spot_img
Monday, May 29, 2023
Homeነፃ አስተያየት“ያልነቃው አንቂ” በሕዝባችን ደም መነገድ ያቁም! (ክፍል ሁለት)

“ያልነቃው አንቂ” በሕዝባችን ደም መነገድ ያቁም! (ክፍል ሁለት)

- Advertisement -

ጥበበ ሳሙኤል ፈረንጅ
ሚያዚያ 20 ቀን 2013 ዓ. ም.

ሽብርተኝነት የሕሊና ጦርነት ነው። አሸባሪዎች፤ ፍርሃት፣ አለመረጋጋት፣ እንዲሁም በማህበረሰባችን ክፍፍል በመፍጠር ሊቆጣጠሩን እና ባሕሪያችንን እንድንቀይር ለማድረግ ይሞክራሉ።ፓትሪክ ኬነዲ

መጪውን ምርጫ ሆን ብለው የሚያጣጥሉ ሃይሎች፤ ሃገራችንን አንድ እርምጃ ወደፊት ለማራመድ ተግተው በሚሰሩ ብርቅዬ ዜጎቻችን ላይ እንቅፋት በመፍጠር፤ አንድም በማወቅ፤ ሌላም ደግሞ ባለማወቅ፤ የአጥፊዎች ተባባሪ እየሆኑ ነው። አውቀው የሚተባበሩት፤ አንድም በገንዘብ የተገዙ ሲሆኑ በሌላ ደግሞ የራሳቸው፤ ሥልጣን ላይ የመፈናጠጥ ሕልም ያላቸው ናቸው። እነዚህ የሥልጣን ሕልም ያላቸው ሃይሎች፤ ሃሳብን በሃሳብ በመሞገት፤ ለሃገር ይበጃል የሚለውን እቅድ በመንደፍ አደባባይ የመውጣት አቅም ስለሌላቸው፤ ሁሌም ነውጥ በመፍጠር፤ ወደ የሚጎመጁባት የሥልጣን ማማ ላይ ለመውጣት ይሞክራሉ። ማንም ዜጋ ሥልጣን እንዲመኝ እና ሕዝብ እንዲያገለግል ሊበረታታ ይገባል። ሆኖም፤ ሥልጣን የሚይዘው ሕዝብን ለማገልገል እና በሕዝብ ፈቃድ ብቻ መሆኑንም እንዲገነዘብ ማድረግ ያስፈልጋል። ጽንፈኛ የሥልጣን ጥመኞች ግን፤ ዓላማቸው ግላዊ እንጂ ሕዝባዊ ባለመሆኑ እና የሕዝብን ልብ በማሸነፍ፤ ወደ ሥልጣን የመምጣት ፍላጎትም ችሎታም ስለሌላቸው፤ ሁሌም የሚጠቀሙት አማራጭ ነውጥ ነው። እንቆምለሃለን የሚሉትን ሕዝብ የሚፈልጉት፤ በደሙ ለመነገድ እንጂ፤ ለሕዝቡ አንድ ቁም ነገር ሰርተው አያውቁም። “የገበያ ግርግር ለሌባ ይመቻል” እንዲሉ፤ በሃገር ውስጥ ቀውስ እንዲፈጠር ተግተው ይሰራሉ፤ ከቀውስ ፈጣሪዎች ጋር ይተባበራሉ፤ ይህ ሲሳካ ደግሞ፤ “መፍትሔው እኛ ብቻ ነን” “ከእኛ በላይ ለሃገር ተቆርቋሪ የለም” በሚል እሳቤ፤ ለሌላው “ዜግነት ለመስፈር ይሞክራሉ”፤ ባለተሞረደ አንደበት እና ሃገርን የመምራት አቅም አለኝ ከሚል የፖለቲካ ኃይል የማይጠበቀ፤ ጠብ አጫሪ የሆነ የመግለጫ ጋጋታ ያዘንባሉ። “ከጳጳሱ፤ የበለጠ ርስቲያን ነኝ” በሚል ደካማ እሳቤያቸው፤ ለሃገር ቀናኢ እሳቤ ያላቸውን ዜጎች በማሳሳት፤ የእኩይ ዓላማቸው መሳሪያ ያደርጋሉ።

