“የአዲስ አበባና የአፋን ኦሮሞ ጉዳይም እየተሠራበት ያለ ጉዳይ ነው…” (Interestingly Unusual Frankness)
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
የካቲት 13 ቀን 2011 ዓ.ም.
በአጠቃላይ የኢትዮጵያም ሆነ በተለይ የአዲስ አበባ ዕጣ ፋንታ በተሳለጠ ሁኔታ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እየተጓዘ ይመስላል፡፡ 99 በመቶ የሚሆነው ዜጋ ጥልቅ ዕንቅልፍ ውስጥ ሆኖ ዕንቅልፉን ቢለሸልሽለም ታሪክ ግን ጉዞውን አያቋርጥምና መረረንም ጣፈጠንም የሀገራችን መፃዒ ዕድል የሚወሰንበት ወሳኝ የጡዘቶች ጫፍ ላይ ደርሰናል፡፡ መርዶም ይሁን የምሥራች በራችንን ሊያንኳኳ ተቃርቧል፡፡ ሕወሓትና ጌቶቹ የቀበሯቸው ቦምቦች ሁሉ ሊፈነዱና በመጨረሻው አርማጌዶ ውሉ ሊለይ ጊዜው ደርሷል፡፡
ይህች ወቅት ለኢትዮጵያውያን ልክ እንደሰሙነ ህማማት ብትቆጠር አይበዛባትም፡፡ ጥቂት የማንባል ዜጎች በቀንም ሆነ በሌሊት የኅሊና ዕረፍትና የአልጋ ላይ ዕንቅልፍ አጥተናል – በ“ምን እንሆን ይሆን?” መሳቀቅ፡፡ ዘጠኝ ሞት ቢመጣ አንዱ መግባቱ ለማይቀረው ስለኛ ብቻ ሣይሆን ስለመጪው ትውልድ በመጨነቅ የባዘነ ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን፡፡ በዚህም ምክንያት ሌሊቱን አንዳንድ የድረ ገፅ የመረጃ ምንጮችን ሳገላብጥ አድሬ አሁን ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ አይደለም፡፡ ጥቂት ሃሳቦችን ልሰንዝር ብዕሬን ያነሳሁትም ለዚህ ነው፡፡
አቻምየለህ ታምሩ በአጭሩ ያስቀመጣቸው ዕይታዎቹ ስበውኛል – ከሣተናው ድረ-ገፅ እንዳነበብኩት፡፡ (https://www.satenaw.com/amharic/archives/63906)
ሕወሓትና ኦህዴድ አያ ዲያብሎስ በአንድ ምጣድ ያሰፋቸው በተለመደው አገላለጽ የአንድ ሣንቲም ሁለት ገጽታዎችና በጠባይም በምግባርም አንድ አካል አንድ አምሳል መሆናቸውን በወቅታዊ ምሣሌ አስደግፎ አቻምየለህ በዛሬ ሌሊት ቅልብጭ ያለች አጭር መጣጥፉ አስረድቷል፡፡
ወደ ቀጣዩ አንቀጽ ከመሸጋገራችን በፊት ከዚህ በታች ያስቀመጥኳትን ብሂል አጢኑልኝም፡፡
እዚያ ማዶ ሆኖ ክፉ ሰው ተጣራ፤
እዚህ ማዶ ሁኖ ክፉ ሰው ወይ አለው፤
ጎበዝ ተጠራጠር ይህ ነገር ለኛ ነው፡፡
