spot_img
Wednesday, March 22, 2023
Homeአበይት ዜናዘር-ፍጅት ወንጀለኞችን ለሕግ ለማቅረብ ትብብር ጥሪ!

ዘር-ፍጅት ወንጀለኞችን ለሕግ ለማቅረብ ትብብር ጥሪ!

- Advertisement -

በኢትዮጵያ የዘርፍጅትመከላከያማኅበር (ኢዘመማ)
ሓምሌ 22 2012 ዓ ም

በሃገራችን  ብሔርን መሠረት ያደረገ የፖለቲካ አገዛዝ ተግባራዊ ከሆነበት ከ1983 ዓም ጀምሮ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በ ብሔር ተለያይቶ እንዲፉጅ መንግሥት መርዘኛ ተንኮል ሲፈጸም ቆይቷል ። የኢትዮጵያን መዐከላዊ መንግሥት ላለፉት 27 አመታት ተቆጣጥሮ የቆየው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር (ሕወሃት) ሕዝባችን ለዘመናት ገንብቶት የኖረውን ሕብረ ብሄራዊ አንድነቱን በማላላትና እርስ በእርስ በጠላትነት እንዲተያይ በማድረግ ዛሬ ለደረስንበት አስከፊ ብሄራዊ ቀውስ ዳርጎናል ።

ሕወሃት በዋናነት፣ ሌሎች ተገንጣይ ኃሃይሎች በተላላኪነት፣ በብዙ ሺህ ለሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ሞት፣ መፈናቀልና ስደት ምክንያት ሆነዋል ። በተለይም የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በአርባጉጉ፣ በወተርና በበደኖ ያካሄደው አንድን  ብሔር መሠረት ያደረገ ዘግናኝ ጭፍጨፉ የሚዘነጋ አይደለም ። እነዚህ ጽንፈኞች የአማራን ተወላጆችና ክርስቲያኖችን በመነጠል ላደረሱት የጅምላ ጭፍጨፉ በተገቢው መንገድ አለመጠየቃቸው ከዛ በሗላ ለተከተሉት ተደጋጋሚ የዘር ጭፍጭፉዎች ምክንያት ሆኖ ቆይቷል ። 

በቅርቡም በአክራሪ የኦሮሞ ሃይሎች በሻሸመኔ፣ በዝዋይ፣ በባቱ፣ በአርሲ ነገሌና በጅማ ለደረሰው አማራንና ክርስቲያኖችን የለየ ጭፍጨፉ መሰረቱ፣ ለሚፈጸመው ተደጋጋሚ ወንጀል ተጠያቂ የሚሆን አካል አለመኖሩ የፈጠረው ክፍተት ለመሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም ። ከሁሉም በላይ የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ ያለበት መንግሥት ሃላፊነቱን በተገቢው መንገድ ለመወጣት አልቻለም ። በፊትም አሁንም በጸጥታ መዋቅሩ ያሉ ሃላፊዎች ለወንጀኞች ተባባሪ በሆኑ አካላት መሞላታችውን መንግሥት ባለመቆጣጠሩ ለደረሰው እልቂትና ውድመት ከተጠያቂነት አያመልጥም ።

ከዶር አብይ አህመድ ሹመት በኋላ በተደጋጋሚ ለተካሄደው በአማራና በክርስቲያኖች ላይ ለደረሰው ጭፍጨፉ ተጠያቂ መሆን የሚገባቸው፣ ሕዝብ በይፉ የሚያውቃቸው ግለሰቦችና አካላት ለሠሩት ወንጀል ሕግ ፊት ሲቀርቡ አልታየም ። መንግሥት ሕግን ለማስከበር ዳተኛ መሆኑ ሰሞኑን ለደረሰው፣ በአይነቱም በመጠኑም ከፉ እና አሰቃቂ ለሆነ፣ እልቂትና ውድመት አብቅቶናል ። እስካሁን የተፈጠረውን በዘር ላይ ያተኮረ እልቂት ከመደባሰስ አልፎ፣ የችግሩን ክብደት ቀርቶ መኖሩን እንኳን መንግሥት በገሃድ ለማዎቅ ፈቃደኝነት አያሳይም። ወደፊትም መንግሥት ወንጀለኞችን ይዞ ለፍርድ ያቀርባል ብሎ ለመገመት ያስቸግራል ።