እነዚህ ኃይሎች፤ የዐብይ አስተዳደር ምንም ቢሰራ አይጥማቸውም፤ ለሁሉም ነገር ስበብ አላቸው። ከዚህ ቀደም፤ ምርጫው እንዲራዘም ሲወተውቱ ነበር፤ ምርጫው በኮቪድ-19 ምክንያት ሲራዘም ደግሞ፤ ሙዚቃቸውን ቀይረው፤ “ዐብይ ሥልጣኑን ለማራዘም ሲል ምርጫውን ሰረዘው፤ መቼ ምርጫ እንደሚካሄድ እንኳን አይታወቅም” ሲሉ ይከሳሉ። ምርጫውን ያራዘሙት ዐብይ እንዳልሆኑ እና ምርጫውን ለማራዘም ዐብይ ምንም ዓይነት ሥልጣን እንደሌላቸው ያውቃሉ። ምርጫው እንዲራዘም የጠየቀው ምርጫ ቦርድ እና ጥያቄወንም የተቀበለው የሃገሪቱ ምክር ቤት ነው። አሁን ደግሞ ምርጫው እንደሚካሄድ እና አይቀሬ መሆኑ ሲገባቸው፤ አሁን ሃገሪቱ ባለችበት ሁኔታ “ምርጫ ቅንጦት ነው” የሚል ዜማቸውን ጀምረዋል። ለየትም ሃገር ምርጫ ቅንጦት ሆኖ አያውቅም። ሕዝባችን፤ ፈልጎ እና ወዶ ድምፁን በሚሰጣቸው የፖለቲካ ሃይሎች የመምራት መብት አለው። ዛሬ ላለብን ትርምስ አንዱ ምክንያት፤ በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት አለመኖሩ ነው። ዶ/ር ዐብይ ወደ ሥልጣን የመጡበት ዋነኛ ዓላማ እና ሕዝቡም የሰጣቸው ከፍተኛ ሃላፊነት፤ በሃገራችን ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ተካሂዶ በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት ሥልጣን እንዲይዝ ነው። ይህ ሆኖ ሳለ፤ ጽንፈኛ ሃይሎች የሚጠይቁት ጥያቄ “ዐብይ ከሥልጣን ይውረድ” የሚል ነው። ከዛስ ለሚለው ደግሞ መልሳቸው፤ በሽግግር መንግሥት ስም እኛን ሥልጣን ላይ አውጡን የሚል ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁለት የሽግግር መንግሥት አስተናግዷል፤ አንድም በደርግ፤ ኋላም በሕወሃት የሥልጣን ዘመን። ሁለቱም “የሽግግር መንግሥታት” ሕዝባችን ላይ ያደረሱት ግፍና ጠባሳ እስካሁን አልዳነም። ምርጫ ቅንጦት ነው የሚለው ትርከት፤ ባልነቁ አንቂዎች፤ የሚደሰኮር ተራ መፈክር እንጂ ለሃገር የሚፈይድ አይደለም። የሚያሳዝነው፤ እነዚህ ሃይሎች፤ ባማሩ እና ተገቢ በሚመስሉ የቃላት ሃረጎች፤ ለሃገሩ ቀናኢ የሆነውን ዜጋ መንገድ ማሳታቸው እና የእኩይ ዓላማቸው ተሳታፊ ለማድረግ መሞከራቸው ነው። እንኳን ኢትዮጵያ፤ ኢራቅ እና አፍጋኒስታን እንኳን በጦርነት እና በሽብር እየተናጡ ምርጫ አካሂደዋል። ሆን ብለው እና አቅደው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ምርጫ ቅንጦት ነው  ብለው የሚሰብኩ የፖለቲካ ሃይሎች፤ በሃሳብ ተከራክረው ለማሸነፍ የማይችሉ፤ በሃሳብ ጠኔ የተጠቁ እና፤ በሕዝብ ደም በመነገድ ወደ ሥልጣን መምጣት የሚፈልጉ ናቸው።   

