spot_img
Sunday, May 19, 2024
Homeነፃ አስተያየትለተራበ ሳይሆን ለጠገበ እንዘን፣ (ከሰማነህ ታምራት ጀመረ)

ለተራበ ሳይሆን ለጠገበ እንዘን፣ (ከሰማነህ ታምራት ጀመረ)

ከሰማነህ ታምራት ጀመረ
ጥር 6, 2013

ለብዙ ዘመናት ሰው ሲፈራ የኖረው ረሃብን እንጅ ጥበብን አይደለም። ነገር ግን እንደ ጥጋብ አስፈሪ ነገር የለም። ምክንያቱም ጥጋብ እንደ ረሃብ በአንድ ጎኑ ብቻ አይጎዳምና ። ከመጠን በላይ ያለፈ ጥጋብ በሁለት አቅጣጫ ማለት በላይ እና በታች ያጣድፋል። የተራበ ሆዱን ይቆርጠው እንደሆን እንጂ በታችና በላይ የሚአጣድፈ ነገር እምብዛም የለበትም። ለዚህ ነው ወላጆቻችን ለተራበ ሳይሆን ለጠገበ አዝናለሁ የሚሉን። እውነት አላቸው። 

በተፈጥሮ ሕግ ውሃ ወደ ላይ እንደማይፈስ ብናውቅም አንድ አንድ ጊዜ ግፊት ሲበዛበት ሽቅብ ይፈሳል። ይህ ከተፈጥሮ ሕግ ተቃራኒ ቢሆንባችሁ እንጅ ፈፅሞ ውሸት ግን አይደለም። ፈረንጆቹ “ማንኛውም ነገር ይቻላል” እያሉ ታዳጊ ተማሪዎቻቸውን የሚያበረታቱት ለዚህ ነው። ወያኔ በአማራ ሕዝብ ላይ በሃሰት እና በውሸት ትርክት ለሰላሳ ዓመት ደጋግሞ የሰበከው እውነት መስሎ ስለተንፀባረቀ በአማራ ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ተፈጽሟል። ለማንኛውም አንድ ነገር ከተፈጥሮ ሕግ በተቃራኒው እንዴት ሊሄድ እንደሚችል (ውሃ እንዴት ወደ ላይ እንደሚፈስ) ከዚህ በታች ያሉ ሶስት አስረጅዎችን እንጥቀስ።

 1. ለብዙ ዘመን ዴሞክራሲ  በሰረጸባት አሜሪካ ጥጋብ፤ መብትና ነፃት ያለገደብ ተመግቦ ያደገው ሕዝቧ በዴሞክራሲ ቁንጣንና ትዕቢት ተወጥሯል። ቁንጣ ከመጠን በላይ ደርሶ በመፍሰሱ ካፒቶል ሂልን ሲአናወጥ አይተናል። በቀርቡ የአሜሪካ ምክር ቤት  አንተ፣ አንች፣ ወንድ፤ ሴት፤ ወዘተ ተውላጠስሞች (pronouns) ተጠቅሞ መጥራት የሚከለክል ሕግ ምክርቤት (congress) ደንግጓል[1]። የሰው ልጅ ዲሞክራሲን መከታ በማድረግ ከላይ የመጣውን የተፈጥሮ ትእዛዝ ከታች ሆኖ አፍርሷልና ቻሉት!
 • በካናዳ ኒውብረንስዊክ (New Brunswick) እና ሃሊፋክስ (Halifax) በሚባሉ ሁለት ግዛቶች መካከል ባለ ‘የፈንዲ ባህረ ሰላጤ’ (Bay of Fundi) ቁልቁል እየፈሰሰ ውቅያኖስ የሚገባ ወንዝ አለ። ይህ ከውሃ ፍሰት የተለምዶ ሕግ ውጪ የሚከሰትበት ሁኔታ የውቅያኖሱ ማዕበል ሲበዛ ወንዙን እየገፋ ይገዳደረዋል። ግፊት የበዛበት ወንዝም ወደላይ ሲፈስ ይታያል።
 • የሰውልጅ  ጥጋብን ከመመገብ ጋር ያዛምዳል። ጥጋብ ግን በብዙ መልኩ ይከሰታል። የስልጣን ጥጋብ ማናለብኝነትን፤ የሃይል ጥጋብ ኩርትና ትእቢትን፤ የሃብት ጥጋብ ትምክህተኝነትን፤ የምግብ ጥጋብ ቁንጣንን ይወልዳሉ። የተመገብነውም ሆነ ያካበትነው ሃብት፤ ስልጣንና ሃይል ከልኩ ሲአልፍ ጥጋበኛውን እያስጨነቀ በላይም በታችም ያጣድፈዋል።