በሃገራችን ከዚህ በሗላ ተመሳሳይ ማንነትን መሠረት ያደረገ ጭፍጨፉና ውድመት እንዳይከሰት፣ ወንጀለኞችና ተባባሪዎቻቸውን በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለመክሰስ እንቅስቃሴ ጀምረናል ። 

እንቅስቃሴያችን ሰብዓዊ መብትን ለማስጠበቅና ወንጀለኞችን ሕግ ፊት ለማቅረብ ከተሰማሩ ሃገር-አቀፍና አለም-አቀፍ ተቋማት ጋር በመደጋገፍና መረጃ በመለዋወጥ ለመሥራት ተዘጋጅቷል ። ይህ ጅማሮ ለውጤት እንዲበቃ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከምንዘረጋቸው መዋቅሮች ጋር በመሆን ሕጋዊነትን በተከተለ መንገድ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን ።

የሃገር ሰላምና የሕዝባችን ደህንነት እንዲጠበቅ የሚፈልጉ አካላት፣ የመንግሥት አመራሮች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣
የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶች ያላቸውን ማንኛውንም የተፈጸመውን ወንጀል የሚገልጽ መረጃ ወደ እኛ እንዲልኩልን
ፍትህ በሚሻው ወገኖቻችን ስም እንጠይቃለን ።
መርጃዎቹም:-

  1. የተቀረጹ የቪዲዮ ምስሎች
  2. ፎቶዎች
  3. የሰነድ ማስረጃዎች
  4. በድምጽ የተቀረጹ (ኦዲዎ) ማስረጃዎች
  5. ወንጀሉ ሲፈጸም ያዪ ፈቃደኛ ምስክሮች
  6. በማሕበራዊ ሚድያ በቀጥታ ስርጭት ጄኖሳይድ እንዲፉፉም ሲቀሰቅሱ የነበሩ ሚድያዎችና ግለሰቦች ከግዜ
    በኋላ ያጠፏቸው ጽሁፎችና ምስሎች።
    ከላይ የተጠቀሱትን እና ሌሎችም የወንጀል ድርጊቱን ሊያሳዩ ይችላሉ የምትሏቸውን ተጨባጭና ሕጋዊ መረጃዎች
    በቅርቡ በምናሳውቀው መንገድ እንድትልኩልን በአክብሮት እንጠይቃለን ።
    ፍትሕ በግፍ ለተጨፈጨፉ ወገኖች!

SAGE Executive Committee
sage.ethiopia@gmail.com
July 28, 2020

___________________________________

በፒ ዲ ኤፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,440FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

2 COMMENTS

  1. Under ዐብይ አህመድ እስካሁን ድረስ ለህዝብ ያሻገረውና የሠጠው ዴሞክራሲ ወይም ሠላም የለም!!! (ዘ ኢኮኖሚስት) – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

