spot_img
Monday, December 4, 2023
Homeነፃ አስተያየትለተከበሩት አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ የፊደራል ጠቅላይ ዐቃቢህግ (የኢትዮጵያ ፖለቲካ እሥረኞች አንድነት ኮሚቴ...

ለተከበሩት አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ የፊደራል ጠቅላይ ዐቃቢህግ (የኢትዮጵያ ፖለቲካ እሥረኞች አንድነት ኮሚቴ በካናዳ)

advertisement

የካቲት 14፣ 2011 ( ፈበርዋሪ 21፣ 2019)
(በፒ ዲ ኤፍ ለማንበብ ይሄንን ይጫኑ)

ለተከበሩት አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ
የፊደራል ጠቅላይ ቃቢህግ
አዲስ አባባ

የተከበሩት አቶ ብርሀኑ

ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ በህዳር 3፣ 2011 የአባራሽ በርታንና የሌሎችንም መዳረሻቸው ያልታወቀ የፖለቲካ አስረኞች ሁኔታ በጉጉት ለሚጠብቁት ወዳጅና ዘመዶቻቸው እንዲሆም ለመብት ተሟጋቹ ማህብረሰብ እንደያሰታውቁን በመጠየቅ ደብዳቤ መጻፋችንን ተከትሎ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የአማርኛው ፕሮግራም እርሰወን በኖቨምበር 15፣ 2018 እንዳነጋገረ ይታወሳል። በዚያም ቃለ ምልልስ ውስጥ የወይዘሮ አበራሽ በርታን ፣ለማ ሃይሌ፣, ሙሉ አምባውን፣ ፀጋየ ገብረመድህንን፣ ይስሀቅ ድበረጽዩንን፣ በለጠ አምሃ, ሐጎስ በዛብህ , ስጦታው ሁሴን, ተክላይ ገ/ሥላሴ,, አባይነህ ሽፈራው , አበበ ዓይነኩሉ ፣አዛናው ደምል , ደምሴ ተስፋዬ ወዘተ ጉዳይ እስከቃለምልልሱ እለት እንደማያውቁ ገልጸው ሁኔታውን እንደሚከታተሉ እጅግ ትልቅ ተስፋ ሰጭ የሆነ ምላሽ እንደሰጡ ይታወሳል።https://www.facebook.com/ethiopianbrief.ethio/videos/1375079972626519/UzpfSTEwMDAxMzgzMjI4Mjc3Mzo1NDQ0NDQzNTkzNTk5Njk/

ያንን ቃለምልልስ ተከትሎም የወይዘሮ አበራሽ በርታ፣ አቶ ሙሉ አምባውና የሌሎችም መዳረሻቸው አልታወቀው የፖለቲካ እስረኖች ወዳጅኛ ዘመዶች የእስረኞቹን ሁኔታ በተመለከተ ምን አዲስ ጉዳይ እንዳለ ለማወቅ እጅግ በጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ።

ከነዚህ በጉጉት ከሚጠብቁ ኢትዩጵያውያን ውስጥ ብዙወች እኛን በተደጋጋሚ በስልክ በኢሜል አንዲሁም በግንባር በማግኘት ምን አዲስ ነገር እንዳለ በተደጋጋሚ ይጠይቁናል። ከ20 አመት በላይ መዳረሻቸውን ያላወቋቸውን የወዳጅ ዘመዶቻቸውን መዳረሻ ለመወቅ የቤተሰቦቻቸውንም ሆነ የ እኛን ድርጅት ጉጉት ክቡርነትወም ሆነ መንግስት በትክክል እንደሚገነዘቡ እርግጠኞች ነን።

የዛሬው ደብዳቤያችን ዋና አላማም ፣ በገቡት ቃል መሰረት የተካሄደ ወይንም የተጀመረ ማጣራት ካላ እንዲገልጡልን በአክብሮት ለመጠየቅ ነው። የተጀመረ ጉዳይ ከሌለም ባስቸኳይ እንዲጀመር ለመማፐን ነው። እርስወም እንደሚያውቁት የዘገየ ፍትህ እንደተከለከለ ፍትህ ሊመሰል ይችላልን አሁንም ለዚህ ጉዳይ ልዩ አጽንኦት በመስጠት እልባት እንዲያገኝ እንደሚያደርጉ ባለሙሉ ተስፈ ነን።

በእኛ በኩል ምርመራውን ሊያግዝ በሚችል መንገድ ሁኑ ለመተባባር ምን ጊዜም ዝግጁ መሆናችንን ስንገልጽ በታላቅ ትህትና ነው።

ከታላቅ አክብሮት ጋር

አክሊሉ ወንድአፈረው
የ ኢትዮጵያ ፖለቲካ አስረኞች አንድነት ኮሚቴ ካናዳ
ሊቀመንበር
ግልባጭ፣ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት፣ ለፕሬዚደንት ጽህፈት ቤት
___
Solidarity Committee for Ethiopian Political Prisoners (SOCEPP-Canada)
የኢትዮጵያ ፖለቲካ እሥረኞች አንድነት ኮሚቴ በካናዳ (ኢፖእአኮ-ካናዳ)
Email: socepp.can@humanrightsethiopia.com and socepp.can@sympatico.ca
Web: www.humanrightsethiopia.com

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here