“ፍኖተ ካርታቸው” የዐብይን አስተዳደር በማጣጣል ላይ ብቻ የተመሰረተ የፖለቲካ ሃይሎች፤ ውቅያኖሱን ሳያዩ፤ ወኃውን ብቻ የሚያዩ መሆናቸው ሊያስገርመን አይገባም። ከአፍንጫቸው አርቀው ማሰብ ስለማይችሉም ነው፤ በየጊዜው ሙሾ ከማውረድ ባሻገር፤ ሥልጣን ቢይዙ፤ ቆመንለታል ለሚሉት ሕዝብ ምን እንደሚያደርጉ እንኳን ሊነግሩን የማይችሉት። እነሱ መጽደቅ የሚፈልጉት ሌላውን በመኮነን እንጂ የራሳቸውን የጽድቅ ሥራ በመስራት አይደለም። ለመሆኑ፤ እነዚህ ኃይሎች፤ አዲስ አበባ ተቀምጠው፤ የመግለጫ ጋጋታ ከማዝነብ ውጭ ለሕዝቡ ምን ሰሩ? መልሱ ምንም ነው። “የድርጅት አመራር” የሚል ታርጋ ስለለጠፉ ብቻ፤ ከመኮፈስ በቀር ምን ሰሩ? ሌላውን መውቀስ እና ማብጠልጠል ቀላል ነው። ሥራ ግን ማሰብን እንዲሁም ሸሚዝ ጠቅለል አድርጎ “ጭቃ ማቡካትን” ይጠይቃል። እነሱ የመስራት አቅም ስለሌላቸውም ነው፤ የዓብይ አስተዳደር የሚሰራቸውን መስረት ልማቶች የሚያጣጥሉት። የእንጦጦ ፓርክ ቅንጦት ነው ይሉናል፤ ከፓርኩ ባሻገር ግን፤ በርካታ የሥራ እድሎች አሉ፤ ኢኮኖሚውን የሚጠግን፤ የውጭ ምንዛሪ አለ፤ ስደትን ይቀንሳል፤ ወዘተ። ይህ ቅንጦት አይደለም።  