ማሌሊት ማነው ሕወሓት ሰሞኑን መግለጫ አውጥቷል፡፡ መጋቢት 17 ቀን 82 ዓ.ም ሰሜን ሸዋ ደራ ከተማ ላይ ከምርኮኛ ወታደሮች ጠፍጥፎ የሠራው ልጁ ኦዴፓም እንደዚሁ፡፡ የሁለቱም መግለጫዎች በፉከራና በጦርነት ዐዋጅ የታጨቁ ናቸው፡፡ ሁለቱም ድርጅቶች ኢትዮጵያን በሸጥና በጎጥ በታትነው ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎችን ለማስደሰትና በርዕሰ አድባራት ሊቀ ሣጥናኤል አማካይነት ወደር ለሌለው ጀግንነት እንዲሰጥ የተዘጋጀላቸውን የታላቅ ጀብዱ ሊሻን ለመቀበል የሚራወጡ ናቸው፡፡ ሕወሓት ለይቶለት የኢትዮጵያን ስም መጥራቱን ቢጠየፍም ኦዴፓ ግን በአዲስ ሥልት በሚያቀነቅነው “እምዬ ኢትዮጵያ” በሚለው ዘፈኑ ብዙዎችን እያነሆለለ ውስጥ ለውስጥና አሁን አሁን ደግሞ በግልጽ ሀገራችንን የማፈራረሱን ሥራ በገሃድ እያከናወነ ነው፡፡
በርዕሴ ላይ ያስቀመጥኩት የአማርኛው ክፍል በግልጽ የሚናገረው የሚከተሉትን የኦህዴድ ተግባራት ነው፡-
1. (በነሱው አጠራር) ፊንፊኔን ከአማራ ለማጽዳት የጀመርነውን ፈጣን እንቅስቃሴ በስፋትና በጥልቀት እንቀጥላለን፡፡ ከዚህም አንጻር –
1.1 በሽዎች የሚቆጠሩ አማሮችን ከየመሥሪያ ቤቱ እየመነጠርን እንዳንሳፈፍናቸውና በኛ ጎሣ አባላት እንደተካናቸው ሁሉ አሁንና ወደፊትም ይህን ተግባር በሚያስደምም ፍጥነት እንቀጥላለን፡፡ የወያኔን የ27 ዓመት ድካምና ልፋት የሚያስንቅም ድል በቅርብ እናስመዘግባለን፡፡ ስለዚህ በግራም በቀኝም ያላችሁን ደጋፊዎች በኛ ኩሩ፡፡
1.2 በፊንፊኔ ዳርቻዎች የጀመርነውን የአማራና የሌሎች ጎሣዎችን መኖሪያ ቤቶች በግሬደር የማፈራረሱን ተግባር ቀጥለን ነገና ነገ ወዲያ መሀል ከተማ የሚገኙትን የኦሮሞ ያልሆኑ ቤቶችና ሕንጻዎችን እንገነዳድሳለን፡፡ (ልብ አድርጉ በነዚህ ሁለትና ሦስት ቀናት ብቻ በለገጣፎ አካባቢ ወደ አራት ሽህ የሚጠጉ መኖሪያ ቤቶች እንደፈራረሱ በሣተናው አንብበናል፡፡ አስቡት – አራት ሽህ ቤት እያንዳንዱን በአምስት የቤተሰብ አባላት ብታባዙት 20 ሽህ ሰው በአንድ አዳር ጎዳና ወጣ፤ ሀብት ንብረቱም በግሬደር ተጨፈላለቀ፡፡ አራት ሽህ ቤት ማለት በከተሞች ብያኔ የሁለት ከተማ ሕዝብ ማለት እንደሆነም መረዳት ተገቢ ነው፡፡ የኦዴፓ ጀግንነትና ኢትዮጵያዊነት እንግዲህ በዚህም ይገለጻል፡፡ ዘርን ካጸዱ አይቀር እንዲህ ነው፡፡ ጎበዞች!! ያበጠው ይፈንዳ እንጂ ኧረ በርትታችሁ ቀጥሉ፡፡
