spot_img
Wednesday, May 29, 2024
Homeአበይት ዜናበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዘር ማጥፋት መከላከያ ድርጅት (ኦቴጅ) O.T.A.G.E የተሰጠ መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዘር ማጥፋት መከላከያ ድርጅት (ኦቴጅ) O.T.A.G.E የተሰጠ መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዘር ማጥፋት መከላከያ ድርጅት (ኦቴጅ) O.T.A.G.E የተሰጠ መግለጫ
 
መጋቢት ፳፰ ፪፻፲፫ ዓም (April 6. 2021)

ከስድሰት ወራት በፊት በብፁእ አባታችን አቡነ ቴዮፍሎስ የሰሜን ካሊፎርንያ የኔቫዳ እና የአሪዞና አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ሊቀመንበርነት ቡራኬ እና ፀሎት ሥራውን የጀመረው እና ሲያካሄድ የነበረው ይህ ድርጅት ዛሬ የመጀመሪያውን ታላቅ እርምጃ ወስዷል። ይህ ድርጅት በተቋቀመበት ወቅት በያዘው የማይናወጥ ዓላማ መሠረት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በመካሄድ ላይ ያለውን በሀይማኖት : የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮችን: በዘር ደግሞ አማራን ለማጥፋት እየተፈፀሙ ያሉት የዘር ማጥፋት ወንጀሎችንና ሌሎቹንም የኢሰብአዊ ወንጀሎችን ለዓለም አቀፍ የፍትህ ተቋማት በተለይም ይህንን ለመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ወንጀሎች ተብሎ በአውሮፓውያን አቆጣጠር  በ2002ዓም በጣልያን አገር ሮማ ለተቋቋመው የዓለም አቀፍ ወንጀል መቅጫ ፍርድ ቤት ( International Criminal Court)  ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ፣ አለ ደመወዝ ፣በፈቃደኝነት በተሰባሰቡ ባለሙያዎች ሥራው በትጋት ሲያከናውን ቆይቷል።

ኦቴጅ በስሙ የቤተ ክህነት ድርጅት ይምስል እንጂ ለክርስትያን ለእስላም ለአማራ ለ ኦሮሞ ለትግራይና ለመላው ህብረተሰብ የቆመ ነው:: በታሪኩዋ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ከጥንት ጀምሮ ለኢትዮጵያ ህልውና ሰላም አንድነት: ዘር: መልክ:  ቋንቁዋ ሳትለይ ሁሉን በአንድ ዓይን ተመልክታ ከመላው ህዝብ ጋር የቆመች ነች:: ዛሬ ግን የፌዴራል መንግስትና የማዕከላዊ መንግስትና የፌደራል መንግስታት በይፋ አማራና የኦርቶዶክስ ሀይማኖት  መጥፋት አለባቸው ብለው ምእመናን በአስቃቂ መልክ ሲገድሉ : ቢተክርስትያንን ሲያቃጥሉ : እስላሞችንም እማራ በመሆናችው ሲገደሉ ሲፈናቀሉ ሁላችንም በየእለቱ የምናየው የምንመስክረው ሰለሆን ለእነዚህ የበለጠ ትኩረት ስጥተናል:: በመጠናት ላይ ካሉት 11 ክሶች ውስጥ የአክሱም;  የማይካድራ የወለጋ የጌዶ : የሶማሊያ: እና የኦሮሞዎችም ጭምር ይገኝባቸዋል::

ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ወንጀለኞችን ለማቅረብ በጣም ዘርዘር ያሉ ስራዎችንና ረዥም ጊዜ ስለሚወስድ እውቀት ያላቸውንና ጊዜአቸውን መስዋእት ለማድረግ የቆረጡ: ማስረጃዎችን ሰብስቦ በሚፈለገው መልክ ለማቅረብ ብዙ የኦቴጅ አባላትንና  እንዲሁም በተመሳሳይ ስራ ላይ ተሰማርተው ለተባበሩን ሁሉ ምስጋናችንን እናቀርባለን:: እነዚህን መረጃዎች ለፍርድ ቤት ለማቅረብ ከማመቻቸት በላይ፣ እነዚህን በኦቴጅ የተጠኑትን መረጃዎች ከተከሳሾች ጋር አያይዞ ለዓለም ዐቀፍ ፍርድ ቤት ጠበቃዎች ማቅረብ ከባድ ሥራ ነበር።