ሌላው በተደጋጋሚ የሚያነሱት፤በተለይ የሃገራችንን የተለያዩ ተቋማት፤ ዘመናዊ እና ለተልእኳቸው የሚመጥን ኅንፃ መገንባት እና ያንን ማስመረቅ እንደ ጥፋት መቁጠር ነው። እንዲሁ በግርድፉ ሲታይ፤ የሚያቀርቡት ምክንያት አሳማኝ ሊመስል ይችላል። ምክንያታቸውም “ሕዝብ እየሞተ፤ እየተፈናቀለ እና እየተሰደደ ኅንፃ ማስመረቅ ቅንጦት ነው የሚል ነው። እነዚህ ኃይሎች ያልተረዱት ነገር የሽብርተኞች ዓላማ፤ ንፁሃን ዜጎቻችንን በመግደል በውስጣችን ፍርሃት ለመፍጠር እና፤ በፍርሃት ተሽብበን የቀን ተቀን ሕይወታችንን እንዳንኖር ለማድረግ ነው። መንግሥትም ቢሆን መደበኛ የልማትም ሆነ የማህበራዊ ሥራዎቹን እንዳይሰራ ለማድረግ ያለመ ነው። መንግሥት ስራውን ካቆመ፤ አሸባሪዎች አሸነፉ ማለት ነው። ከዛም አልፎ እንኳን እንደ ኢትዮጵያ ባለ ታላቅ ሃገር ይቅርና፤ በአንድ ድርጅት ውስጥ እንኳን፤ የተለያዩ ክፍሎች (Departments) የሚሰሯቸው የየራሳቸው የስራ ክፍፍል አሉዋቸው። ፀጥታውን ለማስከበር የዘመተው ሠራዊት አይደለም ኅንፃ የሚገነባው፤ ወይም ከሰራዊቱ፤ የሰው ሃይል ተቀንሶ አይደለም ሌላው ሥራ የሚሰራው። ሽብርተኞች በሚያደርሱት ጥቃት የተነሳ ሃገር ባለችበት አትቆምም። ሥራው ይቀጥላል። ሽብርተኞች፤ የሚፈልጉት፤ የሃገሪቱን ሥራ ማሰናከል ነው። ኬነዲ እንዳሉት፤ አሸባሪዎች ሕሊናችንን በፍርሃት በመቆጣጠር፤ ባሕሪያችንን እንድንቀይር ነው የሚፈልጉት። የልማት ሥራዎችን ማቆም ማለት፤ አሸባሪዎች እንዲያሸንፉ ፈቀድን ማለት ነው። ከዚህም ሌላ፤ ከኅንፃዎቹ በስተጀርባ ለሃገር ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው ተቋማት ናቸው የሚገነቡት። ለምሣሌ የኢንሳ ኅንፃ ምርቃትን የሚተቹ ሃይሎች፤ ማየት የቻሉት ኅንፃውን ብቻ እንጂ ከኅንፃው በሰተጀርባ ያለውን ቁም ነገር አይደለም። ኅንፃው የተገነባው፤ የደህንነት ተቋሙን በሰው ሃይል፤ በቴክኖሎጂ እና በአስፈላጊው ቁሳቁስ በይበልጥ ለማደራጀት እና፤ ሃገራችንን ከውስጥም ሆነ ከውጭ የሚሰነዘርባትን ጥቃት ቀድሞ በማወቅ ለመመከት እንዲቻል ነው። ከኅንፃዎቹ በስተጀርባ፤ የሕዝባችንን ሰላም የማስጠበቅ አላማ አለ፤ ሥራ የመፍጠር አላማ አለ። የኅንፃ ግንባታው ዓላማ በሚሊዮን የሚቆጠረውን ሕዝብ የመታደግ ዓላማ ያነገበ ነው። ከዛም አልፎ ለአሸባሪዎች ግልጽ መልዕክት አለው። ሃገራችንን ማሰናክል አትችሉም፤ በአረመኔ ተግባራችሁም አታረበተብቱንም የሚል።

