spot_img
Wednesday, May 29, 2024
Homeነፃ አስተያየትአስቸኳይ ደብዳቤ ፣ ይድረስ ለአቢይ አህመድ፣ (ከደብሩ ነጋሽ -ሃኪም)

አስቸኳይ ደብዳቤ ፣ ይድረስ ለአቢይ አህመድ፣ (ከደብሩ ነጋሽ -ሃኪም)

የኦሮሞው ሹማምንቶችህ ህጋዊ ቤቶች የማፍረስ ዘመቻ፣ በኢትዮጵያውያን ላይ የጦርነት አዋጅ ነው።

ከደብሩ ነጋሽ -ሃኪም
የካቲት 17 ቀን 2011 ዓ.ም.

ለዘመናት ሲያሰቃይ የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ወራሪ ወያኔን በአመጽ አፍረክርኮ፣ አንተንና መሰሎችህን ስልጣን ሲያስጨብጥ፣ ፈንጥዟል። ክስተቱ የመለኮት ስራም ነው ያሉ የዋሆች ነበሩ። በተለይ አንተንና ለማ መገርሳን፣ ሲያወድሱ የነበሩት ጥቂት አልነበሩም። ባደባባይ ትናገሩ የነበረው፣ ህዝብ ሊሰማ የሚፈልገውን ስለነበር፣ ያልታጠቀን ህዝብ ደም፣ በግፍ ካፈሰስው ኦነግ፣ የምትለዩ መስሎታል። በህዝብ አመጽ ልስልጣን በቅተህ ፣ በግፍ የታሰሩን በማስፍትታትህ፣ ህዝብ ተደሰተ። ግን እመነት የጣለብህ፣ በከንቱ እንደሆነ ፣ ያለፉት ሁለት ሶስት ወራት ክስተቶች ያመለክታሉ። ለነገሩ፣ የግንዛቤ እጥረት ካልሆነ በስተቀር ፣ የስራዐት እንጂ የሹማምንት መቀያየር እርባና እንደሌለው በተረዳ ነበር።

ስልጣን ከያዝክ ጀምሮ ፣ ያንተም ሆነ የባለሟል ኦርሞዎች ማንነት ፣ ይፋ ሆኗል። የሰሞኑ የመግስትህ ድርጊት ግን ፣ በእትዮፕያውያን ላይ ጦርነት እንዳወጅክ ግልጽ ነው። ‘’ጅብ እስኪነክስ ያነከስ’ ‘እንዲሉ፣ ያንተና የለማ፣ አማላይ ቃላት ፍሬከርስኪነት ግልጽ ነው። ድርጊታችሁ፣ ከጅብ ትክክለኛ ባህርይ ፣ ያመሳስላችኋል። ላብነት ከዚህ የሚከተሉትን እንዘርዘር።

‘አደባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ’

ትላንት በወለጋ አያሌ ባንኮች፣ ኦነግ በተሰኘው የኦሮሞ ቡድን ሲዘረፉ ፣ ንጹሃን ሲፈጁ፣ መንግስት እያንደላቀቀ ሆተል የሚያኖረው አዛዣቸውም ሆነ ፣ ከምንዝሮቹ ፣ አንድ ሰው ተይዞ ለፍርድ አልቀረበም ። በርካታ ሚሊየን የህዝብ ገንዘብ ተዘርፎ ሳንቲም አልተመለሰም። አንድ ሚሊየን ህዝብ ሃረርጌ ሲባረር፣ ወደተወለደበት ከመመለስ ይልቅ፣ የኦሮሞን ቁጥር በአዲስ አበባ ለማግዘፍ በሚመስል መልክ፣ አዲስ አበበ እየሰፈረ ነው። እንግዲያው ገጠርና ቆላማ በሆነው ሃረር፣ በእርሻና ከብት ርቢ ይተደደር የነበረውን ህዝብ፣ መልሶ፣ ባገሩ ማቋቃም ሲገባ፣ አዲስ አበባ ማስፈሩ ለእኩይ አላማ መሆኑ ግልጽ ነው። የስራ እድል በሌለበት ፣ ነባር ነዋሪዎች በመብራት፣ የውሃ ችግር ሲሰቃዩ፣ የአማራና የሌሎች ዜጎችችን ቤቶች፣ ለገዳዲና ለገላፍቶ በግፍ እያፈረሱ፣ ከሃረር ኦሮሞዎችን ማስፈር ፣ አንተም ሆንክ፣ ቡድንህ ከመጠየቅ አይድንም።