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተመሳሳይነት ባለው የርዋንዳን ጉዳይ በተመለከተ በአሩሻ ታንዛኒያ  በተባበሩት መንግስታት የተቋቋመው ኢንተርናሺናል የወንጀለኛ ቲሪቢውናል ፍርድ ቤት  (International Criminal Tribunal Court  for Rwanda ) ልምድ ያላቸው፣ የኢትዮጵያን ሁኔታ በአንክሮ የተመለከቱ፣ በዓለም ታዋቂነት ያላቸው ጠበቆች ለማግኘት ሲደከም ቆይቷል።  በዚህም መሠረት የሕግ ኮሚቴው ብዙዎች ዓለም አቀፍ ጠበቆችን ካነጋገረ በኋላ፣ ለዚህ ሁኔታ አመቺ ነው ተብሎ የተመረጠውን ለጠቅላላ ጉባዔ አቅርቦ ከተመረጠው ድርጅት ጋር ውል እንድናደርግ ተፈቀደ። ይህ ውል ዛሬ በኦቴጅ መሪዎችና በጠበቆቹ መሀከል በዛሬው እለት የተከናወነው አንዱና ዋናው ጉዳይ ነው:;

እንደሚታወቀው  ይህ ልዩ ትሪቡናል (ICTR)በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ከተሰሱት መሀክል  96 ባለስልጣኖች ፍርድ ያሰጠ ነው::ምንም እንኮን ብዙውቹ ከአገር እምልጠው ቢወጡም ከያሉበት እየተለቀሙ ለፍርድ ቀርበዋል:: ፍትህ ጊዜ ሊወስድ ይችላል :: አሁን ባለንበት ዘመን ግን ጊዜው ይርዘምም ይጠርም እንድ ጊዜ ክሱ ከቀረበ በሁዋላ መያዝና መጠየቅ መፈረጅ አይቀሬ ነው::

ከዚህ ዓለም አቀፍ የህግ ድርጅት ጋር  በዛሬው  ዕለት ኦቴጅ ከያዛቸው 13 የወንጀል ድርጊቶች ውስጥ የተጠናቀቁትን ሁለት የዘር  ማጥፋት ወንጀሎች ለህግ እማካሪዎቹ እቅርቦኣል:: እነዚህ በመጠናት ላይ ካሉት 13 ወንጀሎች ሁለቱ ብቻ ናቸው::ከዚህም ጋር ግንባር ቀደም  የተከሳሾችን  ስም ዝርዝር   ለጠበቃዎቻችን አቅርበናል።እነዚህ በዚህ ቅጽበት በደረስንበት የመረጃ ስብሰባ እና ምዘና  በከፊል የቀረቡ እንጂ ፤ በሚቀጥሉት የስራ ሂደቶቻችን ውጤት መሰረት በተጠይቂነት ስማቸው የሚካተት የቀድሞ እና የአሁን ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል ባለስልጣናት፤ የፓርቲ ወይም ንቅናቄ መሪዎች፤የመገናኛ ብዙኋን ሃላፊዎች፤ ዕልቂት አነሳሾች ስም ዝርዝር ይካተታል::

በተጠናቀቁት ሁለት ስራዎች  በቤንሻንጉል ክልል የመተከል ዞን እና አሩሲ ዞን(ሻሸመኔ) በአማራ ብሄር እና በኦርቶዶክስ ክርስትያን አማኞች ላይ እንዲሁም  ከአማራ ጋር ግንኙነት ያላቸውን የሌሎች ብሄረሰብ አባላት  ተለይተው የተጨፈጨፋበትን እና ለዚህም ተጠያቂ ሊሆኑ የሚገባቸውን በተሟላ ማስረጃ  ለህግ ጠበቆቹ አቅርበናል።

 ይህ ዕለት እስካሁን የተደከመባቸውን ስነዶች የኦቴጅ ባለሙያዎች እንደመረመሩት: ክሳችንን የሚያጠናክሩ  ብዙ ጽሁፎች፣ ቪዲዮዎች፣ ፎቶዎች: ቃለ ምልልሶች እና  ምስክሮች፣እንዲሁም  ከዘር ፍጅቶች እና ማፈናቀሎች ጋር በማድረግም ባለማድረግም ( Omission or Commission) ተጠያቂ የሚሆኑ አውራ ባለስልጣናትን ከወንጀሎቹ ጋር የሚያይዛቸውን  ነገሮች ሁሉ መርምረን ያጠናቀቅናቸውን ሰነዶች ለኢንተናሽናል ፍርድ ቢት እንዲቀርቡ ለኢንተናሽናል ህግ አማካሪዎች አጠቃልለን ያቀረብንበት ቀን  በመሆኑ ለኦቴጅ ታሪካዊ ቀን ነው ብለን እናምናለን።

