የኅብረት ለኢትዮጵያ ማህበር በሀገራችን ስለአለው ወቅታዊ ጉዳይ የጋራ አቋም መግለጫ

Hibret Le Ethiopia Association _ ኅብረት ለኢትዮጵያ ማህበር

የኅብረት ለኢትዮጵያ ማህበር በሀገራችን ስለአለው ወቅታዊ ጉዳይ ከተወያየን በኃላ የያዘው የጋራ አቋም መግለጫ

ኅዳር 26 2013 ዓ.ም.

1. የኢትዮጵያ መንግስት በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በተለይ በትግራይ ክልል እየተደረገ ያለውን ሕግ የማስከበር ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል እና የወደሙ የልማት ድርጅቶችን  ተጠግኖ ወደ ስራ እንዲገባ። የትግራይ ክልል እና ሕዝብን መልሶ የማቋቋም ስራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል፣  በተጨማሪም ሕግ የማስከበር ስራውን ጊዜ ባልወሰደ መንገድ አጠናቆ ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲያቀረብ እንጠይቃለን፡፡

2. የሕዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ/ሕወአት/ ፤ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር/ኦነግ/ እና ሌሎች ተመሳሳይ የፖለቲካ ድርጅቶች ጥምረት በመፍጠር በሀገራችን እና በሕዝባችን ላይ በተለይም በአማራው ህብረተሰብ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ በፈፀሙት የዘር ማጥፋት እና የዘር ማፅዳት ወንጀል በኢትዮጵያ ታሪክ መቼም የማይሽር ቁስል ያስቀመጠ ስለሆነ እነዚህ ድርጅቶች በሀገር ውስጥም ሆነ በአለማቀፍ ደረጃ በአሸባሪነት እንዲመዘገቡ እና ከሀገራችን የፖለቲካ ምህዳር እንዲሰረዙ እንጠይቃለን፡፡ 

ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም. 
ዋሽንግተን ዲሲ 
አሜሪካ

One Response to "የኅብረት ለኢትዮጵያ ማህበር በሀገራችን ስለአለው ወቅታዊ ጉዳይ የጋራ አቋም መግለጫ"

Leave a Reply

Your email address will not be published.