spot_img
Wednesday, March 29, 2023
Homeነፃ አስተያየትወዲ ከሃዲ! "መሸጥ የለመደ እናቱን ያስማማል"

ወዲ ከሃዲ! “መሸጥ የለመደ እናቱን ያስማማል”

- Advertisement -
 Lidetu Ayalew _ Yilkal Getet
አቶ ልደቱ አያሌው (በስተቀኝ)፤ አቶ ይልቃል ጌትነት በስተግራ ከአውሎ ሚዲያ ጋር ጋዜጠኛ ጋር ቆይታ ባደረጉበት ወቅት (ፎቶ ግራፉ ከውይይቱ ቪዲዮ ስክሪን ላይ የተወሰደ ነው)

ከቴድሮስ ሐይሌ 
ጥር 25 , 2013 ዓ.ም.

ይልቃል ጌትነትና ልደቱ አያሌው ሰሞኑን የሰጡት ቃለመጠይቅ አነጋጋሪና ሆኗል::  ሃሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ መብት ቢኖራቸውም የሃገርን ሕልውናና ብሄራዊ ጥቅም በሚጎዳ መልኩ ማቅረባቸው ተገቢ ብቻ ሳይሆን ወንጀልም ነው:: 

አንዳንድ ቀና ወገኖችና ደጋፊዎቻቸው ሃሳባቸውን እንደ ጠንካራ የፖለቲካ አቋም ሲመለከቱት ይታያል::  የሃገር ሕልውናና የፖለቲካ አመለካከት ለየ ቅል ነው:: ፖለቲካ ቀመር የሌለው በሁኔታ ላይ ተመዝኖ የሚሰላ ባህሪ አለው:: ስለ አንድ ሁኔታና ጉዳይ በተለያየ መዐዘን የሚታይ የሚተንተንና የሚያወያይ የሚሆነው:: ሃገር ግን እንደዛ አይታይም::  በይሆናል ተገምቶ በዘፈቀደ አይለካም::  ሃገር ማለት ከሃሳብ በላይ ነው::  በፖለቲካ ዱቄት ታሽቶ የማይጋገር ልዩ የሕልውና ማገርና የማንነታችን እሴት ነው::  

ለዚህ ነው በፖለቲካ የሚለያዩ አልፎም ተርፎ መሳሪ መዘው የሚገዳደሉ ተቀናቃኝ    ሃይሎች ጭምር ግጭታቸውን አቁመውና ልዩንታቸውን ለግዜው ትተው ለሃገራቸው ሕልውና ቅድሚያ የሚሰጡት::  ፖለቲካ የሚታሰበው ሃገር ሰላም ሲሆን ነው:: 

       የሰሞኑ የኢንጅነር ይልቃልና የአቶ ልደቱ ንግግር ውግዘት ያስክተለው የሃገርን ሕልውና ክዶ ተራ የፖለቲካ ፍላጎትን ለማሳካት ታሳቢ በመሆኑ ነው::  ግለሰቦቹ በሃገር ሕልውናና በሕዝባችን ሰላም ላይ በሕወሃት የተቃጣውን አደጋ እንደ ቀላል የፖለቲካ ጉዳይ በማንሳት ሃገር    እየመራ ያለውን መንግስት ሲወነጅሉ የታዩት::  መንግስትን ብዙ የምንቃወመውና የምንታገለው ጉድለት ቢኖርበትም ሕወሃትን በተመለከተ የሚቀርብበት ክስ ግን ውሃ የሚቋጥር አይደለም:: እንደውም የጠቅላይ ሚንስትር አብይ መንግስት መጠየቅ ካለበት ለሕወሃትያሳየው እዮባዊ ትዕግስትና ብዙ ግዜ መስጠቱ ነው:: ከዛ በተረፈ የተለኮሰበትን ጥቃት ለምን ተከላከለ በሚል የሚቀርብ ሰንካላ ክስ ከአንድ ፖለቲካን በቅጡ ከሚረዳ ፖለቲከኛና የሃገር ጉዳይ ይመለከተናል ከሚሉ አካላት አይጠበቅም::  

