spot_img
Friday, June 14, 2024
Homeነፃ አስተያየትየስደተኞች ፈተና በአውሮፓ (አሸናፊ በሪሁን ከseefar)

የስደተኞች ፈተና በአውሮፓ (አሸናፊ በሪሁን ከseefar)

አሸናፊ በሪሁን ከseefar
ግንቦት 12 ፤ 2011 ዓ ም

ዛሬም ብዙ ስደተኞች የተሻለ ኑሮን ፍለጋ ከአፍሪካ አህጉር የተስፋይቱ ምድር ወደሚሉዋት ወደ አውሮፓ ይሰደዳሉ። ሆኖም አብዛኛዎቹ ስደተኞች አልመውት የሚሄዱት ህልም እና ጠስፋ እና እና አውሮፓ ከደረሱ በሃላ ያለው እውነታ ለየቅል ነው ፡፡ እነሱም አውሮፓ ከገቡ በሆላ ስለሚያጋጥሟቸው መሰናክሎች ፈፅሞ ግንዛቤ የላቸውም።
ስደተኞችን በተመለከተ የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት የሚተዳደሩት በደብሊን መተዳደርያ ደንብ መሰረት ነው፡፡ በዚህ ደንብ መሠረትም ጥገኝነት ጠያቂዎች በመጀመርያ በገቡበት የአውሮፓ አገር ውስጥ ሃላፊነት ወይም ተጠያቄነት ስር ናቸው። ይህም ማለት ስደተኞች አንድ የአውሮፓ አገር ከደረሱ በሃላ ወደ ሌላ አገር ከተንቀሳቀሱ ተይዘው መጀመርያ ወደ ገቡበት አገር እኒዲመለሱ ይደረጋሉ። በተጨማሪም የደብሊን መተዳደርያ ደምብ ጥገኝነት ጠያቄዎች በየትኛው ሀገር እንደሚኖሩ ፣ የየትኛው ሀገር የጥገኝነት ጥያቄዎቻቸው እንደሚመረምረና በየትኛውም ቦታ እንደሚቀመጡ ምርጫ አይሰጣቸውም።

ብዙዎቹ አፍሪካውያን ስደተኞች አውሮፓ እንደደረሱ ጥገኝነት የሚያገኙ እና ቶሎም ወደ ስራ እንደሚገቡ ያልማሉ ፡፡ ይሁን እንጅ አብዛኛዎቹ የአውሮፓ አገራት ፖለቲካዊ እና የሰብብዊ መብት ይዘት ያላቸው የጥገኝነት ጥያቄዎች ብቻ ነው ተቀብለው የሚመረምሩት፡፡ የእነዚህ የጥገኝነት ጥያቄ ማመልከቻ ሂደትም ረጅም ጊዜ የሚወስድ እና ውስብስብ ነው። ምንም እንኳን አብዛኛዎቹ አገሮች ጉዳዩን በስድስት ወራት ውስጥ እልባት እንዲያገኙ የሚያደርጉ ቢሆኑም፤ ከፍተኛ የጥገኝነት ጥያቄ ማመልከቻዎች በሚበዙበት ሁኔታ ግን ሂደቱ ረጅም ጊዜን ይወስዳል ፡፡ የአንዳንድ አመልካቾች ጥያቄአቸው ተቀባይነት ሲያገኝ የሌሎች ደግሞ ተቀባይነት አያገኙም። ይህም ማለት አለም አቀፋዊ ጥበቃ ወይም ከለላ ለማግኘት ሲሉ ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ የተደረገባቸው ስደተኞች አገሩን ለቀው እንዲሄዱ ይገደዳሉ ማለት ነው ። አንዳንዴም ወደ መጡበት አገር እስኪመለሱ ድረስ በእስር ቤቶች እንዲቆዩ ይደረጋሉ። ብዙ ሕገ ወጥ ስደተኞች አውሮፓ ከገቡ በሃላ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ በመደረጉ ያለ ህጋዊ ቪዛ አውሮፓ በመግባታቸው ምክንያት ተይዘው ወደ አገራቸው ይመለሳሉ፡፡

