- Advertisement -
ለተከበርከው የትግራይ ህዝብ
ለተከበራችሁ የኢትዮጵያ ብሄሮችና ብሄረሰቦች
ትግራይ ሪፐብሊካን ፓርቲ በትግራይ ህዝብ ላይ በተደራጁ የህወሓት አመራሮች ሳቢያ እየደረሰበት ያለውን ግፍና በደል ለመቃወም አስፈላጊ በሆነ መንገድ ሁሉ የነፃነት ትግል ለማካሄድ በአውሮፓ፣ በአውስትራሊያና በሰሜን አሜሪካ በሚገኙ ተጋሩ ኢትዮጵያውያን አማካኝነት እኤ.ኢ ግንቦት 14/2010 ዓም ተቋቁሞ እስከሁን ድረስ መሰረታዊ የፖለቲካ ስራና የህቡእ የአደረጃጀት ተግባር ሲያከናውን ቆይቶ ባለፈው ሳምንት አንደኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ሲያከብር በስራ አስፈፃሚው ኮሚቴው የፓርው ህልውናና አጀንዳ ደረጃ በደረጃ ለህዝባችን ግልፅ ለማድረግ ውሳኔ ተሰጥቶበታል።
_____
በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ክፍለ-ሐገር ትክክለኛ ሥሙ”ትግሬ” እንጂ “ትግራይ” አይደለም፤”ትግራይ”ፖለቲካዊ ሥያሜ ነው።የመጠሪያውም ሥያሜ መነሻ ሰበብ በትግሬ ውስጥ ለመከፋፈል የአርባ አራት ዓመታት የ”ትግረ” ማንነት እንደሌለ ለማሳየትና ሌላውን ኢትዮጵያዊ ዜጋ ተመልካች አድርጎ:-በበላይነት”ትግራይ”ን ለማስቀጠል የሚደረግ መሰሪ በራሳቸው የትግሬ ልጆች ውስጥ የዘረኛነት ደዌ ሆኗል :-ማንነትን የማወናበድ ዕብድነት ነው።
ዛሬ ዛሬማ”ትግሬ”ብሎ የሚጠራ የለም፤ወቸገል ዜናዊ የዘራው አረም እንዲህ በቀላሉ የማይጠፋው(የፋሺሽት-ወያኔዎች ከጣሊያን-ፋሺሽቶች) የወረሱት ነው፤በቀላሉ አይጠፋም።ምክንያቱም በሁሉም ዘርፍ ነው ያረከሰውና።እነዚህ የረከሱት ነገሮች፣ተራራ አልቀረም፣ሕፃናትን ድራሻቸውን ማጥፋት፣ ብሔራቸውን በግድ ማስለወጥ ቤተሰብን መበተንም ዱካን ከማጥፋት አይተናነስም።ከትግሬ በገልባጭ መኪና አጉሮ ተከዜ በረሃ ማስፈር፣የማይ ድሙን ውቅሮ አምጥቶ መበተን፤የአዲ ገብሩን ነዋሪዎች አፍናቅሎ ለፅምብላ ትግሬዎች መንደሮችን መሸለም ስንቱ ይወራል!!!ያም ሆነ ይህ”ትግሬ”ን “ትግራይ” የማይባለው ሰብ-ስብስብ ስለሆነና “ትግረ”ንም የማያካትት በመሆኑ ብቻ ነው።