spot_img
Saturday, September 30, 2023
Homeነፃ አስተያየትየኢትዮጵያና የአካባቢው ፀጥታ (Security) በሽግግር ወቅት (ከዳዊት ወልደጊዮርጊስ)

የኢትዮጵያና የአካባቢው ፀጥታ (Security) በሽግግር ወቅት (ከዳዊት ወልደጊዮርጊስ)

advertisement

ለቪዥን ኢትዮጵያ 7ኛ ኮንፈረንስ
አዲስ አበባ ታህሣስ 18-19 የቀረበ የምርምር ወረቀት
ከዳዊት ወልደጊዮርጊስ

መግቢያ

ከሰላሳ ዓመት በኋላ ይህችን የተወለድኩባት፣ እትብቴ የተቀበረባት፣ የተማርኩባት፣ በውትድርና ሙያም፣ በሲቪልም በተለያዩ ከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ የታገልኩላት፣ የቆሰልኩላት፣ ወድጄ ሳይሆን ተገድጄ ትቻት ሄጄ የነበረችውን ክቡር አፈር ለመርገጥ ላበቃኝ አምላክና ይህንንም ሁኔታ ላመቻቹልኝ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ምስጋናዬ ታላቅ ነው፡፡ በቀሪ ዕድሜዬ ይህንን እመሰክራለሁ ብዬ አልገመትኩም ነበር፡፡ የዶክተር አቢይን አመራርና ራዕይ እንድንደግፍ ጥሪ ካስተላለፉት የመጀመሪያዎቹ ነኝ፡፡ Let us Rally around Prime Ministir Abiy በሚል ፅሑፍ ድጋፌን፣ አድናቆቴን ቀደም ብዬ ገልጫለሁ፡፡ አሁንም አቋሜ ይህ ነው፡፡

በሀገራችን ውስጥ ዘለቄታ ያለው ሰላምና ዕድገት እንዲኖር ይህ ሥርአት መለወጥ እንዳለበት አጠያያቂ ሊሆን አይገባም፡፡ ይህም ማለት ኢህአዲግና ይህ ሕገ መንግሥት ተለውጦ ወደ አዲስ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ካልተሸጋገርን ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም አይኖርም ከሚለው ፅንሰ ሃሳብ ተነስቼ ነው ይህንን ወረቀት ያዘጋጀሁት፡፡

ዛሬ የምንጣላው ከራሳችን ጋራ እንጂ ከውጪ ጠላት ጋር አይደለም፡፡ ስለዚህም የኢትዮጵያ ህልውና በተለየ መልኩ ልዩ የሆነ ፈተና ውስጥ ገብቷል፡፡

ታሪካችን ባህላችን ማንነታችን የማይደግፈው ከጠባብ እውቀት የመነጨ አስተሳሰብ አሁን በሀያ እንደኛው ክፍለ ዘመን ለኢትዮጵያም ለአፍሪካም ለመላው ዓለምም የሚያሳየው ኋላ ቀርነትን ብቻ ስለሆነ ይህች የታሪክ መሰረት ያላት ኢትዮጵያ ጥሩ አመራር ካላት በአጭር ጊዜ ውስጥ ልታጠፋው ትችላለች::እውነት ጠፍታ ከርማለች፡፡ የሚያድነን እውነት ነው::

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ይሄንን ይጫኑ

___
ማስታወሻ:በዚህ ጽሁፍ ላይ የተንጸባረቁ ሳሃቦች የጸሃፊውን/የጸሃፊዋን እንጂ የድረገጹን አቋም አያንጸባርቁም።
ነጻ አስተያየት ወይንም ሃሳብ በዚህ ድረ ገጽ ለማውጣት ጽሁፍዎትን በ info@borkena.com ይላኩልን።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,705FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here