1.3 ባንኮችን፣ አየር መንገድን፣ የገንዘብ ተቋማትን ወዘተ. በመቆጣጠር ለኦሮሞ ባለሀብቶች የምናደርገውን ከወያ የተማርነውን አድልዖ በስፋት እንቀጥላለን፡፡ (ይህም የጠ/ሚኒስትሩን አንደበታዊ አቀራረብና በተግባር ግን ምን እየተከናወነ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ በሀገራችን ውስጥ እነሼክስፒርንና ዳንቴን የሚያስከነዱ ጸሐፌ ተውኔቶችን መፈልፈል የሚጠቁም ነው፡፡)
1.4 ከዚህም በተጓዳኝ ልክ እንደወያኔዎች ሁሉ የአዲስ አበባን የሕዝብ አሰፋፈር ለመለወጥ እስካሁን ብቻ በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከገጠሮች እያመጣን የአዲስ አበባ ኗሪነት መታወቂያ አድለናል፡፡ ገና ደግሞ እንቀጥላለን፡፡ ( በአንድ በኩል ሌሎችን መንቀል – በሌላ በኩል የራስ የሚሉትን ዜጋ ከጠቅላይ ግዛ እያመጡ መትከል፡፡ ይቺ ናት ወያኔያዊ ጨዋታ ማለት፡፡ ወያኔም በወልቃይት፣ በራያና በአፋር እንዲሁም በአዲስ አበባ ያደረገው ይሄንኑ ነው፡፡ ጎረምሳ ዝንጀሮ ያባቱን ኮቴ ከኋላው እየተራመደ ለክቶ እኩል ሲሆንለት ያባቱን ሚስት እናቱን ቀምቶ እንደሚያገባ ሁሉ ኦህዴድም እያደረገ ያለው ልክ እንደዚሁ ነው፡፡ በቡዳ ቤት ሰላቢ ገባና ትያትሩ ጦፈልህ፡፡ ዝም ብለህ መጨረሻውን ብቻ ማየት ነው፡፡)
2. ይሄ ፌዴራላዊ ሥርዓት እንደፌዴራል ሥርዓት ተቆጥሮ ሞቶ ኦህዴድም አቅም አገኘሁ ብሎ ልክ እንደወያኔ “ሥርዓቱ የሚለወጠው በመቃብሬ ላይ ነው፤ በርሱ መጣችሁ ማለት ባይኔ መጣችሁ ማለት ነው” እያለን ነው፡፡ በወረት ፍቅር ከናወዘ ጎረምሣ ዝንጀሮ ከዚህ በላይ አይጠበቅም፡፡
በጥቅሉ ይህ ወቅት ብዙ ነገሮችን አጉልቶ እያሳየን ነው፡፡የፖለቲካ አሰላለፎችም እንዲሁ ግልጽ ሆነዋል፡፡ ማን የማን ጥገኛ እንደሆነ ተለይቷል፡፡ ማን እፍኝ ለማትሞላ ምሥር እንዳደረና ወንድሙን ይሥሃቅን (ሀገርን) እንደሸጠ፣ ማን ለፍርፋሪ ሥልጣን እንደተንበረከከና ወገኑን እንደካደ፣ ሀገራዊ ራዕዩንም አሽቀንጥሮ እንደጣለ፣ማን በአስመሳይነት ካባ ተጀቡኖ ቀን ቀን “ኢትዮጵያ፣ ኢትየጵያ” እያለ ማታ ማታ ከዘረኞችና ከከፋፋዮች ጋር ባንኮኒ ላይ ዊስኪውን እንደሚጨልጥ እየተረዳን ነው፡፡
አሰላለፋችን በሚዲያውም እየለየለት ነው፡፡ በዚህን ወቅት ስለኢትዮጵያ መዘመርን እንደወንጀል የሚቆጥሩ የአንድነት ኃይል ነን ባዮችን እያየን ነው፡፡ እንደጓድ ቆምባጫምባው መሆን አምሮኝ ወይም ፈልጌ አይደለም፡፡ ምሣሌ ለመስጠት ያህል ነው፡፡ አዎ፣ ለምሣሌ ይህችን ጽሑፍ በሚዲያው የሚያወጣት ኢትዮጵያዊ ነው ወይምና ቢያንስ የሃሳብን በነፃነት መንሸራሸር