ከምሳሌዎች የምንገነዘበው ቢኖር ማንኛውም ነገር ከልኩ ሲአልፍ የቅርፅና የይዘት ለውጥ ያደርጋል። ውሃ ያለቅጥ ሲሞቅ ወደ ትነት፤ ሲቀዘቅዝ ወደ በረዶነት ይቀየራል። ሰው ካለቅጥ ከጠገበ ምግቡ ከተዘወተረው ሂደት ውጪ በአፍና በታች በመቀመጫ ይወጣል። የሰው ልጅ ጥበብን ከመጠን ካሳለፈው ጤናው ብቻ ሳይሆን አእምሮውም ሰላም ያጣል።

የዚህ ፁሑፍ መነሻና ዓላማ ከሰሞኑ ከወደ አሜሪካ የተከሰተ መረን የለቀቀ የዴሞክራሲ ጥጋብና በኢትዮጵያም የወያኔ ጥጋብ ከልኩ አልፎ አሁን ከተፈጠረው ክስተትና ውድቀት ሊወሰድ የሚገባውን ጠቃሚ አስተምሮ ለማስገንዘብ ነው።

ህወሃት የአገርና የህዝብ ንብረት መዝረፍ የጀመረው ከጫካ ነው። በሽፍትነቱ ባደረገው ጦርነት የትግራይን አካባቢዎች ሲቆጣጠረ ህዝቡን ምን እናድርግላችሁ ሳይል ከመንግስት የዘረፈውን ገንዘብ፣ መድሃኒትና እህል ወደ ጦር ሰፈሩ እያጓጓዘ አሁን ግብአተ መሬቱ በተፈፀመበት ዋሻ ውስጥ ያከማች ነበር። በተዘረፈ የሀገርና የህዝብ ንብረት ነበር ኤፈርት የተባለውን የዝርፊያ ድርጅት ያቋቋመው።

ከ1983 ጀምሮ ሕወሃት ግፍ በየፈርጁ፤ ንቀት በየዓይነቱ፤ ማነአለብኝነትን በየአቅጣጫው አሳይቶናል። ለ30 ዓመት በብልግና ይህችን ድሃ ሃገር እና ህዝቧን በድሏል፤ ዘርፏል፤ አራቁቷል። የጥጋቡ መጠን ከልክ አልፎ በላይም፤ በታችም አጣድፎታል። ወያኔ የፈፀመውን ኢኮኖሚያዊ፤ ፖለቲካዊ፤ ማህበራዊ፤ ባህላዊ፤ ስነልቦናዊና ብሄራዊ ቀውስ ዘርዝሮ በተሟላ መልኩ ለማቅረብ እራሱን የቻለ ሙያዊ ጥናት ያስፈልገዋል። ቢሆንም የሕወሃትን ጥጋብ ሌሎች እንደተጠበቁ ሆነው አንዳንዶቹን እናስታውሳችሁ።