    አቢይ ብቻዉን ስለፈለገ ዴሞክራሲ አይመጣም፣ ግን ከትግራይ በስተቀር አንድ ለኢትዮጵያ እናትና ልጆች የመጣ ጉዳይ ቢኖር፣ እናትና ልጅ በገዛ ቤታቸው ተማምነው እንዲኖሩ የሆነ ይመስላል፣ ማለትም የአቢይ ካድሬ በየቤቱ እየገባ እናትና ልጅን አያናክስም ማለት የሆነ ይመስላል:: ህወሓት ግን ከተወለደበት ከዛሬ 45 ዓመታት ጀምሮ በየቤተሰብ መሃከል እየገባ መናከስንና መጠራጠርን ስላሰፈነ Globally በትግራይ ህብረተሰብ ውስጥ ህብረተሰባዊ የሆነን ኑሮ የሚመራ የለም:: ከዚህም በመነሳት የኢትዮጵያ እናቶች ከልጄ ጋራ በሰላም ተቃቅፌ ለመኖር ያበቃሄኝ አምላክ ተመስገን ማለት ያለባቸውና ከዚያም ቀጥሎ ለሌሎች ተስፋማ ለውጦች ሰላማዊ ትግላቸውን መቀጠል ያለባቸው ይመስለኛል:: Hostage ውስጥ የሚገኙት የትግራይ እናቶች ግን አሁንም፣ ለኔም እንደ ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን እናቶች ከልጄ ጋር በሰላምና ካለምንም መሰላለል የምኖርበትን ጊዜ አምጥልኝ ብሎ ከመፀለይ አልፎ አንዳችም መንቀሳቀስ እንኳን ለመሞከር የማይችሉበት ሁናቴ ውስጥ ስለሚገኙ የተሻለ ቀን ብቻ ያምጣ ከማለት ሌላ ምን አለ?
    ከዚያም በላይ ደግሞ ዴሞክራሲ እንዳይመጣ ከሚያውኩት ጉዳዮች አንዳንዶችን ለመጥቀስ ያህል: (ግን ደግሞ ዴሞክራሲ ሲባል ያ ማኒፑላቲቩ ነው ወይስ ሻል ያለ አለ)
    1. ከድሮውኑ የለውጡ አውጠንጣኞች ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ አስበዉለት ሳይሆን፣ ለውጡን ያቀነባበሩት ቻይናን ከአፍሪቃ ለማባረር ያሉት ዜቤ ነበርና፣ አሁን ችንጉርትን ተክሎ ድንችን ለምን ወደ ገበያ አታቀርቡም እንደመለት ነገርን ቢተውሳ፣
    2. የለውጡ አውጠንጣኞች የለውጡ ሃይሎችን ሲያስተቃቅፉ ከ1965 (ፈረንጅ) እስከ ዛሬይቱ እለት ድረስ በሕረዶ ቕተሎ ባህል ብቻ አድገው ያረጁን ሃይሎችን ሲከቱበት ሌላን በማሰብ እንጂ ዴሞክራሲን በማሰብ አልነበረምና፣ አሁን ከችንኩርት ተከላ እንዴት ተብሎ ነው ድንች ገበየ እንዲቀርብ የሚጠበቀው?
    3. የኖቤል ሽልማቱ ከጉቦነት ጋራ እንጂ ከሌላ ጉዳይ ጋራ የተያያዘ አልነበረምና ስለሱ ማውራቱን ብናቆም የተሻለ ይሆናል፣
    4. አፉን ከፍቶ የመርካቶ ኪስ አውላቂነትን ሲዋደቅ ከስልጣን የተከነበለው TPLF የያልበረደለት አይነት ጎረምሳ በጥባጭነትን በሚጫወትበት አካባቢ ዘንዳ ዴሞክራሲን መርሳትና ለዴሞክራሲ ከምብሓዲሽ ትግል መጀመር ሊያስፈልግ ነው፣