የሚደግፍ ዴሞክራት ነው፡፡ የሚያፍናት ግን ወያኔና ወያኔያዊ ባሕርይ የሚያሰቃየው ነው ወይም የሃሳብን በነፃነት መንሸራሽር የሚጠላ አፋኝና አምባገነን ነው፡፡ ከዚህ የሚያልፍ ነገር የለም፡፡ ስለዚህም አሰላለፋችን ከዚህም ይነሳል፤ ከዚህም ይፈረዳል፡፡ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ሀሰት ከተነገረ በተፈለገው ሁሉ እምላለሁ፡፡ ይህን ጽሑፍ የማያስተናግዱ እደግመዋለሁ ኢትዮጵያውያን ነን ማለት ሊያሳፍራቸው ይገባል፡፡ ለገጣፎ ላይ 4000 ቤት፣ ቤተ መንግሥት አጠገብ ብዙ ቤት፣ በፉሪና በላፍቶ እጅግ ብዙ ቤት እየፈረሰ፣ ፖለቲካው ከቀን ወደ ቀን እየተግማማና ወደ አንድ ወገን ያጋደለችው መርከብ ልትገለበጥ አንድ ሐሙስ ብቻ በቀረበት ሁኔታ ዝም ጭጭ የሚል የፖለቲካ ድርጅትና ሚዲያ ከአድር ባይ አዘጥዛጭ ተለይቶ አይታይም፡፡ በአፍ የሚሉትና በብቅል ቀን የሚወሻክቱት እየተደበላለቀባቸው የሚቸገሩ ወገኖች እንዳሉም እየተረዳን ነው – በዘር ጥላቻ የታወሩ ጭምር፡፡ እነዚህን አስተኔ የሌሊት ወፎች ታሪክ ዋጋቸውን እንዲከፍላቸው ከመጸለይ በስተቀር የምንለው የለም፡፡ ወይም ከወዲሁ ልብ ይስጣቸው፡፡ የሚገርም የነገሮች አካሄድ ውስጥ እንገኛለን፡፡ የዓላማ አንድነት መገለጫው ብዙ መሆኑንም በእግረ መንገድ እያስተዋልን ነው፡፡
ለማንኛውም ያቺ መከረኛ ሴተኛ አዳሪ አለች የተባለውን መጥቀስ ፈልጌ አሁን ጠፋኝና ተውኩት፡፡ ዘንድሮ ይለያል ጉዱ፡፡ አዎ፣ ኢትዮጵያን አጭበርባሪ እስከወዲያኛው አጭበርብሯት አያውቅም፡፡ የመቶ ሚሊዮን ሕዝብ እረኛ በጎጠኞች የሚሸነፍበት አንድም አመክንዮም የለም፡፡
ግን እባካችሁን ስንጣላ እንደምንታረቅ ሆነን እንጣላ፡፡ ስንነጋገር እንደምንግባባ ሆነን እንነጋር፡፡ መቅኒ ውስጥ ገብቶ ከትውልድ ወደ ትልድ እየተላለፈ የሚያመረቅዝ መጥፎ ነገር ከሠራን እኛን ብቻ ሣይሆን ልጆቻችንንም እንጎዳለን፡፡ ወያኔ በተለይ በአማራ ላይ የሠራው ግፍና በደል ከዚህ አንጻር የሚታይ ነው፡፡ አማራንና ወያኔን ለማስታረቅ ልነሳ የሚል ምድራዊ ኃይል የሚፈራው እንግዲህ በአማራ በደረሰው ተዘርዝሮ የማያልቅ የፈሪ ዱላ ዓይነት ወያኔዊ ሰቆቃ ሳቢያ ነውና ከአሁን በኋላ ጉልበተኝነት የሚሰማው ቡድን ጉልበቱን በጠበልም ይሁን በሥነ አእምሮ ህክምና ሰከን እያደረገ በቅጡ እንዲበድል – መበደልም ካለበትና ካማረው – ራሱን ያርቅ፤ ያስተካክል፡፡