 1. ሕወሃት የኢትዮጵያን አንድነትን የሚያፋልስ፣ ሰላምን የሚያሳጣ፣ ጥላቻን የሚተክል በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተመሰረተ የሽግግር ቻርተር፣ የአስተዳደር ክልል እና ህገመንግስት በማሰናዳት አገራችንን ለእርስ በርስ ጦርነት አመቻችቷል:: ሕዝቡም በሆደ ሰፊነት አካሄዳቸውን እንዲአስተካክሉ ቢመክርም ጥጋብ የወጥረው ሕወሃት ግን ደጉንም መጥፎውንም ማግበስበሱን ቀጠለበት።
 • ሕወሃት የስልጣን ኮርቻው ስይመቻች ዘረፋ የጀመረው ከደብረ ማርቆስ ከተማ ጀነሬተርና የድንጋይ ወፍጮ ነቅሎ በመውሰድ ነበር። ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ከመቃብር ቢመለሱ አይረሷትም እየተባለ ከሚነገርላት ድሃ ከተማ ይህን የመሰለ ዘረፋ ሲአካሂዱ ሕዝብ ጉድ አለ። ሲቀጥል በስንት ጥረት ደርግ ፓዌ-መተከል የገነባውን የጣና በለስ መስኖ ፕሮጀክት እና የPVC ቱቦ ማምረቻና መገጣጠሚያ ነቅሎ በመውሰድ የምቀኝነትና የክፋቱን ልክ አሳይቷል።
 • ሕወሃት አማራን ለማጥፋት በወቅቱ የጤና ሚንስትር በነበረው ዶ/ር ቲወድሮስ አደሃኖም አማካይነት የአማራ እናቶችን በመክተብ የወሊድ አቅማቸው እንዲመክን ያደረገ ነፍሰ በላ ነው። በዚህ ሳቢያ 2.5 ሚሊዮን[i] አማራ ከሕዝብ ቆጠራ መረጃ እንዲሰወር አድርጓል። የጥጋባቸው መጠን ገዝፎ ሄዶ ስለጠፋው አማራ ሕዝብ ቁጥር በፓርላም እስከመወያየት ደርሷል። አድሃኖም እና ሕውሃት በሚሊዮን የሚቆጠር አማራ በስውር ገለው የአማራን ሕዝብ ብዛት አሳንሰዋል።
 • ሕወሃት ወጣቱ ለሃገሩና ታሪኩ ባይተዋር እንዲሆንበአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የታሪክ ዲፓርትሜንትን ዘግቷል። በዚህም ብሄራዊ ችግር ፈቺ ትውልድ ከማፍራት ይልቅ ጥገኛ ትውልድ ፈጣሪ ስርአተ ትምህርት ቀርፆ ወጣቱን ስራ አጥ፤ የሱስና ውዳቂ የምእራብ ባህል ተገዥና አምላኪ እንዲሆን አርጓል። ሕወሃትና መለስ የጎሳ ፌድራሊዝም በወጣት ኢትዮጵያውያን አደጋ እንዳይደርስበት በገነት ዘውዴና እንድርያስ እሸቴ ግንባር ቀደም መሪነት እውቅ 40 የዩኒቨርሲቲ መምህራን ካለምክንያትና ካለምንም ቅድመ ሁኔታ በአንድ ጀምበር ከዩንቨርሲቲ አባሯል።
 • ሕወሃት ለክፈተኛ ትምህርትና ለሙያ ስልጠና ወደ ውጪ ሃገር ከሚላኩ ተማሪዎች 85% የሚሆኑት ከአንድ ማህበረሰብ እንዲሆን ያደረገ ዘረኛ ቡድን ነው። የመለስና ግብራበሮቹ ንቀትና ተንኮል ምንያህል እርቀት ሊሄድ እንደሚችል ብሎም ጥጋባቸውና ጥፋታቸው ምን እንደሚመስል የሚአሳይ ተጨባጭ ምሳሌ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።
 • የደቡብ ሕዝብ በአማርኛ እንዳይማር ለማድረግ መለስ ዜናዊ ወጋገዱ የሚባል ቋንቋ ከፍራሹ ስር ፈጥሮ የደቡቡን ሕዝብ ለማስተማር ሞክሯል። በወቅቱ ወጋገዱ የሚባል ቋንቋ በደቡብ ሕዝብ የሚታወቅ አልነበረም። በኢትዮጵያዊነቱ ድርድር የማያውቀው የደቡብ ሕዝብ ምስጋና ይግባውና በጊዜ መቃወም በመቻሉ የመለስ እኩይ ተግባር ከሽፏል። ወደ 85 ሚሊዮን ብር ወጩ ሆኖ የተዘጋጀው የመማሪያና ማስተማሪያ መጻሕፍት በሙሉ እንዲቃጠል ሆኗል።
 • ሕወሃት የሃገሪቱን የኢኮኖሚ፤ ማህበራዊ፤ ደህንነትና መከላከያ መዋቅር በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ስር አድርጎ ሃገሪቱን በሁሉም አቅጣጫ ተቆጣጥሮ በዝብዟል። የሃገሪቱን ካዝና አራቁቷል። ተቃዋሚዎችን ከሰብአዊነት ውጪ በሆነ ሁኔታ ገርፏል። በውንድ ብልት ላይ ሃይላንድ ውሃ እያነጠለጠለ አኮላሽቷል። ከሴት እንዳልተወለደ፤ ሴት ልጅና እህት እንደሌለው፤ ሴት አቅፎ እየተኛ የሴት እስረኞችን ብልት አበላሽቷል። የማናለብኝነትና የጥጋቡ መጠን ድንበር አልነበረውም። ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር (US$35,000,000,000)[2] በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል።
 • በአንድ ወቅት በመከላከያ ሰራዊት ከነበሩት 152 የመከላከያ ጀነራሎች ውስጥ 135 የሚሆኑት አንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች ነበሩ። የማንአለብኝነት ጥግ፤ የጥጋብአቸው መጠን ከቁንጣን በላይም ሆኖመዝረፉንና ብልግናን በይሉኝታቢስነትቀጠለውበታል። የኢትዮጵያ አምላክና ሕዝብም ትእግስቱ አለቀና ቁንጣናቸው እንዲተነፍስ አድርጓል።
 • ሕወሃት በጥጋብ ታጅሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስንና የሙስሊሙን ማህበረሰብ ከሁለት ከፋፍሎ እርስበርስ አባልቷል። የነነውር ጌጡ ጥጋብ መረን ለቆ ኦርቶዶክስንና አማራን ዳግም እንዳያንሰራራ አርገን አከርካሪውን ሰብረነዋል ብለው በኩራት፤ በጉራና በዝና አደባባ ላይ ለፈፉ። በሰላም እንዲኖሩ በሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ለእርቅ ቢጠየቁ ያለቅጥ ስለጠገቡ አሻፈረኝ ያሉ የሰላም ጠላቶች ናቸው።
 1. ሕወሃት በአንድነቷ ታፍራና ተከብራ የኖረች ሀገራችንን አዋርዶ ሉአላዊነቷን አስደፍሯል:: የኢትዮጵያን መሬት ቆርሶ ለሱዳን አስረክቧል። የኢትዮጵያን ጥንታዊ የባህር በሮቿን በእልህ ፖለቲካ አካሄድ የባህር በሯን እንድታጣ አድርጓል:: በባድሜ ጦርነት የመሃል ሃገሩን ሕዝብና አማራውን ከፊት አሰልፎ 70,000 ሕዝብ አስጨፍጭፏል።  