አብዛኞዎ አፍሪካውያን እና ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የኢኮኖሚ ጥገኛ ስደተኞች ናቸው፡፡ ኑሮቸውን እና ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው ለማሻሻል ወደ አውሮፓ አገሮች የተሰደዱ ስደተኞች፡፡ እነዚህ ስደተኞችም ታዲያ በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ በመሆናቸው እና የጥገኝነት ምክንያቶቻቸውም ውሃ የማያነሱ በመሆኑ የጥገኝነት መብት አይሰጣቸውም፡፡ በአውሮፓ አገራት ውስጥ በህጋዊ መንገድ መኖር አይችሉም። ህገወጥ በመሆናቸውም ስራ ለማግኘት ይቸገራሉ፡፡ በአውሮፓ ያለው የቅጥር ሁኔታ በጣም ህግን የተከተለ ነው፡፡ ስራ ፈላጊዎች ተቀጥረው ለመሰራት ህጋዊ የስራ ቪዛ ማግኘት አለባቸው። በአውሮፓ ውስጥ ያሉ ካምፓኒዎች ህጋዊ የስራ ፍቃድ የሌላቸውን ሰዎች መቅጠር አይችሉም። የልዩ ህግ አስከባሪ ወኪሎች ህጋዊ ያልሆኑ ሰራተኞች እንዳይቀጠሩ በካምፓኒዎች ላይ መደበኛ ቁጥጥር ያደርጋሉ፡፡ በአውሮፓ ህግ መሰረት የአንዳንድ አገራት ጥገኝነት ጠያቂዎች መኖርያ ቤት እንዲያገኙ ይደረጋል። ይህ ጥቂት እፎይታ የሚሠጥ ቢመስልም ጥገኝነት ጠያቂዎች የት መኖር እንደሚፈልጉ ምርጫ አይሰጣቸውም። አንዳንዴም ከቦታ ወደ ቦታ እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል። አንዳንደቹ ባሉበት አገር ውስጥ ሆነው ከጓደኞቻቸው ወይም ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው በሩቅ ቦታ እንዲኖሩ ይገደዳሉ። በዚህም ምክንያት ብዙ ስደተኞች ብቸኝነት ወይ የመገለል ስሜት ያድርባቸዋል። ጥገኝነት ጠያቂዎች ጥያቄያቸው አንዴ ተቀባይነት ካገኘ በሃላ ግን አስቀድሞ የተሰጣቸውን መኖርያ ቦታ በመልቀቅ የራሳቸውን መኖርያ ቤት እንዲፈልጉ ይደረጋሉ።

ጥገኝነት ጠያቂዎችና ህገወጥ ስደተኞች በብዙ የአውሮፓ አገሮች ነፃ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ይቸገራሉ፡፡ ህገ ወጥ ስደተኞች ነፃ ህክምና ማግኘት የሚችሉት ለአጣዳፊና ለህይወት አስጊ ለሆኑ ህመሞች ብቻ ነው። ይህ ካልሆነ ግን የህክምና እርዳታ ለማግኘት መክፈል ያለባቸው ሲሆኑ ዋጋውም ከፍተኛ ገንዘብ ነው።

እንኮን ለህገወጥ ስደተኞች ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ላገኙት አፍሪካውያን ስደተኞችም ኑሮ በአውሮፓ ቀላል አይደለችም ፡፡ ገበያው የሚፈልገውን ህጋዊ የስራ ዕድል ለመቀላቀል ዘርፈ ብዙ መሰናክሎች ያጋጥማቸዋል። በአንዳንድ የአውሮፓ አገሮች ያለው የስራ አጥነት ቁጥር በተለይ ዝቅተኛ የስራ ልምድና ትምህርት ወይም ብቃት ባላቸው ወጣቶች ላይ በጣም የላቀ ነው። አውሮፓ ያለው ስራ በአፍሪካ ካለው የስራ አይነት ስለሚለይ በአውሮፓ ውስጥ ስራ ለማግኘት የሚያስችል አስፈላጊውን ችሎታ ወይም ብቃት የላቸውም። ከባህር ማዶ ከአፍሪካ ይዘውት የመጡት የስራ ልምድ እና ትምህርት በቀጣሪዎቻቸው ዘንድ ብዙም ተቀባይነት አያገኝም። ስራን ለማግኘት የሚኖርበትን አገር ቋንቋ መናገር እና መፃፍም ያስፈልጋል። ምንም እንኳን በአውሮፓ ያለው የክፍያ መጠን ከአብዛኛው የስደተኞች ከመጡበት አገር ጋር ሲነፃፀር የተሻለ ነው ቢባልም የኑሮ ውድነት ደግሞ በዛው ልክ በጣም ውድ ነው። በአውሮፓ ለዕለት ኑሮ፣ ለመኖርያ ቤት፣ ለትራንስፖርት፣ ምግብ እና ለሌሎች መሰል ወጪዎች የሚወጣው ወጪ ከፍተኛ ነው።