በተረፈ ዐውድማው በየአቅጣጫው እየተለቀለቀ ነው፡፡ በቅርቡ ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሚሆን በጉጉት ይጠበቃል፡፡ በሬዎቹም ወደየዐውድማቸው በመሠማራት ላይ ናቸው፡፡ በኮረም በኩል ለምሣሌ የተሰማ የጦርነት ጥንስስ ዜና አለ (https://www.satenaw.com/amharic/archives/63877)፡፡ ሁሉም ይሰናዳ፡፡ መቀመጥ መቆመጥ ነው – ምን ይፈይዳል? እህል መጨረስ ነው፡፡ ሰላም ምን ይሠራል? አዎ፣ ጎራዎችም በፀጥታ ብዛት ደንቁረዋል፡፡ የባሩድ ሽታም ናፍቋቸዋል፡፡ ልክ ነው፣ ብንራብ ብንጠማም መለከቱ ይነፋና ወንድና ሴቱ ይለይ፡፡ ከሁልጊዜ ፈስ ደግሞ የአንድ ቀን ምንትስ እንደሚሻል ግልጥ ነው፡፡ ሁልህም ታጠቅ፤ ዝመት፤ ባባቶችህ ወኔም እርስ በርስ ተፋለምና ሀገርህን የጃርት መፈንጫ አድርጋት፡፡ ያ ነው ጀግንነት ማለት! ቀን ሲሰጥህ በወንድሞችህ ጫንቃ ላይ ቆመህ ነው ማስጨነቅ፡፡ አለዚያ ወንድነትህ እንዴት ይታወቃል? ምኑንስ ተወልደከው! ለማንኛውም ታዲያ ርብን ጠብቃት፤ መሀል ሸዋንም አትርሳት፡፡ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ወሎ፣ ሸዋ፣ ባሌ … ክምርህን ከሚገነብሩ ወጣት ዝንጀሮዎች ሰብልህን ጠብቅ፡፡
መረሳት የሌለበት ግን ወያኔ ለአማራ ብላ የረጨቻቸው መርዞች፣ ያቆመቻቸው አፓርታይዳዊ ምሠሶዎች ሁሉ ለተጋሩም የሚተርፉ መሆናቸው ነው፡፡ ለዚህ እኮ ነው “ለሰው ጉድጓድ ስትቆፍር አታርቅ” የሚባለው፡፡ የጥቃቅን ፌዴራል ተብዬ መንግሥታትን ሀብትና ገንዘበስ ማን ነበር የሚዘባነንበት? የዘሩትን ማጨድ ያለ ነው፡፡ አሁን መሀል ሜዳ ቆሞ መጨነቅ ዋጋ የለውም – መጋፈጥ እንጂ፡፡ መጥኖ መደቆስ ዱሮ ነበር፡፡ ቻው ቻው ወያኔ፡፡ ቤት ለእምቦሳ ኦህዴድ!…
አለቃ ገ/ሃናም “ማዘንጊያ፣ እዚያም ቤት እሳት አለ” ያሉትም ለዚህ ነው፡፡ አሁን በውነቱ ከትግሬና ከአማራ ብዙ የሚያጣው ማን ነው? ባለፉት 27 ዓመታት መሬቱን፣ ወርቁን፣ ሕንፃውን፣ ገንዘቡን፣ ምኑን ምናምኑን ሱቅ እንደገባ ሕጻን በስግብግብነት ሁሉንም ያጋበሰው አማራ ነው ወያኔ? እናስ ማን ይሆን ይበልጥ የሚጎዳው? “ባመጣኸው ዳኛ ትሆን እሥረኛ” ማለትም አሁን ነው፡፡ ልናይ አይደል?
(ma74085@gmail.com)
__
ማስታወሻ:በዚህ ጽሁፍ ላይ የተንጸባረቁ ሳሃቦች የጸሃፊውን/የጸሃፊዋን እንጂ የድረገጹን አቋም አያንጸባርቁም። ነጻ አስተያየት ወይንም ሃሳብ በዚህ ድረ ገጽ ለማውጣት ጽሁፍዎትን በ info@borkena.com ይላኩልን።