
ከሃይለገብርኤል አያሌው
መስከረም 1, 2013 ዓ ም
የዶር አብይ መንግስት የእንቁጣጣሽ የመርገም ስጦታ:: የሃዘን ሰፕራይዝ : የበቀል ሰይፍ ለአውዳመቱ የተበረከተየመከራ ዜና:: ስትቃትት ለኖረች ታጋይ ነብስ:: በብቸኝነት ለተዋጠች እናት : ለሚያድግ ልጅ በዚህ የአዲስ አመትዋዜማ የተሰማ አሳፉሪ ውሳኔ:: በአዲስ ተስፉ በታደሰ መንፈስ በአሉን ለመዋል ያሰቡትን ምስኪኖች ማሳዘን ?
ለምን እስክንድር በሕይወቱ የቆረጠ ለአላማው ለመሰዋት የተሰለፈ ስለምንም ነገር ግድ የሌለው የማይሰበርመንፈሰ ጽኑ ሰው ነው:: የሚደርስበትን ሁሉ በጸጋ ያለማማረር የሚቀበል ብርቱ ነው::
በውጣ ውረድ ያልተለየችው ሚስቱ በማያውቀው የሃገር ጉዳይ የሚንከራተተው ልጁ በዚህ በሃገራችን የአዲስአመት ዋዜማ ተከፍተው እንዲውሉ አመቱን ሙሉ በጽልመት እንዲያዩት በዋዜማው ፍርደ ገምድል ውሳኔውለምን? ጥቂት ቀናት አጥታችሁ ወይስ ለመበቀል ? ይህንን በማድረግ ከቶስ ምን ትጠቀማላችሁ?
በልማድ በአዲስ እመት እስረኛ ሲፈታ እንጂ ሲታሰር አልሰማንም:: በአውዳመት ዋዜማ ምንስ በደል የፈጸመእስረኛ ቢኖር ለቀናት ባለበት መተው በአሉን በተስፉ እንዲያሳልፍ መፍቀድ የሰውነት ባህሪ መሆን ነበረበት :: በበቀልና በጥላቻ መሰረት ላይ የቆመ ከሳሽ አላማው እስረኝውንም ቤተሰቡንም አስተክዞና አሳዝኖ ለማዋልታስቦ ካልሆነ::
ፍትሕን ገሎ ፍርድ አይገኝም:: ሃቅን ቀብሮ ሃሰትን ማብቀል አይቻልም:: ውሸት ወንዝ የሚያሻግር : የሚያደርስመንገድ መቼም ሆኖ አያውቅም:: የበቀል ሚዛን ጥላቻና ውርደትን እንጂ ሰላምና ፍቅርን አታስገኝም:: የመሸውሲነጋ የቆመው ሲወድቅ ያኔ ቀላ የነበረችው እውነት ትፈካለች :: ተበዳዮችን አኩርታ በነጻነት ከፍ ስታደርግቀጣፊዎችን አሳፍራ ታዋርዳለች:: የሚሰደዱበት ጥግ የሚደርሱበት ስፍራ ይጠፉል::
በሃገራችን ብዙ ጨካኝ ቀጣፊና ፀረ ሕዝብ የነበሩ መሪዎችን ከነጭፍራቸው ተቀብለን ሸኝተናል:: እንደ ጨውሲሟሙ እንደ ገለባ ቀለው በነው ሲጠፉ አይተናል:: በሃፍረት ተሸማቀው አንገታቸውን ሲደፉ ተመልክተናል:: በጠመንጃ ጉልበት የመጡት በትዕቢት አብጠው ፍርድ
እያጣመሙ ደሃ እየበደሉ የነበሩት ገዥዎች በመጨረሻሲዋረዱ እንጂ ሲከበሩ አላየንም::
ዶር አብይ ቆም ብለው ሊያስቡ ይገባል:: በሃስት በተረኝነት በማስመሰል በማምታታትና በትዕቢይት ብዙ ሊዘልቁአይችሉም:: መጽሃፉ የቆመ የሚመስለው ቢኖር እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ እንዲል ቃሎትን ይጠብቁ ሃሰትንንቀው ከሃቅ ይቁሙ:: አሸባሪ እኛ ነን እንዳሉት እርሶ የሕወሃት ሰላይ በነበሩበት ዘመን ከሚነጋገረው ስልክእስከሚሄድበት የሚከታተሉት እስክንድር ነጋ ከሽብር የራቀ ንጹህ ኢትዮጵያዊ ለመሆኑ ከእርሶ በላይ ምስክርአይኖርም::
የልጆቾ አባት የተከበረ መሪ ሆነው ለመኖር ከፈለጉ ከእውነት ጋር ይሰለፉ:: ዛሬ ጉልበት ስልጣንና ሃይል ያውምበእርሶ ልፉት ሳይሆን በሌሎች መስዋዕትነትና ስጦታ ያገኙት የክብር ዙፉን አያርክሱት:: ወንበሩ ማክበር ብቻሳይሆን ማቅለልም ያውቅበታል:: የጀመሩት የበቀል እና የእብሪት ጉዞ መጨረሻው ውርደትና መቃብር ነው :: ሁላችንም የወደድኖት ስለ መልካም ሃሳቦት ነበር:: የሚያሻግር ሃሳብ : የሚደምር ሃቅ የሚያሰባስብ እራዕይ : ሃቅየምታነጥር የፍትህ ወንፊት: ከያዙ ሊይሰጉ አይገባም:: እስክንድር በልበ ሙሉነት የሚያኖረው መንፈስየሚመራበት እውነት ነው::
እውነት ብትመነምንም አትበጠስም:: መለስ ዜናዊ በሞት ጌታቸው አሰፉን ለመደበቅ ስብሃት ነጋን ለሽምግልናስደት የዳረገች ሃሰት ሌሎች ተረኞች ባትደግሟት መልካም ነው:: ጨው ለራስ ስትል ጣፍጥ! አለያ!!?