    5. የአምሓራ ሓሳድነትም እኔ ደደብ ነኝና፣ እኔ ካላስተዳደርኳችሁ የሓሳድነት ሚናን ከመጫወት በስተቀር ሌላ ቀና ተግባር አይታየኝም አዲስ አበባም ሰላም አታገኝም፣ ይሄንን እርኩስ ጠባዬን ግን ራሴን አሞኝቼ ሌላውንም አሞኘሁኝ ስል፣ ጭራች የማህተመ ጋንዲ ነው እላችኋለሁኝ ባዮች እስካሉ ጊዜ ድረስ ዴሞክራሲን ለሚቀጥለው 3000 (ሶስት ሺህ) አመታትም ልንረሳው እንችላለን::
    6. የተወሰኑ ኦሮሞ ሃይሎች በአንድ በኩል በብረት ሃገሪቱን ማመስና በሌላ በኩል ደግሞ ዴሞክራሲ ብሎ መጮህ ውጤቱ አሁን ያለውን ሁናቴ አናርኪን እንጂ ሌላን አያስከትልምና እንዴት ነው የአስተሳሰብ ጉዳይ?
    7. እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር እንጂ በየሃያላን መንግስታት ዘንዳ እየተጎነበሰ አንዳችም ነገር የሚጠብቅ ከሆነ መሰረታዊ ለውጥ የሚባል ነገር አይመጣም፣ ለምን ቢባል ሃያላን ሃይሎች ንጥረ ሃብትን እንጂ የሰው ልጅን ወደው አያውቁምና
    8. ለህዝባቸው የሚያስቡ ኢትዮጵያውያን ሃይሎች ምናልባት ካሉ፣ ውድድር ሲካሄድ በውድድሩ ዘንዳ መሸነፍም እንዳለ ግልፅ እንዲሆንላቸው ያስፈልጋል፣ ስለሆነም በስልጣን ላይ እስካሉ ጊዜ ድረስ በህዝባቸው የሚያስመሰግናቸው እንጂ የሚያስነውራቸው ተግባራት ዘንዳ መውደቅ የለባቸውም
    9. በእንዲህ ሲንቀሳቀሱ ከቆዩ በኋላም ስልጣንን በሚለቁበት ጊዜ ካለ ምንም ፍርሃት አገራቸው ውስጥ ሊኖሩ ስለሚችሉ፣ ወይኔ በኋላ ወዴት ልገባ ነው ከሚለው ፍርሃት ጋራ አይነታረኩም፣ እንደ ምሳሌ ወይዘሮ ክሊንተንን እንውሰድ፣ ለነገሩ ወይዘሮ ክሊንተን ኦባማንም ሆነ ትራምፕን ማሸነፍ ይገባት ነበረ፣ ኣይተ ክሊንተም፣ ለባለቤቱ ምርጫ ፉክክር በሚደረግበት ጊዜ ወደ ሃርለም ብቅ ብሎ “ጥቁሩ ፕረዚደንታችሁ እኔ ነኝ እንጂ ኦባማ አይደለም” ያለው ነገር በተወሰነ መልኩ ሃቅነት አለው፣ እስካሁን ጊዜ ድረስ እኔ ካየኋቸው የአሜሪካን ፕረዚደንቶች የተሻለው እሱ ነበርና ነው፣ እና እርሱ ከወረደበት ጊዜና ባለቤቱም ከትሸነፈችበት ጊዜ ድረስ ካለ ምንም ስጋት በገዛ አገራቸው ተዝናንተ ይኖራሉ እንጂ ምን ልሁን ወዴት ልሽሽ ከሚል ጣጣ ጋር አይናቆቱም፣ የኛዎቹም ጠቅላላ ሂይወታችሁን አገራችው ውስጥ አዝናንቶ ከሚያኖራችሁ መልካም ተግባራት ላይ ብቻ እንጂ ከሌላ ነገር ጋራ አለመያያዝ፣
    10. የምእራብ ጋዜጠኛ ምን ጊዜም የምእራቡን ፍላጎትን ነውና የሚያስጠብቀው፣ የምእራቡ ፍላጎት ደግሞ ንጥረ ሃብትን መበዝበዝና፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ህዝብ በረሃብ ሲቆላ የምእራቡ ጋዜጠኛ ግን በአመት አስር ጊዜ ቸቸለንና ሆኖሉሉ እየበረረ ፀሃይ መቆላትን ነው ቅድሚያ የሚሰጠው፣
    11. Unity in diversity

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here