ኢንጅንር ይልቃል ስዩም መስፍንን ልደቱ አያሌው አባይ ጸሃዬን እስኪመስሉ ድረስ የሕወሃት መደምሰስ እንዲህ ሊያንገበግባቸው እንደቻለ ሊገባኝ አልቻለም?:: እጅግ በጣም ነጥብ ጥለዋል ::  የሕወሃት ጥቅም ተጋሪዎች እንኳ በነሱ ልክ እንዲህ አልሆኑም:: የኢትዮጵያ ሕልውና በሰራዊቱ ላይ የተፈጸመውን ክህደት ሳያወግዙ መንግስትን ብቻ ነጥለው ለመኮነን የሄዱበት እርቀት ግለሰቦቹ ሌላ ተልዕኮ ያላቸው እስኪመስል ድረስ ብንጠራጠራቸው አይደንቅም::    የዲጅታል ወያኔ የሳይብር ሰራዊት በሃሰት የሚነዛውን ፕሮፓጋንዳና የኢትዮጵያ የቅርብና የሩቅ ጠላቶች  የሚያኪሂዱትን የዲፕሎማሲ ተጽዕኖና ጣልቃ ገብነት ፍጹም በሚረዳ አሰላለፍ በኢትዮጵያ ሕልውና ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል ፈጽመዋል::  

እነልደቱ ለሕወሃት ውድቀት ሙሾ ካሰሙት በላይ በኤርትራ መንግስትና መሪው ላይ ያቀረቡት ክስና ስድብ ፍጹምጨዋነት የጎደለው ያካባቢውን ጂዖ ፖለቲካ ያላገናዘበ ስሜታዊ ውንጀላ የሕወሃትን ትርፍራፊ ጀሌን ካልሆነ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን የሚጠቅም አይደለም::  ሕወሃት ኢትዮጵያን ለማፍረስ በተዘጋጀባቸው ያለፉት ሁለትአመታት ውስጥ የኤርትራን ወዳጅነት ለማግኘት የኢሳያስን ጫማ ከመሳም እስከ ሕዝብ ለህዝብ ግንኙነትያላደረገው ተማጽኖ አልነበረም:: ከሻብያ ጋር እርቁ ሳይሳካ ሲቀር መሪውን አስገድሎና የአስመራን መንግስት በእጅ አዙር መፈንቅለ መንግስት ገልብጦ ለመያዝ ብዙ ሴራ ሞክራለች:: 

በሕወሃት ክብረ በአላት የኤርትራ ባንዲራ ከፍ ብሎ አንድ ነን የሚል መዝሙር ከመዘፈኑም በላይ የነገደ አግዐዚያን ንቅናቄ በሚል የትግራይ ትግርኝን አሮጌ አጀንዳ በማራገብ የደጋውን ኤርትራና የትግራይን ሕዝብ በፖለቲካ ለማዋሃድ ብዙ ጥረት ተሞክሯል:: 

የኤርትራ መሪዎች የሕወሃቶችን ልመና ንቀውና ገፍተው ከሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ለመሰለፍ በመፍቀዳቸው ሊመሰገኑ እንጂ ፍጹም ሊሰደቡ አይገባም:: 

     ሕወሃቶች እንዳሰቡት የኤርትራን መንግስት ወዳጅነትና ድጋፍ ቢያገኙ  ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ በምን ሁኔታ ላይ ሊገኝ እንደሚችል መገመት ቀላል ነው:: በተለይ የአማራው ሕዝብ ምን ሊደርስበት እንደሚችል ሳስበው ይዘገንነኛል:: ማይካድራ ላይ በቀናት ውስጥ የታየው በቀልና ጭካኔ ዞር ብሎ የሚያስብ ሕወሃት ጎንደርና ጎጃምላይ ምን ሊያደርስ እንደሚችል አይጠፉውም:: 

