advertisement
ጥቅምት 30 2013 ዓ ም

እንደሚታወቀው በተደጋጋሚ ፣ “መንግሥት ሕግ የማስከበር ሚናውን መወጣት አለበት!” እያልን ድምፃችንን ስናሰማ ቆይተናል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጠሩትም ሁከቶችና ብጥብጦችም ራሱን “የትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት/ግንባር” የሚለው ኃይል ከፍተኛውን ድርሻ የያዘ ስለመሆኑ ፀሐይ የሞቀው፣ አገር ያወቀው ሲሆን፣ በመላ ኢትዮጵያ ለተከሰቱት የሠላምና ፀጥታ እጦቶች ከፍተኛውን ሚና መጫወቱ ዕሙን ነው። መንግሥትም በዚህ አደገኛና ከፋፋይ ቡድን ላይ የሚወስደውን እርምጃ እንደምንደግፍና አባሎቻችንም ጭምር ከመንግሥት የፀጥታና የሕግ አስከባሪዎች ጎን እንዲቆሙ በጥቅምት 26/2013 ዓ.ም ባወጣነው መግለጫ ላይ በግልጽ አንጸባርቀናል።