ጊዜ የቀረ መስልኝ ነበር። ጊዜውን እረስሁት እንጂ ካራት ውይም አምስት አመት በፊት እንደዚሁ እያደረጉ ጉቦ በሉት ሌብነት መንግስትን እንደሚዘርፉ አውቅ ነበር። ሌላው ቀርቶ በቪዲዮ እንደዚሁ የታክስ ገንዘብ ሲወስድ የተገኝ አንድ አቀላጣፊ ሶስት ቀን ታስሮ ይጣራ ተብሎ እንደተፈታ ስምቻለሁ። እንዚህ ሰዎች ሌላ “አገር” አላቸው። አሁንም እንኩዋ አያርፉም። ሰንቱ ሰው በታክስ ምክንያት መክፈል ስለማይችል ድርጅቱን ዘግቱዋል። አንዳንዱም ድርጅቱን ዘግቶ የፑል መጫወቻ ከፍቷል፣ ይህም የፑል ቤት ሰው ስራ ሲፈታ ለመዝናኛ የሚሄድበት ሳይሆን፣ ሰው ሥራ ስለሌለው የሚሄድበት ቦታ ሁኗል። ታዲያ ምን ያረጋል ሁሉም ነገር የዶክተር አብይ “እዳ” መሆን የለበትም አልኩና ወደጉዋደኛ አፍጥጨ እያየሁ ” ባህርዳር አትሂድ” አልኩት
“ለምን” አለኝ
“ይህ ነገር ማብቃት አለበት” አልኩት
“እንዴት” አለኝ
ነገ ባህርዳር ከምትሄድ በየሆቴሉ ዙርና የሆቴል ባለቤቶችን አናግር። ይህ ችግር ያንተ ብቻ አይደለም፣ የሁሉም ነው። በመሆኑም ባንድ በዚህ ጥያቄ ከተደራጃችሁ የራሳችሁ ጠበቃና አካውንታት መቀጠር ትችላላችሁ። የታካስ ጥያቄን በጋራ ትወጡት አላችሁ። ለመንግስትም የሚገባው ታክስ ወደመንግስት ይገባል። እነዚህ ወንቤዴውችንም በጋር ትታገላላችሁ። ይህ ብቻ አይደለም “መደራጀታችሁ ብዙ ጥቅም አለው። ምርጫም ባንድ ላይ በመቆም ለሚያማችሁ ጥያቄ ለሚጎረብጣችሁ አስተዳደር ባንድ ላይ ለማበር ያገለግላችሗል “አልኩና ጨረስኩ
ጉዋደኛየ ግን በበነገታው ወደባህርዳር ሄደ እኔም የዶክተር አብይ “እዳ” አልኩ።
የታክስ ጥያቄ የዶክተር አብይ “እዳ”፣ የምርጫ ነገርም ሲመጣ የዶክተር አብይ “እዳ” ሁኗል። ጉዋደኛየነም ይህን አደረክ ብየ ልወቅሰው አይገባኝም። እሱ ነጋዴ፣ ሆቴል ነው ሥራው ። ሌላ የማደረጀትን ተጨማሪ ሥራ መሥራት አለብህ ብየ ላስገድደው አልችልም። ቢያረገው ጥሩ ነበር። ይህን የማደራጀት ሥራ ሃላፊነት መሸከም ያለባቸው፤ ዶክተር አብይ ሰብስቦ ያናገራቸው፣ ከሰማንያ በላይ የሚሆኑት ድርጅቶች መሆን ይኖርብታል።
በታክስ ጥያቄና በሌሎችም ህብረሰቡ በሚያመው ማደራጀት ካአሁኑ ቢጀምሩት ከአንድ አመት በማይበልጥ ጊዜ ማደራጀትና ለምርጫ ማዘጋጀት ይቻላላ ብየ አምናለሁ። ይህ ብቻ አይደለም ዶክተር አብይ ሶስትም፣ አምስትም በሚያመሳስላችሁ የጋር በሆነ ጥያቄ ላይ ብትተሳሰቡ ብለው ለተቃዋሚ ድርጅቶች ሲመክሩ፤ መሰባሰቢያው አጀንዳ ኢትዮጵያዊነት ነው ብየ ወስጀዋለሁ።
የዶክተር አብይ “እዳ” የኔም እዳ አድርጌ ብወስደውና ምክር ቢጥየቁኝ የምላቸው “የርስዎ ድርጅቶች፣ ሶስቱን፤ ኦዴፓ፣ አዴፓ፣ የደቡብ ህብረትንና አጋር ድርጅቶን በማሰባሰብ አንድ ብሄራዊ ድርጅት ቢመሰርቱ፤ አሁን ከለንበት ማጥ ለመውጣት የመጀመሪው እርምጃ ይሆናል። ይህ ከሆነ ኢትዮጵያን የሚመራት በአብላጫ ድምፅ የተመረጠ እንጂ በመንደር ወይም በክልል ታጥሮ በተመሰረተ ድርጅት አይሆንም።
