spot_img
Monday, June 24, 2024
Homeአበይት ዜናለኢትዮጵያውያን በሙሉ ወገን አድን ልዩ ጥሪ: ስለ ታገቱት ሴቶች ልጆቻችን ዝም አንልም፡፡

ለኢትዮጵያውያን በሙሉ ወገን አድን ልዩ ጥሪ: ስለ ታገቱት ሴቶች ልጆቻችን ዝም አንልም፡፡

ለኢትዮጵያውያን በሙሉ ወገን አድን ልዩ ጥሪ: ስለ ታገቱት ሴቶች ልጆቻችን ዝም አንልም፡፡

 አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት ሰሞኑን ድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን አስከትሎ በአገራችን ኢትዮጵያ በተከሰተው አሳዛኝና አሰቃቂ ድርጊት ውድ ህይወታቸውን ላጡት በግፍ ስልተገደሉትና ስለተጨፈጨፉት ኢትዮጵያውያን ወገኖችች በሞላ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን፤ ድርጊቱንም አጥብቀን እናወግዛለን፣ ወንጀሎኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ጸርና ጠንቅ የሆነውን የወያኔን የጎሳ ክልል ስርአት ለማስወገድ የተደረገው የለውጥ ትግል ተጠልፎና ተቀልብሶ፣ አንዱን ጸረ ኢትዮጵያ የጎሳ መንግስት (የወያኔ/ኢህደግ)በሌላ የጎሳ መንግስት (ኦነግ/ብልጽገና) በመተካት ህዝብን ለእልቂት የሚዳርገን አጥፊ ነባራዊ እውነታ ላይ እንድንገኝ ሆነናል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍለ ከተማዎች፣ በአዲስ አበባ፣ በሀረር፣ በሻሸመኔ፣ በድሬዳዋ፣ በአርሲ ነገሌ በዝዋይ በባሌ ወዘተ፤ በማንነታቸው ምክንያት ብቻ እየተለዩ በተለይ በአማራው ህዝብ ላይ ካለፈው በቀጠለ ትኩረት እንዲሁም ሌሎች ኦሮሞ ባልሆኑ ማህበረሰቦች ላይ በታጠቁ የኦሮሞ ጽንፈኛ ሀይሎች የዘር ማጥፍትና ማጥራት ወንጀል ተካሂዶል አሁንም እንደ ቀጠለ ነው፡፡

በአንድ አገር ውስጥ በሚፈጠር ጦርነት ሆነ በግጭት ወቅት የመከራና የችግሩ ገፈት ቀማሽ ተጠቂዎች በአብዘሀኛው ሴቶችና ልጆች ናቸው፡፡ ዛሪም እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሴቶች በገዛ አገራቸው ተሰደዋል፣ ተፈናቅለዋል፣ በአሰቃቂ ሁኔታ ተግድለዋል። ነፈሰ ጡሮችና ህጻናት ቤታቸው በላያቸው ላይ ፈርሶና ተቃጥሎ መንገድ ላይ ወድቀዋል፤ በርካታ ሴቶች ተደፍረዋል፣ ጭካኔ ለተሞላበ ኢሰባአዊ ጥቃት ተዳርገዋል። አማራ በመሆናቸው ብቻ በደንቢ ደሎ፣ ወለጋ ከፈለ ሀገር በኦሮሞ ታጣቂ ወንበዴዎች ለብዙ ወራት የታገቱት ወጣት ሴቶችን ለማስፍታት የአብይ አህመድ አስተዳደር ጉልበት የለውም ወይም ጆሮ ዳባ በማለት በተዘዋዋሪ ያስጠቃል። ለሚፈልገውና በሚፈልግበት ጊዜ ግን ወንጀለኞችን ያዝኩ ይላል፣ የታገቱት ወጣት ሴቶች የት እንዳሉ ማወቅም ሆነ ወንጀለኞችን መያዝ ግን ተሰኖታል።  ወንጀለኞች እንድ ልብ ህዝብን ሲገድሉ፣ ስያሸብሩና ሲዘርፉ አይቶ እንዳላየ የሚያልፈው የአብይ አህመድ አስተዳደር፣ እውነትኛ የህዝብ ወገን የሆኑትን አገር ወዳድ የፖሊቲካ መሪዎችና ታጋዮችን፣ ያለምንም ወንጀል በጅምላ ማሰርና ማንገላታት ላይ ግን በሰፊው በብርቱ ተሰማርቶል።

