በዳምጠው ተሰማ ደነቀ
ሰኔ 19 2012 ዓ ም
ያች ያፍላጦስ ሃገር
የፈላስፋ ምናብ
በከበረው ውሸት-አስታርቆ ያነጻት
በነፍስ ክፋይ ተረክ
መሪ አበጅቶ ጠባቂ አቁሞ
ላይጠረቄው መሻት -መንገድ ያጸናባት
ያፍላጦስ ሃገር ውስጥ ሀገሬን ጠየኳት
ውሸትሽ ምነድነው?
ኗሪሽ የማያውቀው፡፡
የጸነስሽው ምናብ
ስለኛ በማሰብ፡፡
በመርህ ደረጃ ውሸት ጸያፍ ነው፤ በየትኛውም ማህበረሰብ የሚነቀፍ፡፡ ሆኖም ከውሸትም ውሸት አለ፤ አንዱ የከበረ ሌላው ያልከበረ፡፡ ያልከበረ ውሸት ተዋርዶ ያዋርዳል፡፡ ውሽት መናገር ስህተትነትም ይኖረዋል፤ ይህም አፍራሽ ውሸት (bad lie) ነው፡፡ የግሪኩ ፈላስፋ አፍላጦስ (ፕሌቶ) በግሪክ ማህበረሰብ የፖለቲካ ስርዓት ስኬታማነት የሚበጅ ቅዱስ (ክቡር) ውሸት አስፈላጊ ነው፤ ለሪፐብሊኩ ጽኑ መሰረት ይሆናል የሚለው ተዋስዖው በየትኛውም አለም የፖለቲካ ተዋስዖ ገዢ ሃሳብ ነው፡፡ ከላይ በግጥም እንደተጠቆመው የከበረ ውሸት እንዲኖር መሻት ደግ ነው፡፡ ማንም ሰው ሃገሩን የከበረ ውሸት አለሽ ወይ ሲል ቢጠይቅ በጎ ነው፡፡
ሙሉውን ጽሁፍ በፒ ዲ ኤፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በጽሁፉ ላይ የቀረቡትን የግርጌ ማስታወሻወች አቀራረ ለመጠበቅ ሲባል ይሄን ጽሁፍ በፒዲ ኤፍ ፋይል ቀርቧል፡፡ ከላይ የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ፡፡