spot_img
Saturday, April 13, 2024
Homeአበይት ዜናበሰሜን አሜሪካ ፤ አውሮፓና አውስትራሊያ የሚገኙ የዐማራ ሲቪክ ድርጅቶች የጋራ መግለጫ

በሰሜን አሜሪካ ፤ አውሮፓና አውስትራሊያ የሚገኙ የዐማራ ሲቪክ ድርጅቶች የጋራ መግለጫ

 ሰኔ 30, 2012 ዓ.ም

በትህነግ/ኦነግ አገር ሽንሸና “ኦሮሞ ክልል” ተብሎ የሚጠራው የአገራችን ክፍል የንፁሀን ኢትዮጵያዊያን የሰቆቃ ምድር መሆኑ ሊበቃ ይገባል!!

በሰሜን አሜሪካ ፤ አውሮፓና አውስትራሊያ የምንገኝ የዐማራ ማኅበረሰቦች ፤ የሙያ ማበራት እንዲሁም የዐማራ ሲቪክ ማህበራት በአገራችን ኢትዮጵያ በስልጣን ጥመኞች ልፍያ ምክንያት በአሰቃቂ ሁኔታ እየረገፈ ባለው የንፁሃን ወገኖቻችን ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ኃዘን እንገልፃለን!! በዚህ ጥቃት ቤተሰቦቻችሁን ለተነጠቃችሁ፣ በማንነታችሁ ለተሳደዳችሁ ፤ የህይወት ዘመን ጥሪታችሁን ለተነጠቃችሁ ፤ በአጠቃላይ በደረሰባችሁ ማንነት ተኮር ጥቃት ጭንቀት  እና በመከራ ውስጥ ላላችሁ ወገኖቻችን መፅናናትን  እና ብርታትን እንመኛለን::

ከጠቅላይ ሚንስትሩ ባዕለ ሲመት ማግስት ጀምሮ በቡራዮ በጋሞ ተወላጆች ላይ የደረሰው ዘግናኝ ጭፍጨፋ፣ በጉጂ ዞን በጌዲዮ ተወላጆች ላይ የደረሰው አስደንጋጭ መፈናቀል እና ጉዳዩን ህዝብ እንዳያውቀው የማፈን ሙከራ ፣ በወለጋ እና አካባቢው ንዋሪዎች ላይ  ሁለት አመታት ያስቆጠረው የጦርነት ሰቆቃ ፣ በዐማራ ሴት የዩንቨርስቲ ተማሪዎች  ላይ የተደረገው ጠለፋ እና እስካሁን ደብዛቸው ያለመታወቅ  ፣ የአቶ ጀዋር መሃመድንድርሱልኝ ተከብቢያለሁጥሪ  ተከትሎ በንፁሃን ላይ የደረሰው አስቃቂ ጭፍጨፋ እነዚህ እና በርካታ በተደራጀ እና የመንግስትን መዋቅር ጭምር  በመጠቀም የሚፈፀሙ በርካታ ወንጅሎች / አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡ ወዲህ ያለፉትን ሁለት አመት ኦሮሞ ክልልበተባለው የአገራችን ክፍል በንፁሃን ላይ የተፈፀሙ ማንነት ተኮር ጭፍጨፋዎች እና መፈናቀሎች  አካባቢውን የንፁሃን ኢትዮጵያዊያን የሰቆቃ ምድር አድርጎታል:: 

የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በሴራው  አቀነባባሪዎች መካከል የከረመው የስልጣን ሽኩቻ ወደለየለት ጦርነት አድጎ በአገር ደህንነት፤ በንፁሃን ኢትዮጵያዊያን ህይወት እና ንብረት ላይ አደጋ ደቅኗል::  በአደባባይ በሞት ነጋሪ ሚዲያዎቻቸው ጭምር ‘ውጡና ንፁሃንን ጨፍጭፉ፤ የኢትዮጵያ የሆነውን ሁሉ አፍርሱ’ የሚል የባዕድ  ጥሪያቸውን ተከትሎ ንፁሃን ወገኖቻችን በዚህ ዘመን በሰው ላይ ይፈፀማል ተብሎ ለማሰብ በሚከብድ ሁኔታ ተገድለዋል ፤ በቁማቸው ተቃጥለዋል። 

በሰሜን አሜሪካ ፣ አውሮፓ  እና አውስትራሊያ በልዩ ልዩ የአደረጃጀት መልክ ተደራጅተን የምንቀሳቀስ የዐማራ ማህበራት በንፁሃን  ወገኖቻችን እና በአገራችን ላይ የታወጀውን የሞት ጥሪ በፅኑ እናወግዛለን። ይህ የመጨረሻው ጥቃት መፈፀም ከጀመረ ቀናትን ያስቆጠረ ቢሆንም በእኛ በኩል በዚህ ሰዓት የሚወጡ መግልጫዎች እና ጥሪዎች ጥንቃቄን እንደሚጠይቁ በመገንዘብ  ከቀን ቀን መንግስት ጥቃቱን ያስታግሳል በሚል በትግስት ቆይተናል። ይሁንና ከሚደርሱን ሪፖርቶች እንደተገነዘብነው በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ የፀጥታ አካላት ፤ የከተማ ከንቲባዎች ፤ የወረዳ እና የቀበሌ አስተዳዳሪዎች አገርን ከማረጋጋት እና የንፁሃንን ህይወት ከመጠብቅ ኃላፊነታቸው በተቃራኒ የብሔር  እና ሐይማኖት ማንነት ተኮር ጥቃቱ ዘመቻ ተሳታፊ ሆነው ለገዳዯች እና አስገዳዯች ሽፋን እየሰጡ መሆኑን መረጃዎች አረጋግጠውልናል። በመሆኑም ከዚህ በታች የሚዘረዘሩ ነጥቦችን ለሚመለከተው አካል ሁሉ እንዲደርስ በአደባባይ ጥሪ ለማቅረብ ተገደናል:-