የዘር ማጥፋት ወንጀል አንድ ህብረተሰብን በማንነቱ ወይም በሃይማኖቱ ማጥቃት ወይም ለማጥቃት መሞከር ነው ። የዘር ማጥፋትን ወንጀል ከኢሰብአዊ ወንጀሎች የሚለየው የዘር ማጥፋቱ በማንነት ላይ ያተኮረ በመሆኑ ብቻ ነው ነገር ግን ሁለቱም ወንጀሎች እንደ አውሮፓ አቆጣጠር  በ1948 በተባበሩት መንግስታት ጸድቆ (Resolution 260) በጃንዋሪ 12፣ 1951 በተግባር ላይ የዋለው በእንግሊዝኛው  The Convention on the Prevention  and Punishment  of Crimes of Genocide  የሚባለውንና በሕግ የተዘረዘሩትን ወንጅሎች የሚያሟሉ  ናቸው:: እነዚህም በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1949 ዓ፣ም በወጣው የኢትዮጵያ ወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 289 ላይም የተዘረዘሩ ናቸው::

 የኢንተርናሽናል አማካሪዎች በተጣሩት ጉዳዮች ላይ ሲሰሩ ሌሎቹ 11 የክስ  ጥናቶች እንደተጠናቀቁ ይቀርብላቸዋል።በቀጣይነትም ኦቴጅ ባለፉት  በርካታ የመከራ ዓመታት በኢትዮጵያውያን ላይ በሁሉም አቅጣጫዎች የተፈጸሙ የዘር ማጥፋት እና ኢሰብአዊ  ወንጀሎችን  ከነፈጻሚዎቻቸው እና ተባባሪዎቻቸው ጋር ወደ ፍትህ አደባባይ እንዲቀርቡ ይሰራል።

ክዚህ የኢነተርናሽናል ህግ እማካሪዎች ጋር የገባነው ውል: ኦቴጅ በራሱ ጥናት በኢንተርናሽናል ህግ ያስጠይቀዋል የሚባሉትን ሁሉ በኢንተርናሽናል ፍርድ ቤት ለክስ የሚቀርቡ የሚችሉትን ጥያቁዎች መስረት ለህግ አማካሪዎቹ ማቅረብ ሲሆን የህግ እማካሪዎች  ደግሞ በዘር ማጥፋት ወይም በኢሰብእዊ ወንጅሎች የሚጠየቁትን ለያይተው ያቀረብናቸውን ማስረጃዎችን ጥንካሬ በመመርመር የጎደለውን እንድንሞላ ጠይቀውን የሚያረካ ደረጃ ላይ መድረሱን ሲያረጋግጡ ወደ ፍርድ ቤቱ ያቀርባሉ:: 

በሮም በ2002 እንደ እውሮፓ እቆጣጠር የተፈረመው የኢንተርናሽናል ወንጀለኞች ፍርድ ቤት የሚመለከታቸው ወንጀሎች ከዚያ ጊዜ በሁዋላ የተፈፀሙትን ብቻ ነው:: በተለይም ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት  የዚህ ውል ፈራሚ መንግስት አልነበረም:: ለውጥም መጣ ከተባለ በሁዋላ መፈረምና የፈራሚዎች መንግስታት  እባል መሆን ሲቻል ይህ መንግስት አልፈቀደም:: በጊዜው  139 መንግስታት ሲፈርሙና 118 በፓርላማቸው ያጸደቁ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት እስከአሁን ሁለቱንም እላደረገም::እውነት ፍትህ ፈላጊ መንግስት ከሆነ በዚህ ወንጀል ተጠያቂ የሆኑትን ለመመርመርና ካስፈለገ ለመክሰስ ይህንን ውል እንዲፈርም ኦቴጅ ይጠይቃል::

ይህ ካልሆነ በቀጥታ ተከሳሾችን እዚህ ፍርድ ቤት ለማቅረብ እማራጮች አሉ:: አማራጮቹን በውስጣችንም ከብዙ የህግ እማካሪዎችና የኢንተርናሽናል ወንጀለኛ መቅጫ ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ ጋርና ከተባበሩት መንግስታት ባለስልጣኖች ጋር ተወያይተናል። የዚህ ውል ፈራሚ ያልሆኑ ሀገሮች በመንግስትም ሆነ ማለትም  በኢንተርናሽናል የፍትህ ፍርድ ቤት ( ICJ) ወይም ደግሞ በሌሎች ጉዳዬች ይመለከተናል በሚሉ መንግስታት እማካይነት ከተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይችሉ ማረጋገጥ ይቻላል:: በተጨማሪም ይህንን የመሳሰሉ የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን እይፈጸሙ እና እያስፈጸሙ ያለ ቅጣት  በስልጣን ማማ ላይ ለመክረም እና ለማምለጥ የሚውተረተሩ አምባገነን መሪዎች በሚመሯቸው ሀገራት ላይ  ለምሳሌ ለመጥቀስ ያህል አለማአቀፋዊ ማዕቀብ ሊጣልባቸው  እንደሚቻል መገንዘብም ያስፈልጋል::  ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደው የህዝብ ፍጅትና ትርምስ በሰብአዊ ቀውስነቱም ሆነ ከድንበር ባሻገር ሊያመጣ የሚችለውን ከባድ ስጋት ተመርኩዘው የአለም ህብረተስብ ጣልቃ እንዲገባ የሚጠየቅበት ጊዜ እየተቃረበ መሆኑን ልብ ይሏል።