ከወራት በፊት፣ በትግራይ ድንበር ላይ የነበረ ሰራዊት ወደ ማህል አገር በመንቀሳቀስ ላይ ባለበት ግዜ ደጋግሞ ታግቷል። ለቀናት መንገዱን በዙጉበት ዜጎች አንዲት ጥይት አልተተኮሰም። ይህም ተገቢ ነበር። ግን ይህ በሆነ በሳምንት ግዜ ፣ ጎንደር አካባቢ ይሀው ኢትዮጵያ ሰራዊት ፣ 29 ሰላማዊ ሰልፍ የወጡን አማሮችን በግፍ በጥይት ደብድቦ 9 ውድያው ገድሏል። የወያኔን የመንገድ ስራ ድርጅት ተሽከርካሪዎች በፍርድ ቤት ማዘዣ ለመፈተሽ፣ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በነበሩ አማሮች ፣ የጥይት ናዳ ያወረደባቸው የወያኔን ግል ድርጅት ያጀበ ሰራዊት ነው። በትግራይ ውስጥ ጠጠር ሳይወረወር፣ በአማራው ላይ ጥይት ያዘነበው ሰራዊት የጦር አበጋዝ፣ ለዎያኔ ያደረ ምርኮግኛው ኦሮሞ መሆኑን ልብ ይሏል።

የድንበርን ውዝግብ ይፈታ ዘንድ በሚል ምርህ፣ በተቋቋመው ቡድን ፣ በሃይል የወልቅይትና ራያን ወደ ትግራይ የከለለውን የወያኔ የቀድሞ መሪ ሳይቀር አካተሃል። በዋኔና ኦነግ የተጠነሰስ ህገንግስት ሳብያ፣ ወሎን፣ ሸዋን ቆራርጦ ኦሮምያ ለተባለው ግዛት ለደለደለውና ለበርካታ ሚሊዎን አማራ እልቂትም ሆነ፣ ባገርቷ ለደረሰው መከራ ከሚጠየቁት መሃል አንዱን፣ ነጋሶ ጊዳዳን ጭምር ሰይመሃል። ለድንበር ዳኝነት ያሰባስብካቸውን አላማውን የሚዋጅ ስብዕና የሌላቸውን ጭምር ናቸው። ግማሹ ከኦሮሞዎች ናቸው። ያንን አጥፊ ሰነድ ሽሮ ፣ በኢትዮጵያውያን ፈቃድ ህግ_መንግስት ከመቅርጽ ይልቅ “የአይጥ ምስክሯ ድንቢጥ” እንዲሉ ሆኗል።

በ 1440 ግድም፣ በግፍ አንድን ቄስ የገደለ ልጁን፣ በፍትሃነገስት ህግ መሰረት፣ በስቅላት የቀጣው አጼ ዘራዐያዕቆብ የነገሰባት ኢትዮጵያ ፣ ከግማሽ ምዕት ዐለም በኋላ ፣ እንዲህ የወረዳ መውረድ፣ “እሪ በይ” ኢትዮጵያ ያሰኛል።
በመጨረሻ፣ የባለቤትነት ህጋዊ ሰነድ ያላቸውን ሰዎች ቤቶች፣ ከማፍረስ የባሰ የጦርነት አዋጅ የለም። በለገዳዲና ለገጣፎ ፣ መሬቱን የቸበቸቡ የኦሮሞ ሹማምንትና አፍራሽ ግብረሃይል፣ እንደወራሪ ጦር ፣ ቤቶቹን ሲያፈርሱ፣ ኡኡ ፣ ይሉ የነበሩን ባለቤቶች ‘መጤ’ በማለት እየተሳደቡም፣ነበር። እነኝህ ለህግም ሆነ፣ ለስረአት ባይተዋር የሆኑ፣ የኦሮሞ ሹማምንት፣ ‘መጤ’ የሚሉት ያን የፈረደበትን አማራ ብቻ አደለም። ከድፍን ኢትዮጵያ የመጡ ወገኖቻችን ሁሉ ነበር። ይህ የፈሪዎችና ፣ የአይምሮቢስ ኦነግ ልሂቃን ድርጊት፣ የጨዋና የደጉ ኦሮሞ ህዝብ ሊያውግዘው ይገባል። ይህ ግፍ ከቀጠለ፣ የኦሮሞን መንግስት ወረራ የማይቋቋም አይኖርም።

