spot_img
Friday, June 21, 2024
Homeነፃ አስተያየትበጀርመን ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መግለጫ

በጀርመን ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መግለጫ

በጀርመን ከባየር ግዛት ሙኒክ እና አካባቢው ከኖርድራይን ቬስትፋለን ግዛት ከኮሎን እና አካባቢው ከሄሰን ግዛት ፍራንክፈርት እና አካባቢው  ከሃምቡርግ ግዛት ሃምቡርግ ክተማ ለፍትህ የቆምን ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መግለጫ 

በጀርመን ከተደረጉት ተቃውሞዎች አንዱ(ፎቶ ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ)
በጀርመን ከተደረጉት ተቃውሞዎች አንዱ(ፎቶ ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ)

ሐምሌ 29 , 2012 ዓ.ም.

በመጀመሪያ በሃገራችን ኢትዮጵያ በዘራቸው እና በሃይማኖታቸው ተለይተው ጄኖሳይድ ለተፈጸመባቸው ወገኖቻችን ጥልቅ ሃዘናችንን እየገለጽን ቤተሰቦቻቸውም ድጋፋችን እንደማይለያቸው ልናረጋግጥ እንወዳለን። 

ከጀርባው ጉድ ባዘለ ለፖለቲካ ጥቅም በመንግስት አቀነባባሪነት በጀርመን በርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ለአንድ ግለሰብ ገንዘብ አዋጡ ከፍላችሁም አስታውቁን በሚል በኤምባሲው ደብዳቤ የተሰራጨውን የተረኝነት ስሜት የተጠናወተው አሳፋሪ እና ወገንተኛ አሰራር ማውገዝ ብቻ ሳይሆን እንቃወመዋለን።

ኤምባሲው የሚያዘው መንግስት በኢትዮጵያ የተፈጸመውን ዘር ማጥፋት ለመሸሸግ ያሰራቸውንም ንጹሃን የፖለቲካ መሪዎችን ከወንጀለኞች ጀኖሳይድ ቀስቃሾች እና መሪዎች ጋር በመወንጀል ማሰሩ ብቻ ሳይሆን

ኤምባሲው በኢትዮጵያ በኦሮሞ ፖለቲካ እስላም አክራሪዎች የተፈጸመውን ጀኖሳይድ እንዲሸፈን አቅጣጫ ለማስለወጥ የተለያዩ ዝግጅቶችን በመፍጠር ኢትዮጵያውያንን ለማዘናጋት እና ለመከፋፈል ሲሯሯጥ ይታያል። 

ይህ የመሸሸግ ሙከራ የትም አያደርስም። ይህን ጀኖሳይድ ከማጋለጥ ወደሁዋላ እንደማንል ለማስታወቅ እንወዳለን። ስለዚህም የግለሰብ መዋጮ የአባይ ግድብ ድጋፍ ሰልፍ የምናምን ዝግጅት እያላችሁ የተፈጸመውን ጀኖሳይድ ዘርማጥፋት ለማዘናጋት አትሞክሩ እንላለን።

የስልክ ጥሪ የማትመልሱ የኢትዮጵያን ህዝብ የውጭ ምንዛሪ እያከሰራችሁ ያለ በቂ አገልግሎት ከቁጥር በላይ በኢትዮጵያ ኤምባሲ እና በቆንስላ ሰፍራችሁ በእናንተ የሚወድመው የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ሳያንስ በተጨማሪ የጥቂት ስነ አደሮችን ሆድ በመሙላት እና በውስኪ በማስከር የሃገር ሃብትን ከስነአደሮቻችሁ ጋር ማውደማችሁን አቁሙ እንላለን።

ኤምባሲው በየጊዜው በጀርመንም ሆነ በአውሮፓ የጠረንፋቸውን የኢትዮጵያውያን ተወካዮች ተብዬዎች የማናውቃቸው መሆኑን እና በምንኖርበት ጀርመን አገር ለወካይም ሆነ ለተወካይ ነጻ ምርጫ የሚባል ነገር እንዳለ ባለማወቅ ዴሞክራሲን ሳይኖሩበት ሳያውቁት በአብዮታዊ ዴሞክራሲ እና በካድሬ አመራር ሊዘውሩን የሚሞክሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ቆንስላ አባሎች መሳታቸውን እንዲያውቁት እያልን  የምንኖረው በትክክለኛ ዴሞክራሲ በሰፈነባት ጀርመን አገር መሆኑን የኢትዮጵያ መንግስት እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲገነዘበው እንፈልጋለን።  

ከዚህም ተያይዞ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት ለተፈጸመው ዘርማጥፋት የጄኖሳይድ ዋና ቀስቃሾች የጥላቻ ንግግር ተዋያንኖች እንደ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለዚህ ለደረሰው ጀኖሳይድ ዘር ማጥፋት ዋና ተጠያቂ ሲሆኑ 

