spot_img
Sunday, September 24, 2023
Homeነፃ አስተያየትበኢትዮጵያ የመሰረተ-ልማት ስርጭት ፍትሃዊነት ሲፈተሽ (ዶ/ር አዳነ ገበያው ካሳ)

በኢትዮጵያ የመሰረተ-ልማት ስርጭት ፍትሃዊነት ሲፈተሽ (ዶ/ር አዳነ ገበያው ካሳ)

advertisement

ዶ/ር አዳነ ገበያው ካሳi
ጥቅምት 9 2012 ዓ .ም.

በዕውነት ወይም በሃቀኛ መረጃ የተደገፈ ውይይት የአገራችንን ችግር ለመፍታት ከሚያስፈልጉ ተቀዳሚ ነገሮች አንዱ ነዉ። በኢትዮጵያ መሰረተ-ልማትን በፍትሃዊነት ማዳረስ ተገቢ ከመሆኑም አልፎ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ይረዳል። ዜጎችም ስለ መሰረተ-ልማቱ ስርጭት ግልጽ፣ ተዓማኝና ወቅታዊ መረጃ የማግኘት መብት ሊኖራቸው ይገባል። 

ከቅርብ ጊዜ ወድህ በአማራዉ ክልል የዳስ ትምህርት ቤቶች መኖራቸው እየተዘገበ ነው። ይህም የአማራ ክልል እንደ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ የጤና አጠባበቅ መስጫ ተቋማት፣ መንገድ እና ንጹህ ዉሃን በተመለከተ ከሌሎች ክልሎች አንጻር ሲታይ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ተጠቃሚ ሆኗል ወይ የሚለዉን ጥያቂ እንድናነሳ ያደርጋል? የዚህ ጽሁፍ ዋናዉ አላማ በአሃዛዊ መረጃ ላይ ተመርኩዞ ለዚህ ጥያቄ መልስ ለማግኘት ነው። 

ኢትዮጵያ ከአለም የመጨረሻወቹ ድሃ አገሮች አንዷ ናት። ህዝቡ ብዙ ያልተሟሉለት መሰረታዊ ነገሮች አሉ። ምንም አንኳ ይህን አብዛኛዉ በችግር ዉስጥ የሚኖር የኢትዮጵያን ህዝብ በቋንቋ በተመሰረተ አስተዳደራዊ ክልል ከፋፍሎ በዚህ መንገድ ማነጻጸር አስደሳች ነገር ባይሆንም፣ በዜጎች መካከል መልካም ግንኙነትን ለማጠናከር አሃዛዊ መረጃውን በግልፅ ለህዝብ ማቅረብና ዕዉነቱን ማሳየት ተገቢ ነው። 

ለዚህ ትንተና የዋለው መረጃ ሁሉም የተገኘዉ ከኢትዮጵያ መንግስት ነው። የአገልግሎቶቹን ስርጭት ፍትሃዊነት ለመመዘን እያንዳንዱ ክልል ከኢትዮጵያ ህዝብ ስንት በመቶዉን ይዟል የሚለውን እንደማነጻጸሪያ (benchmark) ተወስዷል። በኢትዮጵያ ፍትሃዊ የአገልግሎትና መሰረተ-ልማት ስርጭት ሊኖር ይገባል። ሆኖም ግን፣ ፍትሃዊነት ማለት እኩልነት ባለመሆኑ፣ መንግስት ከዚህ ተጨማሪ ማነጻጸሪያና አግልግሎቶቹን የማዳረሻ መመዘኛዎች ሊኖሩት እንደሚችልም ይገመታል። 

ሙሉውን በ ፒ ዲ ኤፍ ፍርማት ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

___

ማስታወሻበዚህ ጽሁፍ ላይ የተንጸባረቁ ሳሃቦች የጸሃፊውን/የጸሃፊዋን እንጂ የድረገጹን አቋም አያንጸባርቁም። ነጻ አስተያየት ወይንም ሃሳብ በዚህ ድረ ገጽ ለማውጣት ጽሁፍዎትን በ info@borkena.com ይላኩልን።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,682FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here