ከታሪካችን የምንማረው፤ ኢትዮጵያን እንሞትልሻለን ብለው ሲመፃደቁ የኖሩ፤ ግን ገዝግዘው የገደሏት ጥቂቶች እንዳልሆኑ ነው። የሃገር ፍቅር የሚለካው በሥራ እንጂ፤ መፈክር በማንገብ እና መፈክር በማጮኽ አይደለም። ለተራበው እና ለተፈናቀለው ሕዝባችን እርዳታ ለማሰባሰብ የሚተጉ ብርቅዬ ዜጎችን በማዋረድ፤ እጅና እግራቸውን አጣጥፈው እንዲቀመጡ ያደረጉ “ያልነቁ አንቂዎች” ለሕዝብ ተቆርቋሪ መስለው በመግለጫ ሲያደነቁሩን መስማት እጅግ ያማል። የሃገር ፍቅር መገለጫው የሚሰሩ ሰዎችን ላይ እንቅፋት መፍጠር አይደለም። ዛሬ፤ “አንቂ ነኝ፤ ከእኔ በላይ ኢትዮጵያዊነት ላሳር” ብሎ የሚመፃደቅ፤ “ያልነቃ አንቂ” ጀግንነቱ በማህበራዊ ሚድያ እንጂ በሥራ ሲገለጽ አናይም። የትኛው በሃገር ውስጥ ያለ አንቂ ነው ‘ተፈናቀለ፤ ተገደለ፤ ተሰደደ’ እያለ ሙሾ ለሚያወርድለት ሕዝብ፤ መሰሎቹን አሰባስቦ፤ ለተራበው እና ለተፈናቀለው ሕዝብ እርዳታ ሲያሰባሰብ እና የዚህን ሕዝብ እምባ ለማበስ ሲጥር ያየነው? ዛሬ ግን “ጀግንነቱን ለመግለጽ” “የአማራ ወጣት ታጠቅ” ሲል ይደሰኩራል። ይህ ታጠቅ የሚል “ያልነቃ አንቂ”፤ እራሱ መሣሪያ ለመታጠቅ እና ለመፋለም በቦታው እንደማይገኝ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ከተመቻቸ ወንበር ላይ ተቀምጦ፤ ከወላፈኑ ርቆ፤ በቅንነት ለሃገር በትጋት የሚሰሩ፤ እና ብዙ መስዋዕትነት የከፈሉ እና እየከፈሉ ያሉ፤ ቅን የሕዝብ አገልጋዮችን ማብጠልጠል እጅግ ቀላል ነው። ሜዳውም ክፍት ነው፤ ፈረሱም ተዘጋጅቷል፤ እስኪ ማድረግ የሚችሉትን በሥራ ያሳዩን። ተመሳሳይ አስተሳሰብ ያለውን ፖለቲከኛ በአንድ የድርጅት ጥላ ሥር ማሰባሰብ ያልቻሉ ሰዎች፤ እንዴት ነው በጣም ውስብስብ ችግር ያለባትን ሃገር እና፤ የተለያየ አመለካከት እና አስተሳሰብ ያለውን ሕዝብ ሊመሩ የሚችሉት? ሃገር ማስተዳደር መሸታ ቤት እቁብ እንደመጣል ቀላል አይደለም። መንግሥት እንደ መንግሥት የሚወስዳቸው እርምጃዎች ጥንቃቄ እና ሃላፊነት የተሞላበት ሊሆን ይገባል እንጂ፤ እንደ ሽፍታ በማሰብ፤ እንደ ሽፍታ፤ ሊተገብር አይችልም። መንግሥት ለሕዝቡ ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርግ፤ ሃላፊነታቸውን ያልተወጡ ባለሥልጣናትን ከሥልጣን እንዲያነሳ፤ በሰው እና በቴክኖሎጂ የታገዘ መረጃ የማሰባሰብ ብቃቱን እንዲያጠናክር መጎትጎት ያስፈልጋል። ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ ስንቆም እና በቅንነት ለሃገራችን ስንተጋ፤ አሸባሪዎችን ማሸነፍ እና ሕዝባችንን መታደግ እንችላለን። ነገር ግን፤ ይህ “ወርቅ ሲነጠፍለት ፋንድያ ነው” የሚል “ያልነቃ አንቂ” ለስራ የሰነፈ፤ ዋጋ ለመክፈል ያልተዘጋጀ፤ የሚሰሩትን የማያሰራ፤ ንዝህላልና የሃገር ጠንቅ የሆነን ሃይል፤ የሕዝቡን ተገቢ ጥያቄ ሲጠልፍ እና በአረመኔዎች በተጨፈጨፈው ሕዝባችን ደም ሲነግድ፤ በዝምታ ካለፍን፤ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ፤ የዚህ ጽንፈኛ ኃይል ተባባሪ ከሆንን፤ እኛም የመፍትሔው አካል ከመሆን ይልቅ የችግሩ አካል እንሆናለን። ለዚህም ነው፤ ይህንን ጽንፈኛ ኃይል በአንድ ድምጽ፤ በሕዝባችን ደም መነገድ ያቁም ልንል የሚገባው።

ቸሩ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ይባርክ።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,864FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

