spot_img
Wednesday, June 12, 2024
Homeነፃ አስተያየትከዕለታት አንድ ቀን- ስለዘ-ሃበሻ

ከዕለታት አንድ ቀን- ስለዘ-ሃበሻ

ሰማነህ ታ. ጀመረ፤ ኦታዋ፤ ካናዳ
ቀን፥ ሚያዝያ 10, 2012

ቀዳማይ ት/ቤት እያለን ታሪካዊ ድርሰት ጻፉ ስንባል የመግቢያ ዓረፍተ ነገራችን የሚጀምረው’ከዕለታት አንድ ቀን’ በሚል ሀረግ ነበር። በልጅነት አዕምሮዬ የተቀረፀች በመሆኗ እጅግ እወዳታለሁ። ‘ከዕለታት አንድ ቀን’ በጊዜ መርከብ አሳፍራ ብዙ ታስጉዛለች፤ የማስታወስ ችሎታን ታዳብራለች፤ መስካሪና ተራኪም ስለምታደርግ ከሃምሳ ዓመት በላይ ይዣት እዞራለሁ።

ወደ ርዕሴ ልመልሳችሁና ከዕለታት አንድ ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተሰቤን ይዠ ወደ ሚኒሶታ ተጓዝሁ። የጉዞየ ዓላማ በሚኒሶታ የሚኖሩ ወድሞቸንና ዘመዶቸን ለመጠየቅና በገደምዳሜም አሜሪካንም ለመጎብኘት ነበር። በግሌ አሜሪካን ቀድምሲል ባውቃትም ለቤተሰቦቸ ግን መጀመሪያቸው ነው። ስንደርስ ብዙ የሚወራላት አሜሪካን እንደጠበቅነው ሆና አለገኘናትም። በእኛ እይታ ከካናዳ ብዙ የተለየች ባትሆንም ለየት የሚአደርጉ ባሕሪያትን ግን አስተውለናል። አሜሪካ ነገሮቻቸው ሁሉ ለቀቅ ለቀቅ ያሉ ናቸው። ለምሳሌ ሃገሩ ትልቅ፤ አውራጎዳናዎች ሰፊና ረዥም፤ ሰውና መኪናው ግዙፍ፤ ምግቡና በርገሩ ደጓሳ፤ ድምፃቸው አንቂ፤ ገንዘባቸው ጉልበተኛ፤ መረጃ ለምስጠት ቀናኢና ፈቃደኞች፤ ሲአነጋግሩህ ለግብግብ የፈለጉህ ስለሚመስልህ የመበርገግ ብርክ ይይዝሃል። እነዚህ በጉብኝት ጊዜ የሚገኙ ገጠመኞች እንደሆኑ አውቀህ በትዕግስት ካለፍኸው ትወደዋለህ።

እናም አገር ጎብኝ ስትሆን መረጃ ከዚህም ከዚያም ማሰባሰብ ተቀዳሚ ስራህ ይሆናል። ጋዜጣ በማንበብ፤ ራዲዮና ቴሌቪዥን በማየት እንግዳነትህንና ባይተዋርነትህን ለማሸነፍ ትሯሯጣለህ። አንድ ቀን ወንድሜ ወደ አንድ የምግብ መደብር ይዞኝ ይሄዳል። በሱቁ ብዙ ጋዜጦች ተደርድረው ስላየሁ ጠጋብየ ስቃኝ ዘ-ሃበሻ የሚለው ጋዜጣ ቀልቤን ሳበው። ገጾቹን እያገላበጥሁ ገረፍ ገረፍ አድርጌ አነበብሁት። በጋዜጣው ሽፋን፤ አጻጻፍ እና ይዘቱ ስለተመሰጥሁ ልገዛው ወሰንሁ። ወንድሜ ክፍያ ለማድረግ ወደ ገንዘብ ተቀባይዋ ሲጠጋ የያዝሁትን ጋዜጣ ስላየው ነፃ ስለሆነ መክፈል የለብህም አለኝ። ይህን የመሰለ ጋዜጣ ለምን ነፃ እንደሆነ ውስጤ እየተገረመ ይዠው ወጣሁ።

