spot_img
Monday, May 29, 2023
Homeነፃ አስተያየትምስጋና ለእረኛው ሐኪም ፕሮፌሰር ምትኩ- ለካ በዚህም ዘመን እንዲህ ዓይነት ኢዮጵያዊነት አለ?

ምስጋና ለእረኛው ሐኪም ፕሮፌሰር ምትኩ- ለካ በዚህም ዘመን እንዲህ ዓይነት ኢዮጵያዊነት አለ?

- Advertisement -


ሰማነህ ታ. ጀመረ ከኦታዋ፤ ካናዳ፤
መጋቢት 2012

ኮምኒዝም የኢትዮጵያን ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ አዘበራርቋል፤ መሰረታዊ የማንነት እሴቶቻችንን አፋልሷል። በትውልድ፤ በቋንቋ፤ በማህባራዊና በኢኮኖሚ የተሳሰረውን ሕዝባችንን አለያይቷል። የራስን እድል ያለቅድመ ሁኔታ እስከ መገንጠል መብትን ሕጋዊ አድርጎ ሕዝብን እርስ በርስ አባልቷል። ኢትዮጵያን ማዳከም ተራማጅ አስብሏል። ዓለም ይህን ተግባራችንን እየታዘበ መሳቂያ አድርጎናል። አሁን አሁን ለኢትዮጵያ ሕልውና የሚሟገቱ አነሊቀጳጳስ ዴዝሞን ቱቱ፤ ጃማይካዊያን፤ ግርሃም ሃንኩክን የመሳሰሉ ወዳጆቻችን ሆነዋል።

ይህን አፍራሽ ተግባር በፊታውራሪነት ሲአስተናግድ የቆየው ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይሆን ተማርሁ፤ ተመራመርሁ የሚለው የፖለቲካ ልሒቅ ነው። ልሂቁ የሃገራችንን ተጨባጭ ሁኔታ ሳያገናዝብ፤ ኮሙኒዝምን እንደወረደ ቀድቶ በሕዝባችን ላይ በመጫን ቤተሙከራ አድርጓል። እኔን ጨምሮ ኑሮውን በአሜሪካና በአውሮፓ እየኖረ ኢትዮጵያን በጎሳና በሃይማኖት ያናክሳል። የውጪው ዓለም ዘር፤ ጎሳና ሃይማኖቱን ሳይጠይቁ ዜግነት፤ ስራና ትምህርት ሰጠው አስተናግደውታል። ሰብአዊነትን በሚአስቀድም ማህበረሰብ ውስጥ እየተንደላቀቀ ወገኑን በጎሳ፤ በሃይማኖትና በጎጥ እየፈረጀ የሚአናቁርበት ምክንያት እንቆቅልሽ እንደሆነብን እንዳለን አለን። ከዚህ አጥፊ ስህተት መቸ እንደሚማር ባይታወቅም የመማር እድሎች ስላሉት በተሎ ቢአውቅበት ለራሱም፤ ለወገኑም ሆነ እወዳታለሁ ለሚላት ሃግሩም የሚበጅ ይሆናል።

መጋቢ ሃዲስ ኮሮና ሐዋርያ ነው ሲሉ ወረርሽኙ ጎሳና ጎጥ ለይቶ እንደማያጠፋ ሲአስተምሩ የማይማር ካለ እርሱ በጆርጅ ኦርዌል-84 የቅዥት ዓለም የሚኖር ብቻ ነው። ይህን የምንልበት ምክንያት በጅምላ ለመውቀስ ተፈልጎ ሳይሆን ኮሮና ካላስተማረ ሌላ ምን ያስተራል የሚለውን ማህበራዊ ሐቅ አፅንኦት ሰጦ ለመግለጽ ከመፈለግና በኦርዌል ዓለም ውስጥ የሚዳክሩ በሃገር ቤትና በውጪ የሚኖሩ የልሂቃን ትርክት፤ ንግግርና ሰበካ አሳሳቢና አስደንጋጭ ስለሆነም ነው። ለምሳሌ   አንዳንድ የጦር አበጋዞች፤ የታሪክ ምሁራን፤ የቋንቋ አስተማሪዎች  ቋንቋ መገናኛ ድልድይ መሆኑን እረስተው ቤተሰቦቻቸውንና ማህብረሰባቸውን አማርኛ እንዳይማሩ፤ በአማርኛ እንዳይገበያዩ፤ መጤ የሚሏቸውን በሜንጫ እኒዲአፀዱ ሲሰብኩና ሲቀሰቅሱ አይተናል። ጉድ የሚአሰኘው ደግሞ እነዚህ ፀረ ቋንቋ የሆኑ ሰዎች ቅስቀሳቸውን የሚአደርጉት በአማርኛ መሆኑ ነው። ይህ ማለት እንደ አስተማርነው እንጂ እንደምግባራችን አትሁኑ ነው። እንዲህ የዘቀጠ ምሁርና ፖለቲካኛ በየትም ዓለም አይገኝም።