ስለዚህም የአለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት ስለ ኢትዮጵያውን ወገኖቻችን በአጠቃላይ፣ በተለይ አማራ በመሆናችው ስለ ታገቱት ሴቶችን ልጆቻችን ዝም አንልም እንላለን፡፡

በማህበረሰብ መቃወስ፣ በህዝብ መፈናቀል፣ ሞትና ትርምስ ለፖለቲካ ትርፍ የሚጠቀሙ መንግስትም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ የፖለቲካ ሃይሎች በስውርም በግልጽም የጥፋት ተባብሪ ስለሆኑ ለሚደርሰውም ጉዳት ተጠያቂ ያደርጋቸዋል፣ ከህዝብ እልቂትና ስቃይ በተጨማሪ የኢትዮጵያ አገራዊ ሉኦላዊነትና አንድነትን የሚያሰጋ አደጋ ሊከሰት የሚያስችል አጋጣሚን ይፈጥራልና፡፡ የአብይ አህመድ መንግስት ይህን ውስብስብ ችግር ለመፍታትም ሆነ የዜጎችን ደህንነት፣ የአገርን ሰላም ለማስጠበቅ አሁን በያዘው መንገድ አለመቻሉን ሆነ አለመፈለጉን፣ (ከከንቱ ወዳሴና ሃሳዊ ጮሌነት ባሻገር) በተድጋጋሚ ላልፉት ሁለት አመታት አሳይቶል፡፡ ይህን አለመገንዘብና ተገቢውን አለማድረግ በተለይ ለአገርና ወገን የሚያስቡ ምሁራን፣ የሰብዊ መብት ተቆርቆሪዎችና የፖለቲካ ደርጀቶች፣ በአሁኑ ወቅት በእውነት ጎን ባለመቆማቸው በህዝብ ላይ ለሚደርሰው በደልና ሞት ታሪክ ወደፊት ተጠያቂ ያደርጋቸዋል።

ጽንፋዊ ልዩነትንና ጥላቻን ባነገቡ የኦሮሞ የጎሳ ሃይሎች ሰላማዊ ህዝብ ለጥቃት ሲዳረግ መንግስት ነኝ የሚል ሃይል በሰበብ ባስባቡ ማስጠቃት እንጂ አስፈላጊውን ጥበቃ ስለማያደርግ በተደጋጋሚ እንደታየው፤የኢትዮጵያ ህዝብ ባጠቃላይ፣ የአማራ ህዝብ በተለይ ለዘመናት ባካበትው የአብሮነት ጥበብ በመጠቀም የራሱን ደህንነት የመጠበቅና ኢትዮጵያን በትንንሽ የጎሳ አገሮች ለመበታተን፣ እንዲሁም ህዘቦንም በቁጥር እንዲቀነስ ለሚፈልጉ ሀይሎች ሰለባ ላለመሆን አስፈላጊውን ማድረግ ታሪካዊ ኢትዮጵያዊና ሰብአዊ ሃላፊነት አለብን። ስለዚህም የአለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት ህዝባችንን ከበለጠ እልቂትና የእርስ በርስ ግጭት ለማዳን በጊዜ አሰፈላጊውን ትብብር ሁሉ እንዳረግ ዘንድ ወገናዊ ጥሪ ለአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እናቃርባለን።