በአውሮፓ ብዙውን ጊዜ የዩኒቨርስቲ ትምህርት በነፃ ይሰጣል። ለስደተኞች የሚሰጠው ነፃ የትምህርት ዕድል ግን ጥቂት ነው፡፡ ከፍሎ ለመማርም የአውሮፓ ዩኒቨርስቲዎች የሚጠየቁትን ውድ የትምህርት ክፍያ ለመክፈል አቅም የላቸውም። ይህ ሁኔታም ስደተኞች በቂ ዕውቀትና ችሎታ ከማግኘት ስለሚያግዳቸው ከፍተኛ ክፍያ የሚያገኙበት ስራ የማግኘት ዕድል የላቸውም። በዚህም ምክንያት አብዛኛዎቹ ስደተኞች በቂ ገንዘብ አግኝተው ራሳቸውን ለመቻል ይቸገራሉ። ቀደም ብሎ በአገራቸው ውስጥ እያሉ የተማሩት እና ሙያን የሚጠይቅ ስራ ለማግኘት ሲፈልጉ አገራቸው ከሚገኙት የትምህርት ተቋሞች ህጋዊ በማስረጃ የተረጋገጠ የትምህርት መረጃ እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ። አንዳንድ ስራ ቀጣሪዎች ለሙያው ዕውቅና አይሰጡትም።

ከአውሮፓ ማህበረሰብ ጋር መቀላቀል ሌላው የአፍሪካ ደደተኞች ፈተና ነው ፡፡ ብዙ ስደተኞች ቤተሰቦች ለአገራቸው ባህል ያላቸው ከፍተኛ ዋጋ በመጠበቅ ከአዲሱ ባህል ጋር መቀላቀል ያስቸግራቸዋል ፡፡ በአውሮፓ ያለውን የተለየ አዲስ ህይወት ለመልመድ ይቸገራሉ፡፡ በጊዜ ሂደት ቢለማመዱትም በቋንቋ እና በሌሎች ባህላዊ ልዩነቶች ምክንያት ከአካባቢው ማህበረሰብ አድልዎ ይደርስባቸዋል። አንዳንድ ስደተኞች የመኖርያ ፍቃድ ካገኙ በሃላ ቤተሰቦቻቸውን ወድያውኑ ወደ አውሮፓ ለማምጣት ተስፋ ያደርጋሉ። ሆኖም ግን ቤተሰብ የማዋሃድ ወይም የማገናኘት አቤቱታ ረጅምና ጥብቅ በሆኑ ሂደቶች ውስጥ የሚያልፍ በመሆኑ ጊዜ የሚወስድ እና አድካሚ ነው ፡፡

አሁን አሁን በስደተኞች የተማረሩት አውሮፓውያን እና ማህበረሰቦቻቸው ስደት ጠል የሆኑ ፓሊሲዎችን እና አመላካከቶችን ማራመድ ጀምረዋል፡፡ በታቻላቸው መጠንም ስደተኞች ላለመቀበል የሚያስችሉ ቢሮክራሲዎችን በማብዛት ስደተኞች እንዲማረሩ በማድርጋቸው ስደተኞች ተስፋ አድርገውት በሄዱት አውሮፓ ለብዙ ፈተናዎችን እየተዳረጉ ነው፡፡ የተስፋይቱ ምድር የሚሉዋት አውሮፓም ለስቃይ እና መከራ እያዳረገቻቸው ነው፡፡ ታዲያ እኛም አፍሪካዎያን ስደትን ወደ አውሮፓ ሲናስብ አውሮፓውያን ስለሚከተሉት የስደተኞች ፓሊሲ፣ከስደት በሆላ ስለሚያጋጥሙን ሁኔታዎች ማወቅ ግድ ይለናል ነው፡፡ ሁሌም ስደት ሲታስብ ህጋዊ መንገድን መከተል ደግሞ የተሻለው አማራጭ ነው ፡፡
___
ማስታወሻ:በዚህ ጽሁፍ ላይ የተንጸባረቁ ሳሃቦች የጸሃፊውን/የጸሃፊዋን እንጂ የድረገጹን አቋም አያንጸባርቁም። ነጻ አስተያየት ወይንም ሃሳብ በዚህ ድረ ገጽ ለማውጣት ጽሁፍዎትን በ info@borkena.com ይላኩልን።

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here