2 COMMENTS

  1. አሜሪካውያን ያልገቡበት የማያውቁት ጦርነት የለም፥፥በነሱ ልክ እሳት አቃጥሎ ገድሎ የዞ ንባ የሚያረግፍ የለም፥፥ሰው መቀያየር የማስመሰል ድርጊት ነው፥የክህደታቸው ዋቢ ው፥፥አቢይ ሰላያቸው ኢሳያስ ኤርትራውያንን እየገረፉ ከሀገር ያስወጡበት የጉማሬ አለንጋቸው ነው፥፥ከየትኛውም ሰብዊ ቀውስ በስተጀርባ ስለመኖራቸው የሚጠራጠር ፍጡር ቢኖር ለአቅመ አዳም ወሔዋን ያልደረሰ ዜና ሰምቶ የማያውቅ ነው፥፥ዜናው በራሱ አንዱ ካንዱ ይጋጫል፥፥አሁን ደግሞ ምስኪን ሕዝብን ከሶርያ የበለጠ እንጎዳሃለን እናፈራርስሀል እያሉ በአሽሙር ይዝቱበታል፥፥መቼ ይሆን አለም ከነርሱ የምርው፥፥እኛ የነርሱን ኪስ የሚያደልብ በየመኪውና በየመንገዱ የሚያድረው የእግዜር ውሃ የተወደደበት ሕዝባቸውን የሚያስተነፍስ የሚያረካ ሀብት የለንም፥፥ለኢጎአቹ ለከት ይኑረው ትንሽም እንኳ ባታምኑበትም የምትሰብኩትን መፅሐፍ ቅዱስ ጣጥሙት ርህራሄ ቢያድላቹ ፥ሕዝባችንን ጦር ታውጁበት ረበን ጠማን ጨፈጨፍን እርዱን ነው ያላቹህ

  2. በኢንሳ የሚሰሩ የማሕበረ ቅዱሳን አባላት ከዳንኤል ክብረት ጋር በመተባበር በቅዱስ አባታችን ላይ አፀያፊ ስድቦችንና ለሕይወታቸው አሥጊ የሆኑ ዱለታዎችን እያቀነባበሩ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ፥፥ማሕበረ ቅዱሳን ወጣቶችን ከተለያዩ ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች በመሰብሰብ የመፅሐፍ ቅዱስ መርሐግብር በሚል ሽፋን ለድብቅ አላማው ሲጠቀምባቸው ቆይቷል ይገኛልም፥፥እነዚህ ተማሪዎች በተመረቁ ማግሥት ግብር ለመሰብሰብና በተመደቡበት የሥራ መስክ በሙያቸው ለማህበሩ በሙያቸው በነፃ እንዲያገለግሉ በማቀድ ገና ከለጋነታቸው ጀምሮ የአዕምሮ እጥበት(ሕፅበተ አዕምሮ=ብሬን ዋሽ=)ይፈፅምባቸዋል፥፥ማህበሩ በቤተክርስቲያን ስም የሚንቀሳቀስ የፖለቲካ ድርጅት ነው ስንል በምክንያት ነበር፥፥ይህ ማህበር የሕዝብና የቤተክርስቲያን(ኦርቶዶክስን የገዛ ገንዘቧን ዘርፎ ና ልጆቿን በሀሰት በወንጌል ስም አታሎ በሥራ ና በቀን አበል አገልጋዮቿን ደልሎና አታሎ እውነተኛ ለመምሰል የሚሰራ የፖለቲካ ና የሥለላ ድርጅት ስለ ሆነ ፈርሶ ሌላ መተካት ለበት፥፥እንደብልፅግና እኛ ከተበተንን በሚል ፈሊጥ ችግር እንዳይፈጥሩ መጠንቀቅ ያሻል እኔ ከሞት ሠርዶ አይብቀል ባዮች ናቸው ና ጠንቀቅ እንበል፥፥ልብ እንበል እንደ ዳንኤል ክብረት በተለያዩ ቦታ ሁነው አገር የሚያምሱ በትግይ ላይ ጦርን የደገፉ በኢንሳየሚሰሩ የማህበሩ አባላት አሉ፥፥ጠንቀቅ የቤተክርስቲያንና የሀገር ጠላት ማሕበረ ቅዱሳን ተብየው ማሕበረ ቅርሱሳን ወርኩሳን ይፍረስ በሌላም ይተካ፥የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን እያጥላላ ወደ ሌሎች የእምነት ቤቶች እንዲሄዱ ሲያደርግና ገንዘቧን የሰረቀ ቤተክርስቲያን በቅኝ ግዛት ሲገዛ የቆየ ነው፥፥

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here