1.     የዶ/ር አብይ አስተዳደር ከአሁን ቀደም የተፈፀሙትን ጨምሮ ከዚህ በሗላም በንፁሃን ላይ ለሚደርሰው የብሔር  እና ሐይማኖት ማንነት ተኮር ጥቃት ከሁሉም ቀዳሚው ተጠያቂ መንግስታቸው መሆኑን ተገንዝበው በአስቸኳይ የዜጎችን እና የአገርን ደህንነት የመጠበቅ ቀዳሚ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እናሳስባለን።  

2.     መንግስት የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ገዳዯች ጨምሮ በአዲስ አበባ እና “ኦሮሞ ክልል” ተብሎ በሚጠራው  የአገራችን ክፍል በንፁሃን ላይ ግድያ ፣ ዝርፊያ የንብረት ውድመት እና አጠቃላይ ዘር እና ማንነት ተኮር ጥቃት ያደረሱ ወንጀለኞችን ለህግ እንዲያቀርብ እንጠይቃለን።

3.     የብሔር  እና ሐይማኖት ተኮር ጭፍጨፋው የህይወት ፣ የአካል እና ንብረት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን  ተገቢው ካሳ እና የመልሶ ማቋቋም ስራ እንዲሰራ እንጠይቃለን። 

4.     በተለይም ዐማራን፣ጉራጌ እና ሌሎች ብሔሮችን እንዲሁም ክርስቲያን ኦሮሞወችን ትኩረት አድርጎ የተፈፀመው የብሔር  እና ሐይማኖት ማንነት ለይቶ ጭፍጨፋ በገለልተኛ አለም አቀፍ አጣሪ ቡድን እንዲጣራ ጥሪያችንን እናቀርባለን።  ለዚህም መሳካት የአለም አቀፋን ማህበረሰብ የመቀስቀስ እና የመወትወት ስራችን አጠናክረን እንቀጥላለን።

5.     የአሸባሪ እና የዘር ፍጅት ጥሪ አቅራቢዎችን በህግ ቁጥጥር ስር መዋል ሚዛን ለመጠበቅ በሚል መንግስታዊ የፖለቲካ ድራማ ለእስር እና እንግልት እየተዳረጉ ያሉ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች፣  የአገር ጠበቃ ግለሰቦች በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱ እንጠይቃለን።

6.     የአለም አቀፋ ማህበረሰብ በአገራችን ኢትዮጵያ እየሆነ ያለው ትንናት እንዳይደገም ብሎ ያወገዘው የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ አይነት የዘር ፍጅት መሆኑን ተገንዝቦ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

7.  በውጭ አገራት ተቀምጠው በወገናችን ላይ በልዩ ልዩ መንገድ የሞት ነጋሪት የሚጎስሙትን ፣ኢትዮጵያ እና  ኢትዮጵያዊ የሆነውን ሁሉ አፍርሱ እያሉ የሚለፍፉትን  ባዕዳን በየሚኖሩበት አገር ህግ ተጠያቂ ለማድረግ  የምናደርገውን ጥረት አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊን አንዲቀለቀሉን፣ መረጃ ያላቸው ሁሉ መረጃቸውን በማጋራት እንዲተባበሩን ጥሪያችንን እናቀርባለን!! 

አገራችን ኢትዮጵያን  እና ህዝቧን ፈጣሪ ይጠብቅ!! 

1.     ሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት        
2.     ሞገድ ዐማራ ቀስቃሾች ስብስብ  
3.     ሲያትል የዐማራ ማኅበር     
4.     ነፃ የአማራ ማህበር በቨርጂንያ    
5.     የአማራ ህብረተሰብ ቅርሰ በሚኒሶታ        
6.     የአማራ ማህበር በሎስ አንጀለስ  
7.     የአማራ ማህበር በካሊፎርኒያ      
8.     አማራ ማህበር በኔቫዳ    
9.     የአማራ ማህበር በአሜሪካ
10. የዐማራ ማኅበር አውስትራሊያ
11. የአማራ ማህበር በካናዳ ለሰብአዊ መብት
12. የአማራ ማህበር -ኮሎራዶ 
13. የአማራ ማህበር በዳላሰ
14. የአማራ ማህበር በጆርጂያ
15. የአማራ ባለሙያዎች ማህበር (አምባ) 
16. የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ማኅበራት ምክር ቤት በአውስትራሊያ
17. ደጀን-የአማራ ማህበራት መድረክ  በአውሮፓ (ደ-አማራ)

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here