
ለሊቁ ፕሮፌሰር መስፍን ሽኝት ይሁንልኝ፤
ግዙፉ የእውነት፣ የሐቅና የታማኝነት ተምሳሌት፤ የተዋጣለት የምሁር ጠበቃ እና የሰብአዊነት ተሟጋች፤ ሁሌም በጭካኔ አገዛዝ አንገቱን ቀጥ፤ እራሱን ቀና አድርጎ ሲሟገት የነበረ ብርቱ ሰው ዛሬ በሞት ኃይል ተሸንፏል፡፡ ታላቁ የፖለቲካ ሰው እና ወደር የማይገኝለት ልሂቁ ብሎም እውነተኛው ምሁር ፕሮፌሰር መስፍን በፀጋ እና በክብር አርፏል፡፡
ኪሳራው ለቤተሰቡ፤ ለዘመድ አዝማዶቹ፤ ለጓደኞቹና አድናቂዎቹ ብቻ ሳይሆን ለመቶ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ሁሉ ነው፡፡ ለአንተ ለአስተማሪአችን፣ ለአርበኛችን፤ ለአማካሪአችን፤ የፍትሕ እና የእኩልነት ተሟጋቻችን በሃዘን ሳይሆን በሰላምታ እና በደስታ እንሰናብትሃለን፡፡
ከሁሉም በላይ ስላስተማርኸን፤ ስለተሟገትህልንና ስላሳየኸን ሁሉ ክብር ለአንተ ይሁን፡፡ ከኪራይ ቤት ወጠህ ኪራይ ወደማይከፈልበት የዘላለም ቤትህ ስለገባህ ሁሌም የምታምነው እግዚአብሔር ነፍስህን በአፀደገነት ያኖራት ዘንድ እንፀልያለን።
ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ለማስቀጠል ያቀጣጠልኸውን ችቦ ይዘን ትግልህን እናስቀጥላለን። ደህና ሁንልን። ሰማነህ ታምራት ጀመረ
መሰከረም ፪፫፣ ፳፩፫
A giant advocate of truth, honesty, and intellectual excellence who always stood tall against tyranny has ultimately been defeated by the Supreme power of death. A political man of gigantic proportions and a true scholar of unparalleled excellence passed away with grace and dignity. The loss is for all hundred million Ethiopians. While saluting you we say goodbye to our teacher, warrior, mentor and advocate of justice and equality. I thank you for everything you taught and showed us. Semaneh Tamrat Jemere
October 3, 2020
Canada