አቶ ሽመልስ አብዲሳን በብብት አቅፎ በ አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ግብረ አበሮቻቸው በተዘራው ጥላቻ ሰለባ የሆኑ የጀኖሳይድ ወንጀል የፈጸሙ ወጣቶችን ብቻ ለፍርድ ማቅረቡ ተአማኒነት የሚያሳጣ ነው። 

ስለዚህም የዚህ ዘርማጥፋት ጀኖሳይድ ቀስቃሾች እና አስፈጻሚዎችም በህግ እንዲጠየቁ እንጠይቃለን። 

ወራጅ የለም በማለት አስጨፍጫፊ እና ጨፍጫፊዎችን ያበረታቱ እንደ 

አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ ያሉ ለፍርድ ይቅረቡ።

አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳን በአለም አቀፍ ህግ እንፋረዳለን። 

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በሚያስተዳድሩት ክልል የመንግስት የአስተዳደር አካላት እና  የጸጥታ ሃይሎች ለህዝቡ እንዳይደርሱ በጥፋቱም በመተባበራቸውም  ከነተባባሪዎቻቸው እና አስተባባሪዎቻቸው አንዱ ዋና ተጠያቂ ናቸው። 

አቶ ሽመልስ አብዲሳን በአለም አቀፍ ህግ እንፋረዳለን። 

በሃሰት የተወነጀሉ የተቀናቃኝ ፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎች እና ፖለቲከኞችን በተመለከተ በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን። 

አቶ እስክንደር ነጋ በተለይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጦርነት እንከፍታለን በሚል ማስጠንቂያ ከተሰነዘረበት ጀምሮ የተለያዩ ስብሰባዎቹም ሆነ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት በመንግስት አካላት በግልጽ ሲስተጉዋጎልባቸው አለም አቀፍ የዜና አውታሮች እና ድርጅቶች በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤምባሲዎችም የታዘቡት ነው። 

በዚህ ባለማብቃት በአቶ ታከለ ኡማ የተደራጁ ሽብርተኛ ሁከት ፈጣሪዎች ጋዜጣዊ መግለጫውን ሲረብሹ አለም ታዝቦዋል። ከፍተኛ የመንግስት አመራሮችም የአቶ እስክንድር ነጋ ስብእናን ለመንካት ባዶ የሆነ ሙከራ አድርገዋል። 

አቶ እስክንድር ከታሰሩም በሁዋላ በአቃቤ ህጉዋ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ህገወጥ በሆነ መንገድ በአቃቤ ህጉዋ በብዙሃን መገናኛ አቶ እስክንደር ነጋን ወንጀለኛ አድርጎ የመፈረጅ ለደረሰው ጥፋት ተጠያቂ የማድረግ የሃሰት ውንጀላ የህግ አካሄዱን ተአማኒነት መሰረት ያሳጣ የፖለቲካ በቀል እናወግዛለን።

በኢትዮጵያ በዘር ማጥፋት ጀኖሳይድ ተጠያቂውን እና ከአሜሪካ እስከ አውሮፓ በማሸበር በወንጀል የሚታወቀውን ቄሮ በሚል የተደራጀውን ጨፍጫፊ ሽብርተኛ ቡድን ከለላ በመስጠት አቶ እስክንድር ነጋ ን “የቄሮን ስም በማጥፋት “

በማለት አቃቤ ህጉዋ ውይዘሮ አዳነች አቤቤ ፍትህን በማጣመም ለወንጀለኞች ከለላ በመስጠት የወንጀለኛ ቡድንን ስም ለመጠበቅ የሚያደርጉትን የሃሰት ዘመቻ የህግ አካሄዱ ወገንተኛነት ያለው መሆኑን ያረጋግጣል። ይህንን እንናወግዛለን።

አቃቤ ህጉዋ ወይዘሮ አዳነች አቤቤም የዘር ማጥፋት ወንጀለኞችን ቡድን በላፊነታቸው ከለላ በመስጠት ሊጠየቁ ይገባል። ይህንንም ለአለም ግልጽ እናደርጋለን። 

ስለሆነም

አቶ እስክንደር ነጋ  አቶ ስንታየሁ ቸኮል  አቶ ይልቃል ጌትነት 

አቶ ልደቱአያሌው  ወ/ሮ ቀለብ ስዩም  አቶ ገነነው አበራ 

ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን

በህግ ከለላ ስር ባለው በአቶ እስክንደር ነጋ ላይ የተፈጸመውን ድብደባ እናወግዛለን። ለአለም ህብረተሰብ እናጋልጣለን።

ዘረኛ እና አሃዳዊ ሌላውን ገፊ  የሆነውን የኤትኒክ ፌደራሊዝም ተብየውን የአፓርትይድ ህገመንግስት እናወግዛለን።

በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ዘር ማጥፋት ጀኖሳይድ እናወግዛለን በገለልተኛ አለም አቀፍ ቡድን እንዲታይ እንጠይቃለን።

ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንቆማለን

ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር

ethiopians.for.justice.frg@gmail.com

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here