የኢትዮጵያውያን ለአንድ ትውልድ፣ የግፍ ግፍ የፈጸሙባቸውን የወራሪ ወያኔዎች ቡድን ሲፍረከረክ ፣ ህዝቡ ስራዐቱ የተገረሰሰ መሰሎት ነበር። ከጅምሩ፣ ረዥም እድሜውን በወያኔ ሞግዚትነት እንዳንተ ላደገ ዜጋ፣ ለኢትዮጵያዊነት ባዕድ ሊሆን ይችላል። የኢትዮጵያን ጥንታዊነት፣ ተረትና ፣ የቅርብ ግዜ ፈጠራም እንደሆነች ሲሰማ ለኖረ ፣ በወያኔው ግብረ፟_አበር በኦነግ ትርክት ፣ ‘ምንሊክ 5 ሚሊየን ኦሮሞን ፈጅቷል’፣ ‘የሴቶች ጡት ቆርጧል’፣ እየተባሉ በደረቅ የሃሰት ታሪክ ለተጋቱ ኦሮሞ ሹምምንት፣ ይህ የተፈጸመው ግፍ ፣ ከመጤፍ አይቆጠር ይሆናል። የአቢይና ለማ ማንነት ከዚህ አይዘልም። ‘’ከወርቁ’ የትግሬ ነገድ ‘የተፈጠረኩ ነኝ’ ይል የነበረውን አለቃህን ቃል መቀሌ ሄደህ፣ እንደበቀቀን፣ ስትደግም፣ ያልተቸገርክ አንበሳ ነህ። ባንጻሩ አሜሪካ በሄድክበት ወቅት፣ አለም ያወቀውን ጸሃይ የሞቀውን ፣በአማራ ላይ የተፈጸመ የዘር ፍጅት፣ በአደባባይ የካድክ ጎበዝ ነህ።

በአኖሌው የጥፋት ሃውልት ግንባታ፣ ግዙፍ ተሳትፎ እንደነበረህ አይካድም። በሃሰት ትርክት በተመሰረተ ወንጀል፣ ያልታጠቀ፣ያልጠረጠርንራ እልቆ መሳፍርት የሌለውን አማራ እልቂት ያስከተለን ሃውልት፣ ከመቅጽበት መናድ ሲገባህ፣ አስካሁን ተገትሯል። ስልጣን እንደያዝክ ኦሮምያ በሚባለው የደባ ክልል የሚኖረውን 15 ሚሊዎን ህዝብ ፣ ሰቆቃ ፣ቀጥለህበታል ። በአማርኛ እንዳይማር፣ እንዳያስተምር ፣ በመንግስት ተቋማትም እንዳይገለገል የሚያደርገውን ፣የግፍ እግድ እንኳን አላነሳህም። ከዚይ ይልቅ፣ ኦሮሞ ያልሆኑን ኢትዮጵያውያን ህጋዊ ቤቶች ማስፈራረስ፣ ለም እንዳጣደፈህ ፣ አንድ ቀን የምትጠየቅበት ጉዳይ ነው.።

አንድ በሰሞኑ ለገጣፎ ቤቷ የፈረሰባት እናት፣ ያንተን ከኤርትራን ጋር እርቅ የመሻት ስብዕና ፣ እትዮጵያውያንን በግፍ በመፈንቀል ጭካኔህ ስትገልጽ በእንባ ነበር። ለበድ ስደተኛ የሚሳሳ መንግስትህ፣ በእትዮጵያውያን ላይ ይህን ግፍ መፈጸሙ፣ ይቅር አያሰኝም።

ይህ ኦሮምያ በሚሉት መስተዳደር የተጧጧፈው ፣ የሌሎችን ዜጎች በህግ የተሰሩና ፣ ለአመታት ይገበርባቸው የነበሩን መኖርያ በቶችን ፣ የማፍረስ ዘመቻ ፣ ያንተንም ሆነ ፣ የምትወክለውን ህዝብ ስነልቦና ምንነት ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ኢላማ የተደረጉት የከተማዋ አብዛኛ ነዋሪ የሆነው ፣ በህግ ከለላ የሚፈጀውና የሚፈናቀለው አማራ ብቻ ሳይሆን፣ ከተለያዩ ቦታዎችህ የመጡ ነባር ኢትዮጵያውያን ናቸው።

‘ትኩስ እረሳ፣የደረቀን አስነሳ’

ይባስ ብለህ ፣ የሽዎችን ኢትዮጵያውያንን ቤቶች አፍርሶ ወገኖቻችንን ለቀን ሃሩር፣ ለሌሊት ቁር መዳረግህ፣ መልዕክቱ ግልጽ ነው። ልክ በፋሽስት ጣልያን ግዜ ተሞክሮ እንደከሸፈው ሁሉ፣ ህዝብ ሊያፋጅ መቻሉን አትስተውም። ደግነቱ የሸዋ ኦሮሞ፣ በወገኑ አማራውም ሆነ ለሌሎች፣ አጋር ወንድምነቱን በመግለጽ፣ ልዕልናውን ዛሬም አስመክሯል።

