በወለጋ ጊምቢ ዞን ዲላ ጎላላ ጉሊሶ ወረዳ በአማራ ተወላጆች ላይ በደረሰ ጥቃት ቢያንስ 200 ሰዎች አለቁ

Amhara Genocide _ Guliso
አማራ እልቂት

ቦርከና 
ጥቅምት 23፣ 2013 ዓ ም 

በወለጋ ጊምቢ ዞን ዲላ ጎላላ ወረዳ እሁድ አመሻሽ ላይ የአማራ ተወላጆች ላይ በተደረገ ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት ቢያንስ 200 ሰዎች እንዳለቁ ተሰማ ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎችን ዋቢ ያደረጉ ዘገባዎች አሳውቀዋል፡፡

በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶችም እንደተቃጠሉ ተሰምቷል፡፡ 

ይህ እጂግ ዘገኛኝ ነው የተባለ እልቂት የኦነግ ሽኔ ታጣቂዎች እንዳደረሱ የክልሉ መንግስት አስታውቋል ሆኖም የሟቾችን ቁጥር አላሳወቀም፡፡ የህወሓትንም ቡድን አብሮ ኮንኗል፡፡ 

በወረዳው የሚኖሩ አማራዎች ለውይይት በሚል ለስብሰባ ከተጠሩ በኋላ ተከብው በተኩስ ሩምታ እንደተገደሉም ነው የተሰማው፡፡

ድርጊቱ የተፈጸመው በአካባቢው ተሰማርቶ የነበረው የመከላከያ ኃይል እንዲወጣ ከተደረገ ከአንድ ቀን በኋላ ነው፡፡ ሰራዊቱ እንዲወጣ ያዘዘው የመንግስት አካል እና ለምን ሰራዊቱ እንዲወጣ እንደታዘዘ የታወቀ ነገር የለም፡፡ 

በአማራ ላይ ያነጣነረ እልቂት በተለያዮ የኢትዮጵያ ክፍሎች በተደጋጋሚ እንደተፈጸመ የሚታወስ ሲሆን ሁኔታው እየተባባሰ በመሄድ ላይ መሆኑን ባላፉት ሁለት ወራቶች የደረሱት እልቂቶች ያመላክታሉ፡፡ 

1 comment

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *