
ፈቃዱ በቀለ( ዶ/ር)
ታህሳስ 13, 2013 ዓ ም
በአገራችን ምድር ታዋቂ ግለሰቦችን ወይም የአንድ ድርጅት ሊቀ-መንበርን የማምለክ በሽታ አለ። በአስተዋፅዖቸው ሳይሆን በስም ብቻ ዝናን ያተረፉ ግለሰቦችን ማምለክ ተከታታይነትና ምሁራዊ መሰረት ለሚኖረው የድርጅት አወቃቀር እንቅፋት እየሆነ በምምጣት ላይ ነው። ከውስጥ ዲሞክራሲያዊና ፖሊሲ ነክ የሆኑ ነገሮች ላይ ክርክርም ኡኦነ ጥናት እንዳይካሄድ አመቺ ሁኔታዎችን ሲፈጥር አይገኝም። በፖለቲካ ድርጅት ስም የሚንቀሳቀሱ አብዛኛዎች ድርጅቶችም ለዚህ የተዘጋጁና ለጥናትና ለምርምር የሚያመችና የሃሳብ አድማስን የሚያሰፋ መጽሀፍት ቤት ወይም የራሳቸው የሆኑ ተቋማት የላቸውም። አብዛኛዎች ድርጅቶች የአንድ ግለሰብ ወይም የጥቂት ሰዎች ሀብት የሚመስሉ እንጅ አንድ ፓርቲ ሊያሟላ የሚችለው በስራ-ክፍፍል የተዋቀረ አደረጃጀት የላቸውም። በሊቀ-መንበርነት የሚመረጡ ግለሰቦች ኃላፊነት በመሰማት መሰረታዊ ስራዎች እንዲሰሩ አስፈላጊ እርምጃዎችን ሲወስዱ አይታይም። በሊቀመንበርነት የሚመረጡም ድርጅቱ ወይም ፓርቲው በአገር ደረጃ ሰፊ መሰረት እንዲኖረውና የህዝቡንም ችግር የሚያወያይ መድረክም ሆነ ቢሮ ሳይፈጥሩ በሊቀመንበርንተቻው ብቻ እየተዝናኑ የአምባገነናዊነት ባህርይ ሲያሳዩ ይታያል። አብዛኛዎችም ፓርቲውን እንደግል ሀብታቸው በመቁጠር አንድ ጊዜ ከተመረጡ በኋላ ለብዙ አስርት ዓመታት የሙጥኝ በማለት እዚያው ላይ ይቆያሉ። ይህ ዓይነቱ ባህርይ ለተቀላጠፍና ምሁራዊ መሰረት ለሚኖረው የፓርቲ አወቃቀር ከፍተኛ እንቅፋት በመሆን ላይ ይገኛል። እንደነዚህ ዐይነት ግለሰቦች በአጋጣሚ ስልጣን ላይ በሚወጡበት ጊዜ ከመጀመሪያውኑ አዕምሮአቸው በዲሞክራሲያዊ ክርክርና ጥናት ያልታነፀ በመሆኑ የአምባገነንነት ባህርይ ይይዛሉ። አፍጠው አግጠው የሚታዩ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጥያቄዎችን የመፍታት ብቃት አይኖራቸውም። ከአገራቸው ምሁራን ጋር በመወያየትና እነሱን አማካሪ ከማድረግ ይልቅ የውጭ ኤክስፐርቶችን አማካሪ በማድረግ ያለው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊና የስነ-ልቦና ቀውስ ስር እንዲሰድ ያደርጋሉ። በአጭሩ ሰፋ ያለ ዲሞክራሲያዊና ምሁራዊ እንቅስቃሴ እንዳይዳብር እንቅፋት ይሆናሉ። ህዝብን የሚያገለግሉ ብቃትነት ያላቸው ተቋማትም በየቦታው ስለማይቋቋሙ ህዝቡ ተሰሚ አይኖረውም። ይህ ዐይነቱ ግለሰቦችን በማምለክ ላይ የሚመሰረት ፓርቲ የመጨረሻ መጨረሻ አገራችንን ያዳክማል። በህዝቡ ዘንድ የመንፈስ ጥንካሬ እንዳይኖር ያደርጋል። ጠንካራ ኢኮኖሚም ስለማይገነባ በህበረተሰቡ መሀከለ መተሳሰርና መደጋገፍ ሊኖር አይችልም።
እንደዚህ ዕይነቱ ግለሰቦችን የማምለከ ጠባይ ከፊዩዳላዊ አስተሳሰብ ጋር የተያያዘ ነው። እዚህ አውሮፓ ውስጥም ከሁለት መቶና ከሶስት መቶ ዓመታት በፊት ግለሰቦችን ማምለክ የተለመደ ነበር። ፈላስፋዎችና ሳይንቲስቶች ይህንን ዐይነቱን ነፃነትን የሚያፍን፣ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዳይዳብርና ዕውነተኛ ኢኮኖሚያዊ ዕደገት እንዳይመጣ የሚያግደውን አምልኮአዊ አስተሳሰብ አጥብቀው በመዋጋት የሪፑብሊካዊ ስርዓት እንዲመሠረትና ግለሰብአዊ ነፃነት እንዲታወጅ አደረጉ። ሰለሆነም መንግስትም ሆነ ፓርቲዎች በዚህ መንፈስ በመዳበር አገርን የሚገነቡና የህዝብንም ጥያቄዎች የሚመልሱ ሊሆኑ ቻሉ። የአውሮፓውን የፓርቲዎች አወቃቀር ተከታትለን እንደሆን ሁሉም በርዕዮተዓለም፣ በፕርንሲፕልና በዕምነት ደረጃ የተዋቀሩ እንጂ አንድን ግለሰብ በማምለክ አይደለም። የየፓርቲዎች ሊቀመንበሮችም በሌላ የሚተኩ እንጂ አንዱ የሙጥኝ ብሎ 20ና 30 ዓመት የሚቆይበት ጊዜ አይኖርም ። ለዚህም ነው ፓርቲዎች በኢንስቲቱሹን ደረጃ የተገነቡትና የመቶኖ የመቶ ሃምሳ ዓመት ዕድሜ ሊኖራቸው የቻለው።
በእኛ አገር ያለው ችግር ፓርቲዎችም ሆነ ግለሰቦች ምን ዐይነት ርዕዮተዓለምና ዕምነት እንዳላቸው አይታወቁም። ቀኞች ይሁኑ ግራዎች፣ ፋሺሽቶች ይሁኑ ኮሙኒሰቶች ምንም የሚታወቅ ነገር የለም። የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፖሊሳቸውም ምን እንደሆኑ የሚታወቅ ነገር የለም። እንደ ኢትዮጵያን የመሰለ አገር እንዴት አድርገው ከታች ወደ ላይ እንደሚገነቡም የሚታወቅ ነገር የለም። ፓርቲ ነን ቢሉም በደንብ በፓርቲ ደረጃ የተደራጁ አይደሉም። መጽሄትና ሳምንታዊ ጋዜጣም የላቸውም። የአገራችንን ችግሮች ደረጃ በደረጃ በማንሳት ከህዝብ ጋር አይወያዩም፤ ህዝብንም አያሳተፋም። ከህዝቡም ጋር ምንም ዐይነት ግኑኘነት የላቸውም። ስለሆነም አብዛኛዎቹ ዲሞክራሲያዊ ባህርይ የሌላቸውና የውጭ ኃይሎችን አምላኪዎች ናቸው። ግለሰቦችን የሚያመልኩ ሰዎች ደግሞ ዕውነተኛ ነፃነት ምን እንደሆነ የማያውቁ በመሆናቸው ያለውን አምባገነናዊ ባህርርይ ያጠናልክሩታል። አንዳንዶች ሰላሳና አርባ ዓመታት አወሮፓና አሜሪካ ቢኖሩም የከበርቴው ዲሞክራሲ እንዴት እንደተገነባና እንደሚሰራ የማያውቁ ናቸው። ስለሆነም ባይ ባይ ኢትዮጵያ ብሎ አርፎ መቀመጥ ነው።
በአውሮፓ ውስጥ የፓርቲዎች አመሠራረት የካፒታሊዝም የዕድገት ደረጃ ውጤቶች ናቸው ማለት ይቻላል። በአውሮፓ ምድር እስከ 20ኛው ክፍለ-ዘመን መግቢያ ድረስ የመደብለ ፓርቲ ስርዓት በፍጹም አይታወቅም ነበር። እስከ 19ኛው ክፍለ-ዘመን መጨረሻ ድረስ በአብዛኛዎቹ የአውሮፓ አገሮች የፍጹም ሞናርኪዎች አገዛዝ ነበር የሰፈነው። ከ14ኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ የመንፈስ ተሃድሶ አብዮት ይካሄድ ነበር። በዚያው መጠንም ስነ-ስርዓት ያላቸው ከተማዎችና መንደሮች ይገነቡ ነበር። የዕደ-ጥበብ ሙያና የንግድ እንቅስቃሴ ይዳብር ነበር። ይህ ዐይነቱ እንቅስቃሴ ቀስ በቀስ ለግለሰብአዊ ነፃነትና ለፈጠራ ስራ አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል። ሳይንቲስቶች፣ የማቲማቲክስ ልሂቃን፣ ሰዓሊዎችና የስነ-ጽሁፍ ሰዎች እንደ አሸን ይፈልቃሉ። ጋሊሊዬ፣ ኮፐርኒከስ፣ ዳቪንቺና ሌሎች፣ እንዲሁም ኬፕለርና ኒወተን የመሳሰሉ ከምድር ላይ ሆነው የኮከቦችንና የፕላኔቶችን እንቅስቃሴ በማንበብ በማቲማቲክስ የሚያሰሉ ይፈጠራሉ። ከዚያ በኋላ ሬፎርሜሽንና ኢንላይተንሜንት የሚባሉ እንቅስቃሴዎች በመዳበር ነገስታትን መፈናፈኛ ያሳጧቸዋል። ዘመኑ የጨለማ መሆን ቀርቶ የብርሃን ዘመን መሆኑ ይታወጃል። በዚህ ማዕበል የተገፉ የሞናርኪ አገዛዞች ሳይወዱ በግድ ወደ ውስጥ ያተኮረና እንድን አገር የሚያስተሳስር የኢኮናሚ ፖሊሲ ይከተላሉ። ይህ የኢኮኖሚ ፖሊሲ መርከንታሊዝም በመባል ይታወቃል። ይህ ዐይነቱ የአገር ግንባታ ሂደት ለኢንዱስትሪ አብዮትና ለካፒታሊዝም ዕድገት መሠረት ይጥላል። ውስጠ-ኃይል ያለው የህብረተሰብ ክፍልም ይፈጠራል። መንግስታዊና የፖለቲካ ሪፎርም ይደረጋል። በዚያው መጠንም ዕውቀት ይዳብራል። ትላልቅ ቤተ-መጻህፍትና ዩኒቨርሲቲዎች፣ እንዲሁም የሳይንስ አካዳማዎች ይቋቋማሉ። ይህ ሁኔታ ለምሁራዊ መዳበር ያመቻል። ሶስዮሎጂና ፍልስፍና ይስፋፋሉ። ስለሆነም እያንዳንዱ ሰው የሚለካው ከየትኛው የህብረተሰብ ክፍል እንደተወለደ ሳይሆን፣ በዕውቀቱና ለህብረተሰቡ በሚያደርገው አስተዋፆዖ ብቻ ነው።
ይህ ማለት ምን ማለት ነው? በአውሮፓ ምደር የማቴሪያል ሁኔታዎች ከመፈጠራቸውና ምሁራዊ እንቅስቃሴ ከመዳበራቸው በፊት ፓርቲዎች በፍጹም አልተቋቋሙም። በመጀመሪያ ደረጃ በ19ኛው ክፍለ-ዘመን የኮሙኒስት ሊግ ይቋቋማል። የሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ከዚህ ተሰንጥቆ የወጣ ሲሆን፣ ከተቋቋመ 160 ዓመቱ ነው። የክርሰቲያን ዲሞክራቲክ ወይም ኮንሰርቫቲቭ ፓርቲና ሊበራል ፓርቲዎች ዕድሜያቸው 70 ዓመት ያህል ነው። የግሪን ፓርቲዎች ደግሞ የሰላሳ ዓመት ዕድሜ ነው ያላቸው። እነዚህ ሁሉ ፓርቲዎች በደንብ የተደራጁና ተከታታይነት ያላቸው ናቸው። ግለሰቦችን በማምለክ ላይ የተገነቡ አይደለም። ችሎታ አለኝ የሚልና በራሱ የሚተማመን ለሊቀመንበርነት ለሌሎች የሃላፊነት ቦታዎች መወዳደር ይችላል። ለምን እንደሚወዳደርና ምን ዐይነትስ ፕሮግራም እንዳለው ያሰራዳል። አመኔታ የተጣለበትና ችሎታ አለው ተብሎ የሚገመጥ የመመረጥ ዕድሉ ከፍ ያለ ነው።
የኛ አገር ችገር ምሁራዊ እንቅሰቃሲ እንዲፈጠር አመቺ ሁኔታዎች አልነበሩም፤ የሉምም። ከአፄ ኃይለስላሴ ጀምሮ እሰከ ዛሬ ድረስ ተግባራዊ የሆኑትን የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችና የትምህርት ተቋማት ስንመለከት ለምሁራዊ እንቅስቃሴ መዳበርና ራስን ለማወቅ የሚያመቹ አይደሉም። የከተማዎችን አገነባብና የመንገዶችን አሰራርም ስንመለከት መንፈስን የሚያዘበራርቁና ለውንብድና የሚያመቹ ናቸው። በከተማዎች ውስጥ ከቤተ-መጻህፍትና ከሙዚየሞች ይልቅ ሻይ ቤቶችና የሴተኛ አዳሪ ቤቶች የተስፋፉበትን ሁኔታ እንመለከታለን። በዘመነ ወያኔ ደግሞ የብልግና ኢንዲስትሪ በከፍተኛ ጀረጃ ተስፋፍቷል። ከዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጡ የሚፈልቁ ፓርቲዎችና አገዛዝ ዲሞክራሲያዊና ህዝባዊ ባህርይ ሊኖራቸው በፍጹም አይችልም። እንደምናየው ስራቸው ሁሉ ሽወዳና ተንኮል መስራት ነው።
በዚህ መልክ የተዋቀሩ ድርጅቶች ምሁራዊ መሠረታቸው በጣም የሳሳ ነው። በሳይንሰና በኢኮኖሚ ዕውቀት ውስጥ የተደረገውን እልክ አስጨራሽ ክርክርን የተከታተሉ ባለመሆናቸው የተለያየ ስም ቢለጥፉና ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያሉ አስር ጊዜ ቢጮሁም የህዝብን መሠረታዊ ጥያቄ እንኳ መፍታት የሚችሉ አይደሉም። እየታገልን ነው እያሉ እዚያው በዚያው ፖሊሲ ነክ በሆኑ ነገሮች ላይ ክርከርና ጥናት እንዳይካሄድ ያደርጋሉ። በራሳቸውና በሌሎች የሀገራቸው ልጆች ላይ ከመተማመን ይልቅ ፈረንጅ ችግራችንን ይፈታልን ይመስል የአውሮፓው አንድነትና የአሜሪካን ኮንግረስ ጋ በመሄድና በመለማመጥ ነገሩን ውስብስብ ያደርጉታል። የቴዎድሮስንና የእምዬ ምኒልክን አገር ያዋርዳሉ። ይህንን የትግል ስልት ብለው ይጠሩታል። ቻይናዎች ለነፃነታቸው ሲታገሉ እንደዚህ ያለውን የውርደት መንገድ አልተጓዙም። የትግላቸው መርህ በራስ መተማመን ነው የሚል ነበር። ዛሬ የደረሱበትን ደረጃ ተመልከቱት። ከዚህ ስነሳ ኢትዮጵያ ውስጥ ለምን ፓርቲዎችና ምርጫም እንደሚያስፈልጉ ግልጽ አይደለም።