የህወሃት ጥጋብና ግፍ ተዘርዝሮ የሚአልቅ አይደለምና ለናሙና እነዚህ ይበቃሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን ሁሉ እያወቀ በትእግስት፤ በይቅርታና በሰላምና በትእግስት አልፏቸው ነበር። ከጥጋብና ትቢት የተነሳ የሕዝብን ትእግስት እንደፍራቻ፤ ቁጣውንና ምክሩን በማናለብኝነትና በንቀት አጣጥለውታል። በቁንጣን፤ ትእቢትና ጥጋብ ስለታጅሉ የናቁት ያረጋል ራቁት የሚለውን የሃገራችን አባባል ረሱት።  

በአጠቃላይ ሕወሃት ታላላቅ የሀገሪቱን የገቢ ምንጭና የንግድ ዘርፎች በቡድን በቡድን ሆነው፤ በአክሲዮን ተደራጅተው ጥቅማቸውን እንዲያስከብር ባደራጁት ወታደራዊ ሀይል እያፈኑ አገሪቱን ለ30 ዓመት ግጠው አራቁቷል። ዛሬ የቀን ጅብ እና ጁንታ የሚሏችው መጠሪያ ስሞች ለነሱ በጣም የማይመጥን ኢምንት ቃላት ናቸው።

