ኢህአፓ
ሚያዚያ 13, 2012 ዓ ም
በዓለም ላይ በተለያዬ ጊዜያት ልዩ ልዩ መቅሰፍቶች እየተከሰቱ በሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት
አድረሰዋል፤ በሽታው ከተወገደ በኋላም አገሮችን ከፍተኛ ወደ ሆነ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊና
ህብረተሰባዊ ቀውስ እንደከትቷቸው ጥለውት ከሄዱት የታሪክ አሻራ እንረዳልን። ስለሆነም
አገሮች እንደዚህ አይነት ወረርሽኝ ሲከሰት እንዴት ሊወጡት እንደቻሉ መርምረን አሁን በዓለም
ላይ ህዝብ እየፈጀ ያለውን የኮሮና ወረርሽኝ (COVID-19) እንዴት መቋቋም እንዳለብን ስናስብ
ከፍተኛ የሆነ የሰው ፤ የቁሳቁስና የስነ ልቦና ዝግጅት የሚጠይቅ ሆኖ አግኝተነዋል።
ስልዚህም የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) መደረግ አለበት ብሎ ያመነበትን
ዝግጅት ከተለያየ አቅጠጫ በመመልከት ለመንግሥትም ሆነ ለልዩ ልዩ ተቋሞች የበኩሉን
ለማሳሰብ ይወዳል። በዚህ አጋጣሚ ከመንግሥት በኩል ለተደረገው የትብብር ጥሪም ኢህአፓ
ምላሽ ለመስጠት የሞከረ ሲሆን ለወደፊቱም የሚችለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁነቱን እየገለጸ
ለሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ለፖለቲካ ድርጅቶችም ጭምር፣ አገራችን ያጋጠማትን ችግር
በጋራ እንድንወጣ ጥሪውን ያቀርባል።
ሙሉውን ጽሁፍ በፒዲ ኤ ፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ማሳሰቢያ : በዚህ ጽሁፍ ላይ የተንጸባረቁ ሃሳቦች የድርጂቱን ሃሳብ አንጂ የቦርከናን ሃሳብ አያንጸባርቁም