በአንፃሩ ኢትዮጵያዊነትን አግዝፈው የሚአስተምሩ፤ የሚመክሩ፤ ስለኢትዮጵያና ሰብአዊነት የሚናገሩና የሚሰብኩትን ስናይ እንጽናናለን። ከአኝዋክ ጎሳ የተገኙት አቶ ኦባንግ ሜቶ ስለሰብአዊነትና የኢትዮጵያ አንድነት ሲሰብኩ እያየን ተደስተናል። ከኦረሞ ማህበረሰብ የተገኙት መምህር ታዬ ቦጋለና አምባሳደር ሱሌማን ደደፎን የመሰሉ ምሁርና ዲፕሎማት ለሃገርና ለእውነት ቆመው ሲአስተምሩ ስናይ ኢትዮጵያ ማሕፀነ ለምለም የመሆኗ ምስጢር ይገለጽልናል። በደቡብ ክቡር አቶ ታዲዎስ ታንቱ፤ ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳን የመሰሉ እንቁ አስተማሪዎች እናገኛለን። መጋቢ ሃዲስና ሸህ ሞሐመድ ዓሚንን የመሰሉ ሰባኪ ሲገኝ በሃገርና በእምነት ኮርተን እንለመልማለን።

አሁን ከእረኝነት ተነስተው ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኙት ፕ/ር ምትኩ በላቸው ወንጪ ተወልደው በቤልጅየም የህክምና ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ፤ አንቱ የተባሉ ምሁር፤ ሐኪምና ንፁሕ ኢትዮጵያዊ አግኝተናል። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን እንኳን ደስያለን። በቅርቡ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ያልሰማችሁ ስሙ፤ የሰማችሁ አሰሙ፤ አድናቆታችሁን ለግሷቸው። ከእርሳቸው ዓርእያነት ያለው ተግባር፤ ልምድ፤ ትምህርትና መልካም ስነምግባር እንማር። እንደ ፕ/ር ምትኩ ሰብአዊነትን የተላበሰ ኢትዮጵያዊ ምሁር በዚህ ጊዜ ማግኘት በመቻሉ ሁላችንንም ደስ ሊለን ይገባል። እንዲህ ተምረው የሚአስተምሩ ምሁራንን እንዲአበዛልን ፈጣሪ ይርዳን።

ፕ/ር ምትኩ ወደ ወንጪ ተመልሰው ለህብረተሰቡ የለገሱትን ግብረገብነት የተላበሰ ስነምግባር ስናይ ኢትዮጵያ በትቂት ዘረኞች እና ጎጠኞች የማትፈርስ እንደሆነች እንረዳለን። እርሳቸውን የመሰሉ በሽህ የሚቆጠሩ የተማሩ ኢትዮጵያዊያን በሃገርና በውጭ ስላሉ መንግሥት ሁኔታዎችን በማመቻቸት በእውቀታቸው፤ በጉልበታቸውና በንብረታቸው ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይታደጉ ዘንድ እንዲደግፏቸውና እንዲአበረታቷቸው እንመክራለን። ፕ/ር ምትኩን የመሰሉ ሰዎች ካለፉ በኋላ ገድላቸውን ማውራት ከታሪክነት ባለፈ ብዙ ጠቀሜታ አይኖረውም፡፡ ፀሐይ ሳለ እሩጥ አባት ሳለ አጊጥ ነውና ፕ/ር ምትኩን በሕይወት ሳሉ እናጊጥባቸው። ለአሁኑ በዚህ ዘመን እንዲህ ዓይነት እንቁ፤ ሰብአዊና ምስጉኑን ኢዮጵያዊ ሐኪም ፕ/ር ምትኩን የሰጠችን ወንጪን ከልብ እናመሰግናለን። ፈጣሪ ዕድሜና ጤና ሰጧቸው ይበልጥ ሕዝባቸውን እንዲአገለግሉ እየለመንሁ ቃላት መግለጽ የማይቻለው ምስጋናዬ ለደጉ ፕ/ር ምትኩ ይድረስልኝ። ከእረኝነት ወደ ዓለም አቀፍ ሐኪምነት ባድጉት ኢትይጵያዊ ፕ/ር ምትኩ ስነምግባር የኮራው ኢትዮጵያዊ፤

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,864FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here