የህግ እማካሪዎቻችን  በእያንዳንዱ ክስ ላይ የቀረበውን ማስረጃ  አጠናቀው ለፍርድ ቤት ካቀረቡ በሁዋላ ተከሳሾች ከእገራቸው ሊወጡ የሚችሉት ይህንን ውል ወዳልፈረሙ ሀገራት ዘንድ ብቻ ነው:: ይህንን ውል የፈረሙ ሀገራት ተከሳሾችን የሀገራቸውን መሬት  ከረገጡባት ቅጽበት ጀምሮ በቁጥጥር ስር እድርገው በራሳቸው ሀገር ህግ  ሊጠይቋቸው ወይንም ወደ አለም አቀፍ ፍርድ ቤትም ለመላክም ሙሉ ስልጣን አላቸው::

ወገኖቻችንን ለማሳሰብ የምንፈልገው ፍርድ ቤት ቀርቦ ፍርድ ማግኘት ጊዜ ይጠይቃል:: ብዙ ጬኸት ብዙ ንግግር በብዙ ኢንተርናሽናል መድረክ እየተገኙ መናገርን ይጠይቃል:: እስክዛሬ ግን ይህንን የመሳሰሉ ወንጀሎች ፈፅመው ከኢንተርናሽናል ህግ ያመለጡ ወይንም በራሳቸው አገር ፍርድን ያልተቀበሉ ብዙም የሉም::

እስክዚያው ትእግስታችሁ እርዳታችሁ እና ጸሎታችሁ እይለየን:: ያለ ፍትህ ሰላም የለም: እርቅ የለም:: ኢትዮጵያ እንደገና ታብባለች  ::

ፈጣሪያችን ሀገራችንን ይጠብቅልን

የተክስሾች ዝርዝር:በከፊል:

ሽመልስ አብዲሳ  –  የኦሮሚያ ክልል ም/ ፕሬዘዳንት
አደም መሃመድ – ኤታማጆር ሹም
ደመላሽ ገ/ሚካኤል – (ደህንነት)
አራርሳ መርዳሳ -(የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር)
አበበ ገረሱ – (የኦሮሚያ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ሃላፊ)
ጋዲሳ ሁሴን  – የሻሸመኔ ከተማ ፓሊስ ኮማንደር
አሻድሌ ሁሴን – የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዚደንት       
ደጀኔ ወሰኔ – የምእራብ አርሲ ዞን የፓሊስ አዛዥ
አምባስደር ምስጋናው አድማሱ – የቀድሞ የቤንሽስንጉል ጉምዝ ም/ፕሬዘዳንት
አድጎ አምሳያ – የቤንሻንጉል ጉምዝ ምክትል  አስተዳዳሪ
ጌታሁን እጅጉ -የቤኒሻንጉል ክልል የፕሬዘዳንት አማካሪ
ጋዋ ጃኔ – የተወካዮች ምክር ቤት አባል
አበራ ባይታ -የሰላምና የፅጥታ ሃላፊ
አለምነሽ ይባስ – የክልሉ ምክር ቤት ቃል አቀባይ
አትንኩት ሽንቁጥ – የመተከል ዞን አስተዳዳሪ
አድማሱ ሞርካ  – የድርጅት ጉዳይ  ሀላፊ
ማርዬ አንበሴ – የመተከል የደህንነት ሃላፊ
ሙሉአለም አልባሮ -የክልሉ የሲቪል  ስርቪስ ሃላፊ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

3 COMMENTS

  1. የዓበልን ደም የፈረደ ግዚአብሔር በእናንተ ላይ አድሮ ፍርዱን ይስጥ። በርቱ እውነት ለግዜው ብትቀበርም ጊዜዋን ጠብቃ እንደ እሳቴ ጎሞራ ፈንድታ መውጣቷ አይቀርም። አንታገሳለን አምላካችን ይፈርዳል። ብልቃጥ የማትሞላው የራሔል እንባ ባሕር ውስጥ አስምጣ ለታሪክ እንዳይታወሱ የማድረግ ኃል አላት። በመጨረሻም የሕወኀት ባለስልጣናት ግን የሉም አማራ ገዳይ የሚለውን የተረኩ ፈጣሪዎችስ መቸም ረስታችሁ አይመስለኝም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here