በጋዜጣው መደነቄን ያስተዋለው ወንድሜ ስለጋዜጣው አጀማመር እና ስለአርታዒው ሄኖክ ዓለማየሁ የሚአውቀውን ያህል አጫወተኝ። ከነገረኝ የማስታውሰው ጋዜጣው በአንድ ሰው ተዋናይነት የሚሽከረከርና የሚታተም መሆኑን ሳውቅ እጅግ ተገረምሁ። ሄኖክ ሃገር ቤት በጋዜጠኝነት ሙያ ተሰማርቶ ይሰራ እንደነበር እና ፀረ-መንግስት የሆነ መረጃ ለሕዝብ አሰራጭተሃል በሚል ለእስር ሲፈለግ ከሃገሩ ኮብልሎ ሚኒሶታ እንደገባ ተረዳሁ።

ስደተኞች ወደ ብልጭልጯ አሜሪካ በእንግድነት ሲገቡ ጥንቃቄ ካላደረጉ በብልጭልጭነቷ እየተታለሉና እየተዘናጉ ውቃያኖስ ውስጥ ሰጥመው ይቀራሉ። ቀድሞ የነቃ ስደተኛ ደግሞ ብልጭልጩን እያደነቀና እየተማረበት እራሱን ያቋቁማል። በሙያህና በፍላጎትህ በርትተህ ከሰራህ ፈተናው ብዙ ቢሆንም በመጨረሻ አሻናፊ ሆነህ ትወጣለህ። በአማሪካ እድገትህን ሊገድቡ የሚችሉ ሁለት ነገሮች ናቸውና። እንደኛው ጠፈር፤ ሁለተኛው ስንፍና ናቸው የሚባለው ያለምክንያት አይደለም። ዘ-ሐበሻ ለዚህ ምስክርና አረያ የሆነ ወጣት ኢትዮጵያዊ፤ ጋዜጠኛ፤ ለሙያው ያደረ፤ ስኬታማ ኢትዮጵያዊ በአማሪካ ቢባል ሲአንሰው እንጅ አይበዛበትም።

ሄኖክና ዘ-ሐበሻ ከምንም ተነስተው የዓለም ታዋቂ ጋዜጣና ጋዜጠኛ  እስከመሆን ደርሰዋል። በተለይ ከወገንተኝነት የፀዳ የዜና ምንጭ መሆን በመቻሉ የኢትዮጵያዊያንን አመኔታ አግኝቷል። የኢትዮጵያን ፖለቲካ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚ መረጃ የሚአቀርቡ ብዙ ማህበራዊ ድረገጾችና ጋዜጦች እንዳሸን ፈልተዋል። ሕዝቡም እንክርዳዱን ከፍሬው፤ ሐቁን ከአሉባልታ፤ ሰበር ዜናውን ከተራው ወሬ የመለየት ፈተና ገጥሞታል። ምስጋና ለሄኖክ ይሁንእና ሕዝብ የዜናን ታማኒነት አረጋግጦ የሚአወራው ዘ-ሃበሻ መዘገቡን ካወቀ በኋላ ሆኗል። ዘ-ሃበሻ በአጭር ጊዜ የሐቀኛ ዜና ማመሳከሪያ የሆነ የዘመናችን ዜና አቅራቢ ለመሆን የበቃ ነው።

በዓለም አቀፍ ደረጃ BBC፤ AL Jazeera እና CNN ታዋቂ እንደሆኑ ሁሉ ዘ-ሃበሻም በአስራ አራት ዓመት ውስጥ ከአንጋፋ ዓለም አቀፍ ብዙሃን ተረታ መመደብ መቻሉ አስገራሚ ነው። በተለይ AL Jazeera በፔትሮ ዶላር፤ BBC በእንግሊዝ መንግሥት በጀት፤ CNN በአሜሪካ መንግሥት ተደግፈው ለዚህ ደረጃ ደርሰዋል። ዘ-ሃበሻ ግን በአንድ ታታሪ ወጣት፤ ድሃ ኢትዮጵያዊ፤ ያለማንም ድጋፍ፤ በግል ጥረቱና ለሙያው ባለው ፍቅር ብቻ እራሱን ለከፍተኛ ደረጃ ያደረሰ ስለሆነ ክብር ይገባዋል። በግሌ ‘ከዕለታት አንድ ቀን’ በድንገት የተዋወቅሁት ዘ-ሃበሻ ለዚህ በቅቶ በማየቴ እጅግ ደስተኛ ስለሆንሁ በርታ፤ በርታ ለማለት ወድጀ ይህን መልዕክት አስነበብኋችሁ። መልካም በዓል ይሁንላችሁ።

ሄኖክ-በአካል የማላውቅህ  ኢትዮጵያዊ ወንድምህ፤  

ሰማነህ . ጀመረ፤ ኦታዋ፤ ካናዳ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here