ከዚህ ላይ የክልል መንግስቶች ምን ይሁኑ የሚል ጥያቄ ማንሳት ይቻላሉ።” ለዚህም ቢሆን አንድ እንደአማራጭ በበኩሌ ልወርውርና ሌላውን ወይም የኔን አማራጭም ይሁን ሌላ ለማየት የሚችል ሰሞኑን ለተቇቇመው የማንነተና የወሰን ኮሚሽን ልተውውና የኔን ይህውና።
እንደኔ አሁን ላለው ሶስት ሚሊየን የሚደርስ ህዝብ መፈናቀልና እስካአሁንም ለነበረው ፍትህ ማጣት ምክንያቱ፤ አንድና አንድ ብቻ ነው። ይህም የህወሃት የ27 አመት አገዛዝ የነበረው በብሔር የተደራጀ ክልል ውጤት ነው። ይህ ችግር የመንጨው የብሄርና የብሄረሰብ ክልል ነው። ስለሆነም መፍትሄው ሌላ የብሄረሰብና ብሄር ክልላዊ መንግስት በፌደራል ይሁን በፈለገው አይነት አደረጃጀት መፍትሄ ሊሆን አይችልም። መፍትሄው የዜግነትን ጥያቄ መመለስ ነው። የዜግነትን ጥያቄ ለመመለስ ክልል መልስ አይሆንም
የክልል ችግር የሚመነጨው ክልል መሆኑ ሳይሆን የብሄረሰብ መብት የራስን እድል በራስ በመወሰን ስም ከመንግስት ጥያቄ ጋር መዳበሉ ነው። — የብሄር መብት ሲባል የብሄር መንግስት እንዳልሆነ በማያሻማ መንገድ መቀመጥ አለበት። የማንነትን መብት በክልል መክለል እራሱ መብትን መገደብ ነው። የአማራ ወይም ኦሮሞ ትግራይ ቤኒሻንጉል— ክልል ስንል በውስጣቸው ያሉትን አናሳ ብሄረስቦችስ? በሃረር ድግሞ የተገላቢጦሽ ነው። በክልላቸው የማይኖሩ እንደአማራ ብሄር ያሉ ፣ በቁጥር ከትግራይ ህዝብ የሚመጣጠን በክልሉ ሳለማይኖር ሲፈናቀል መኖር አለባቸው?
ለዚህ መፍትሔ ክልልን በዞን መተካት አንድ አማራጭ ነው
ለምሳሌ አሁን ባለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ፈንታ ከየዙኑ ተወካዮችን በመላክ አንድ የሴነት ፌደራላዊ ምክር ቤት መመስረት። በክልል ፈንታ ከ ዞኖች ተውካዮችን ወደሴነት መላክ አሁን ላለው ችግር መፍትሄ ይሆናል ብዮ አስባለሁ። የወልቃይት ይሁን የራያን ጥያቄ እራሳቸውን ችለው ዞን በመሆን ልክ እምደሌላው ዞን በሴነቱ ስለሚወኩሉ አሁን ካለው የኔ የኔ ክሚል ችግር ያወጣናል። ባጠቃላይ የትግራይ፣ ያአማራ፣የኦርሞ — ክልልም የሚባል ነገር ስለማይኖር ጥሩ አማርጭ ነው እልላሁ። የራሴንም የዶክተር አብይንም “እዳ” በሁለቱ ጥያቄዎች ላይ ጨረስኩ።
ስላም ሁኑ
ሀቢቡ ታከለ
thabibu@gmail.com
___
ማስታወሻ:በዚህ ጽሁፍ ላይ የተንጸባረቁ ሳሃቦች የጸሃፊውን/የጸሃፊዋን እንጂ የድረገጹን አቋም አያንጸባርቁም።
ነጻ አስተያየት ወይንም ሃሳብ በዚህ ድረ ገጽ ለማውጣት ጽሁፍዎትን በ info@borkena.com ይላኩልን።