የአቢይ መንግስት ግን ‘ትኩስ እሬሳ፣የደረቀውን አስነሳ’ አስኝቶናል። የኦሮሞው መንግስት ድርጊት፣ የትላንቱን የከፋውን አባጆቢርና፣ መሰሎቻቸው፣ በወለጋ ፣ በኢሉባቦር፣ በሃረር ፣በጣልያን ሃይ ባይነት፣ የተፈጁትን፣ ያልታጠቁ አማሮች ሰቆቃ ያስታውሰናል። ዛሬ መሳለቂያ ባደረጋቸው ‘አዲስ አበባን የኦሮሞ ናት’ የሚለው ቅዠት፣ የሚናውዙት ፣ የኦሮሞው መንግስት ሹማምንት ቡድን ፣ አቅም ቢኖረው፣ ከፋሽስቱ ወያኔና፣ ከጣልያን ያልተለየ ግፍ ባማራውና በሌሎች ወገኖች ከመፈጸም አለመመለሱን ግልጽ ነው። ባለማወቅ እንጅ፣ ‘የቸገረው እርጉዝ ያገባል’ ሆኖ ነው እንጂ”‘ ባንተ ተስፋ የጣለው፣ የስራዐት እንጂ አንትን መሰል መለዋወጡ እርባና እንደሌለው በተረዳ ነበር። የጭካኔ ዘመቻህ ፣ ያንተም ሆነ የባለሟል ኦርሞዎች ማንነት፣ይፋ ማድረጉ እሙን ነው።

የአዲስ አበባን በረራነት አትስተውም። በትንሹ የ 1500 ዘመናት በፊት ፣ የአማራ፣ የጉራጌና ጋፋቶችና ሌሎችም ኢትዮጵያውያን ከተማ መሆኗን አታውቅም አይባልም። ነባርቹ ኢትዮጵያን እንክዋን ፣ ‘የኛ ብቻ ከተማ ናት’ ብለው አልቀለሉም።

ማንኛውም ነገር ገደብ አለው። ያንተን አመራር ጨምሮ። ዛሬ አንተ የምትመራው በሚመስለው የወያኔ መንግስት ፣ የሚፈጸመው ግፍ አንድ እና ሁለት የለውም። ያለአንዳች ሃፍረት፣ ይሉኝታ፣ ፈሪሃ እግዚብሄር፣ ህዝብን ለርስበርስ ለጦርነት የሚገፋፋ ድርጊት መፈጸሙን መገንዘብ የሚሳንህ አይመስልም። ምናልባትም ፣ ያላዋቂ ትዕቢት ገፋፍቶህ ይሆናል። ተሳስትሃል።

ስለዚህ አንድ ነገር ልብ አድርግ። አግባብ ያልሆነ ተግባር አያዋጣም። ዛሬ የሚፍጸመው ግፍ ፣ ዋጋ ማስከፈሉ አይቀሬ ነው። እዳው ከባድና ከነአራጣው መከፈል ስለሚኖርበት ። አበው ‘አደባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ’ እንዲሉ። ከመቅጽበት ይህንን የህዝብ ሰቆቃ ካላቆምክ፣ የተፈጥሮ ህግ ነውና፣ የተገፋው ይነሳል። የፈላ ሲገነፍል፣ ብዙ መዘዝ ይኖረዋል።

በመጨረሻ፣ የግራኝን ወደር የለሽ ገድል በመጥቀስ ልሰናበት ። ጥሎበት እንደ ወያኔና፣ የባቶቻቸው ጌታ ጣልያን፣ ግራኝም አማራውን እጅግ ይፈራው ነበር። ስለሆነም ፣ ሃይማኖት ሳይለይ፣ እስላሙንም ክርስቲያኑንም አማራ ፣እኩል ነበር ይፈጀው የነበረው። አንዳንድ ያማራ ስፍራዎች ፣ ከአስሩ ነዋሪ፣ አንድ ብቻ የተረፈበት ግዜ ነበር። ዛሬ ኦነግ፣ የወያኔን አማራውን የማጥፋት ዘመቻ ፣ አግጥጦና አፍጥጦ የቀጥለ ይመስላል። በሁለቱ ጣምራ ጦር የተፈጀው ህዝብ፣ ሂትለር ከፈጃቸው አይሁዶች ቁጥር ይበልጣል። ግን ግፍም እንደ ህያው ፣ እድሜ አለው። ዘለቄታ አይኖረውም ። ይቅናህ!!

___
ማስታወሻ:በዚህ ጽሁፍ ላይ የተንጸባረቁ ሳሃቦች የጸሃፊውን/የጸሃፊዋን እንጂ የድረገጹን አቋም አያንጸባርቁም። ነጻ አስተያየት ወይንም ሃሳብ በዚህ ድረ ገጽ ለማውጣት ጽሁፍዎትን በ info@borkena.com ይላኩልን።

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here