ኤርትራ ከኛው የወጣች የእኛው አካል ናት:: ሕዝቡም መንግስቱም በክፉ ቀን አጋርነቱን አሳይቶናል:: ይህን መሰል ሃገርን ከጥፉት ለመታደግ ያስቻለ ድጋፍ ኢትዮጵያ ከሱዳን ይሁን ከኬንያ አታገኝም::  ኤርትራውያን እውነተኛ ወንድሞቻችን በመሆናቸው ኢትዮጵያ ስትነድ ዳር ቆመው ከማየት ይልቅ እሳቱ ውስጥ ገብተው የታደጉን ባለውለታችን ናቸው:: 

ይልቃልና ልደቱ የኤርትራን መሪና ሰራዊት በማንኪያና ሹካ ዝርፊያ ለመወንጀል መውረድቸው አሳፉሪ ብቻ ሳይሆን በህግም ሊያስጠይቅቸው ይገባል::  በሌብነት የሚታወቀው ቀዳዳ በርሜልና አሮጌ ቁና ጭምር ከኢትዮጵያውያን ላይ ሰርቆ ወደ ትግራይ ሲያሸሽ የምናውቀው የልደቱና የይልቃል የጡት አባት ሕወሃት ነው::  ሕወሃት አይደለም በወረራ በያዘው መላው ኢትዮጵያ ላይ ለተራበው የትግራይ ሕዝብ የተላክን እርዳታ በአሸዋ ለውጦ በሕዝብ መቃብር ላይ ድርጅቱን የገነባ ወራዳ ቡድን ነው:: ይሄን ሴጣን ደግፎ የንዋይ ፍቅር የሌለውን የኤርትራ መሪ መዘርጠጥ ያሳፍራል:: 

ሌላው የልደቱና የይልቃል ዝቅጠት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕወሃትን ለማንብርከክ አቅም እንዳጣና እንደአልቻለ ተደርጎ በዲጅታል ወያኔ የሚነዛውን የሕወሃትን አወዳደቅ የማሳመር ተራ ፕሮፓጋንዳ እንደወረደ ተቀብለውየገለጹበት መንገድ ለገዛ ሃገራቸው ያላቸውን ጥልቅ ጥላቻ የሚያሳይ ነው::  ወያኔዎች ቆሞ ቀር በሆነ ትንተናና ዘመን የሻረው የጦርነት ስልት ተመስርተው የጀመሩት ትንኮሳ ባልጠበቁት የመልስ ምት ውልቅልቂቸው ወጥቶ መደምሰቸውንን ለመቀበል ያልፈለገው ደጋፊያቸው ለሽንፈቱ ብዙ የሃሰት ውንጀላን ሲያቀርብ ይታያል::  ከሱማሌ ጀምሮ በርካታ ሃገራት ተረባርበው አጠቁን የሚል የሃሰት ክስ ወያኔዎች ቢያሰሙም እውነታው ግን ሌላ ነው::  አዎን ድንበር ለመጠበቅ በተሰማራው የሰሜን እዝ ላይ መብረቃዊ ያሉን የክህደት ጭፍጨፉ አካሂደው ወደአርት ኪሎ ለመገስገስ ገና እግራቸውን ሳያነሱ  በፈጣን የመከላከልና የማጥቃት እርምጃ የደቆሳቸው የአማራ ልዩ ሃይልና ፉኖ ከመነሻው አከርካሪው በመሰበሩ ለመሆኑ ታሪክ ምስክር ነው::  የአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ከተለያየ አቅጣጫ የመከላከያ ሰርዊታችን ተሰባስቦ የመጨረሻውን ደምሳሽ ዘመቻ እስኪጀምር ባሉት ቀናት በፍጹም ጀግንነት በመመከትና በማጥቃት የሕወሃትን የመጨረሻ መጀመሪ አሳምሮታል::  ተረፈ ሕወሃቶችና ልሳኖቻቸው ገለን ቀብረነዋል ባሉት የአማራ ክንድ ታሪካቸው መደምደሙን ሊቀበሉት ስለከበዳቸው በአሽከርነት ያገለገሉትን ሻብያን በመክሰስና ሌሎችንም ተዋንያኖች በማከል የውድቀት ገጽታቸውን ለመገንባት የሚያደርጉትን ጥረት ከአማራ በሚወለዱት ይልቃልና ልደቱ ማስረገጥ የፈለጉት:: 