ለማንኛውም አንድ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ከመመዝገቡ በፊት የፓርቲውን የህይወት ታሪክና እስከዛሬ ድረስ የሰራቸውን ምህራዊ ስራዎች በደንብ አዘጋጅቶ ማቀረብ አለበት። ስለኢኮኖሚ፣ ስለማህበራዊ ሁኔታ፣ ስለሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ ስለከተማዎችና መንደሮችና አገነባብ የሚያትት ሰፋ ያለ ጽሁፍ ማቅረብ አለበት። አንድ ፓርቲ ነኝ የሚል ምርጫ ቦርድ ጋ ከመሄዱ በፊት የፓርቲዎችን ብቃትነት የሚያጠና በልዩ ተቋማት መመርመር አለበት። ለምርጫ የሚወዳደሩም መፈተን አለባቸው። ከውጭ ኃይሎች ጋርም ያላቸው ግኑኝነት መጠናት አለበት። በራሳቸው ኃይል ብቻም የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውን ብቻ ማረጋገጥ አለባቸው። ከዚህ በፊት በአመጽ ውስጥ የተሳተፉና ያልተሳተፉ መሆናቸውን፣ መሪዎቻቸው ሰው አስገድለው አላስገደሉ እንደሆነ እነዚህ ነገሮች በሙሉ በሚገባ መመርመር አለባቸው። ይህንን ሁሉ ፈተና ካለፉ ብቻ ነው ወደ ምርጫ ቦርድ ሊያመሩና ሊመዘገቡ የሚችሉት። አሁን ባለው የፓርቲዎች አደረጃጅትና አመዘጋገብ በአገራችን ምድር ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ሊቋቋም በፍጹም አይችልም። የምርጫ ቦርድም ተግባር ውስን በመሆኑ የየፓርቲዎች የህይወት ታሪክና አስተዋፅዖዋቸውን መመርመር አይችልም። መልካም ግንዛቤ!!
Sudan is claiming to be thirsty for drinking water as a direct result of the first round filling of the GERD dam. Sudan is announcing it’s government will not waste time on endless negotiations while not reaching agreement , according to the Sudaneese diplomats, Ethiopia must not go ahead with the launching of the second round of the GERD dam filling as scheduled for the month of July 2021 because doing so threatens the Rossires reservoir dam of Sudan.
The heir-apparent of the emperor of Sudan broke his silence about GERD for the first time recently by stating “Ethiopia needs to stop doing the right things the wrong way by repeating the same way of filling GERD, using water irrigated the wrong way as it was done in the first round of the GERD dam filling process because it is a serious threat to the livelihoods of the people of Sudan”.