  1. ዛሪ ህዝብን ለዚህ ሰቆቃ የዳረገው ዋናው የችግሩ መንሳኤ የወያኔ/ኦነግ/ኢህድግ/ብልጽገና ድርጅቶች የታነጹበትና የሚመሩበት ጸረ ኢትዮጵያ ህገ መንግስትና ፖሊሲ ነው፡፡ ስለዚህም ለዘለቄታው ይህን የጎሳ ክልል ስርአትና ህገ መንግስትን ኢትዮጵያዊነትን መሰረት ባደረገ ህገ መንግስት በመተካት ህዝብን በአንድነት፣ በእኩልነት በፍትህ የሚያስተዳድር መንግስት መመስረት አገርንና ህዝብን ከጥፋት ያድናል፣ ይህ ላጭር ጊዜ ሆነ ለረጅም ጊዜ መፍትሄ ይሆናል። ይህ እስኪሆን ግን የጎሳ መለያ ሰባዊነትን ሰለሚያጠፋና ጭካኔን ስለሚያጠናክር የጎሳ መታወቂያን ማስወገድ ወሳኝ ቁልፍ ተግባራዊ ትግል ነው ብለን እናማናለን፤ ከጎሳዊ ወደ አገራዊና ህዝባዊ መንግስት መሸጋገር ፖለቲካዊ ትክክልኝነት ብቻ ሳይሆን በጎሳ ማንነት ምክንያት ሚከሰትውን ጥፋትና እልቂት ማስወገድና መከላከል ስለሚይስችል ይህን አማራጭ ተግባራዊ ለማድረግ በአጽኖት እንዲታሰብበት ለሚመልከታቸው ሁሉ ጥሪ እናደርጋለን።
  • ለብዙ ወራት የአማራ ወጣት ተማሪዎች ልጆቻችን በኦሮሞ አካባቢ በታጠቁ ዘረኛ ሀይሎች መታፈናቸው ያስቆጣን መሆኑን እያሳወቅን በአስቸኮይ እንዲለቀቁ አጥብቀን እንጠይቃለን። ሰለልጆቻችን ደህንነት አጥጋቢ ምላሽ እስኪገኝ በአብይ መንግስትና በተባብሪውች ላይ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊና ዲፕሎማሳዊ ማእቀብ እንዲደርግ በድጋሚ የትብብር ጥሪ እናቀርባለን። ለሚደረሰው የአእምሮና የአካል ጉዳት፣ጥፋትና ቀውስ መንግስትም ሆነ ሌሎች ወንጅለኞችን ተጣያቂ እናደርጋለን።  
  • ህዝቡን፣ ማሳደድ፣ ማዋከብ፣ ማሰር እንዲቆምና በግፍ የታፈኑና በጅምላ የታሰሩት ንፁሀን ዜጎች፣ የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎችና አባላት፣ እነ ወ/ሮ አስቴር ስዩም፣ አቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት፣ አቶ ልደቱ አያሌውና ሌሎች በርካት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ኖዋሪዎችን ባስቸኮይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡ በአንጻሩ በሰላምዊ ህዝብ ላይ በደል ያሚያደርሱትን ወንጀለኞች፣ ኢትዮጵያዊ ቅርሶችን በማውደምና በጭፍጨፋ ተግባር በቀጥታ ሆነ በተዘዋሪ የታሳተፉትን የመከላከያና የልዩ ሃይልን፣ እንዲሁም ሌሎች የታጠቁ ጸረ ህዝብ ሃይሎችን በህግ እንዲጠየቁ እናሳስባለን።
  • ጥያቄዎቻችን በአግባቡና በአስቸኳይ እስኪመለሱ ማንኛውንም የሰላማዊ ትግል በመጠቀም በመንግስትና በሚመለከታቸው ተባብሪውች፣ የፖለቲካና  የንግድ ተቆማት ላይ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚና፤ ዲፕሎማሳዊ ማቀብና ዓድማ እንዲደረግ ከወዲሁ የትብብር ጥሪያችንነ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ እናስተላለፋለን።
  • በአጠቃላይ በኢትዮጵያውያን ሴቶች ላይ የሚደርሰውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ እንዲሁም የጾታ ጭቆናንና ጥቃትን አጥብቀን እናወግዛለን፤ በተለይም በአማራ ሴቶች ላይ በየጊዜው ከሚደርሰው ግፍና መከራ ተጨማሪ ለልዩ የዘር ማጥፋት ጥቃት ሰለባ ሆነዋል፣ እንዳይወልዱ የማምከን ወንጀል ተካሂዶባቸዋል። የኢትዮጵያ እናቶች መከርና ለቅሶ ይቁም እያለን በሴትነታቸው ምክንያት የሚደርሰባቸውን ጉዳት ለማስወገድ፣ መብታቸውን ለማስጠበቅ ማደራጀትና ማጠናከር አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት ወቅቱ የሚጠይቀው አስፈላጊ የጋራ ተግባር ነው እንላለን።

የጎሳ ክልል ፖለቲካ ከኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ይነሳ

ኢትዮጵያ በጀግንነት ተከብራ ለዘላለም ትኖራለች!!

አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት

ሀምሌ 2012

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here