ይልቃልና ልደቱ በዲጅታል ወያኔ መድረኮች በተጋሩ ስብስቦች ደምቀውና ከፍ ብለው ውለዋል:: የሕወሃት ፖለቲካ በደጋፊዎቹ ባኖረው የድጋፍ ችሮታ ከክንቱ ውዳሴ የገንዘብና የጭን ስጦታ ወዶ ገቦችን በማማለል መጠቀሚያ የማድረግ ብቅቱን በደንብ እየተጠቀመበት ይገኛል::  የልደቱና የይልቃል ንግግር ከሃገሪቱ አንጋፉ ፖለቲከኞች እንደቀረብ ክስ እየተቀባባ በየሃገሩ ቋንቋ እየተተረጎመ በትግራይ ላይ በደረሰው ሰብዐዊ ቀውስ ያለው መንግስት እንዲጠየቅና የሰላም አስከባሪ አካል ጣልቃ እንዲገባ እንደ ማስረጃ እየተዘጋጀ ይገኛል::

ሃገራዊ ፖለቲካችን ብዙ ችግሮች የተጋረጡበት ፈተናዎች የበዙበት ለመሆኑ አያከራክርም::  እየከበበን ካለውአካባቢያዊ አደጋ ሰብሮ ለመውጣት የፖለቲካ ማሻሻያ ማድረግ ያላግባብ የታሰሩትን መፍታት ከጎሳ በላይ ለሃገርሕልውና ላይ መስራትና    የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፉት አማራጭ ብቻ ሳይሆን እንደ ሃገር ከገጠመን አደጋ ለመሻገር ብቸኛው መንገድ ነው:: 

በትግራይ ወገናችን ላይ የደረሰውን ችግር ተረባርበን በመፍታት ሕዝቡ ወደ ሰላማዊ ሕይወቱ እንዲመለስ ማገዝ የመንግስት ብቻ ሳይሆን የሁላችንም ተሳትፎ ያስፈልጋል::  እንደሚባለው የኤርትራ ወታደሮች ድንበር አልፈው በሕዝቡ ላይ ተገቢ ያልሆነ ነገር ካደረጉም መንግስት ተገቢውን የእርምት እርምጃ በመውሰድ ሕዝቡን ከጥቃት መከላከል ይኖርበታል:: 

የኤርትራ መንግስትና ሕዝብ ታክቲካል ብቻ ሳይሆን እስትራቴጂካል አጋራችን በታሪክ በደምና ባህል የምንዛመድ ወንድማማች ሕዝብ በመሆናችን ሕብረትና ትብብራችን የሁላችንም ጥቅም መብትና ደህንነት ባረጋገጠ ግልጽና የማያሻማ የስምምነት ማዕቀፍ ሊበጅልት ይገባል:: ኢትዮጵያና ኤርትራ ሕዝቦች በአፍሪካ ቀንድና በቀጠናው ተከብረን ለመኖር የሕዝባችንን ብልጽግናና ልማት ለማረጋገጥ መንግስታት ቢቀያየሩ ሊናድ በማይችል የትብብርና የአብሮነት ጠንካራ መሰረት ላይ መገንባት ያስፈልጋል::  ከዚህ ባሻገር በአንዳንድ ጊዜያዊ ጥቅማቸውን ባስቀደሙ የኢትዮጵያም ሆነ የኤርትራ ተወላጅ ግለሰቦች የጥላቻ ቅስቀሳና ንግግር የሕዝቡን አብሮነትናትብብር እንዳይበክል በግዜ ማውገዝና ሴረኞችን ማጋለጥ በሁለቱም ወገኖች በንቃት ተጠናክሮ መቀጠልይኖርበታል:: 

ኢትዮጵያን እግዚያብሄር ይባርክ!!!  

አሜን!!!

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,460FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here