አበው ከሕዝብና ከእግዚአብሔር ቁጣ ይሰውርህ የሚሉት ያለምክንያት አይደለም። ሕወሃት ከመሆን ይሰውረን። አከርካሪውን ሰብረነዋል ባሉት ቤተክርስትያን ተደበቁ፤ የካህን ልብሰ ተክህኖ ተላብሰው ለመሰወር ሲሞከሩ በጀግናው መከላከያ ሰራዊት የተያዙ ጉዶች ናቸው።  ሕወሃት የአልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል ተጨባጭ ምሳሌ በመሆን ወደ ታሪክ ማህደር ገብቷል። ያለቅጥ ጠግበው፤ በማናለብኝነት ሰክረው የነበሩ በመሆናቸው በላይም በታችም ተንፍሰዋል።

ሕወሃት ያጠፉውን ክቡር የሰው ነፍስ  መመለስ ባንችልም በሃዘን ስናስባቸው እንኖራለን። ወደባችንና የተሸጠው መሬታችን ይመለሳል። ያወደሙት ነብረት ይጠገናል። የሰረቁትንና የዘረፉትን ሃብት የሚመለሰው ይመለሳል ማይመለሰውን ሰርተን እነተካዋለን። ያደነቆሩትን ወጣት በእውቀት እናንፀዋለን። በዘር የከፋፈሉት ሕዝብ ወደ ጥንት አንድነቱ ይመለሳል።  ጥላቻን  በፍቅር እንተካለን። ጥጋብን ፀያፍ በማድረግ በክብር፤ በሞገስና በፀጋ ሕዝባችን በሰላም ይኖራል። ጥጋበኞችን በመቀጣጫነት እያጠቀስን መሪዎችንና ሕዝብን እናስተምርበታለን። በእስር ብቻ መቀጣታቸው በቂ አለመሆኑን እያወቅንና በንስሃም መፁዳት የማይችሉ በመሆናቸው ቀሪ ሕይወታቸውን በወህኒ ቤት እንዲገፉ ይሆናል።  

ዛሬ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የሆነውን ያየ ግለሰብ፣ ቡድን፣ ድርጅት፣ ሕዝብ አገልጋይ መንግስት እና ባለስልጣን ከሁኔታው ብዙ ትምህርት ሊወስድ ይገባዋል። ያለ ህዝብ ፍላጎት ህዝብን በሀይል አፍኖ ለጥቂት ጊዜ ማቆየት ይቻል ይሆናል። ድምር ውጤቱ ግን አሟሟትን ማበላሸት ነው። በመስታውት ውስጥ የሚኖር በድንጋይ ውርወራ አይጫወትም የሚባለውም ለዚህ ነውና ልብ ያለው ልብ ይበል። ጥጋብ ሲበዛ በላይም ሆነ በታች እየወጣ ስግብገቡን አጣድፎ ያጠፋዋልና ሁላችንም ትምህርት ወስደን በጥንቃቄ፤ በጥበብ፤ በታማኝነት፤ በሐቅ ሕዝባችንንና ሃገራችንን እናገልግል። መጪው ጊዜ ብሩሕ ነውና ከዘረኝነትና ከዋልታ ረገጥ የፖለቲካ አስተሳሰብ ወጥተን፣ ለተራበ ሳይሆን ለጠገበ እያዘን ኢትዮጵያን በአንድነት እናሻግር። 

[1] https://www.theblaze.com/news/democrats-house-rules-gender-inclusive-language?inf_contact_key=eeb9fd6207c500d050291f5d5001273e842e902fbefb79ab9abae13bfcb46658::

[2] https://www.goolgule.com/tplf-has-looted-more-than-36-billion-dollar/


[i] https://satenaw.com/three-million-amara-are-missing-an-analysis-based-on-the-1994-and-the-2007-ethiopian-population-censuses/

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here