(ደብሩ ነጋሽ ~ሃኪም)
ነሃሴ 8 2013 ዓ ም
የእናት አገራቸው መቀመቅ መውረድ የሚያንገበግባቸውን ወገኖች እንዳሉ ሁሉ፣ ‘’አንተ ምን አገባህ? አርፈሽ ልጆችሽን አታሳድጊም? አንቺ ብቻ ነሽ በኢትዮጵያ የተፈጠርሽ? ይልቁንስ ወላጆችህን ከምታሳቅቅ አርፈህ አትጦርም?’’ የሚሉ ብዙ ናቸው። እዚህ ላይ ታላቁን አርበኛ፣ ራስ አበበ አረጋይን ማንሳት አግባብ ነው። እኝህ ታላቅ አርበኛና እጅግ አስተዋይ ሰው፣ አንድ እውነታ ተገንዝበዋል። ይሄውም የጠላትነትን ምንነት ያወቀ ሁሉ መጀገኑን ነበር። ስለሆነም፣ የጣልያንን እና ባንዶቹን ማንነት በቅጡ በማስተማር፣ ያቅማማ የነበረ የሸዋ አማራ ወጣት፣ በሺ የሚቆጠር ባገር ፍቅር እየነደደ ፣ የገዛ ቤቱን እያቃጠለ ዱርቤቴ ብሎ፣ ጠላትን አፍረክርኮ ለድል የበቃ ፋኖ መሆኑ ነው። አዎ ለወገኑ የሚነድ የሚቃጠል፣ የሚሰዋ ሁሉ፣ ወዶ ሳይሆን፣ ላገር ለወገን ፣ ለክብሩ፣ ከመነጨ ፍቅር ነው። ለህሊና ከማደርና ብቁ ከመሆን (enlightened በግሊዝኛ) የሚመጣ ነው። ‘’አንበሳ ቢወልድ ልጁን፣ አሳማም ቢወልድ ልጁን’ ነውና፣ የከሃዲ ባንዳ ትግሬ ዝርያ፣ ክህደት ወጉ ነው። ለአርበኛ አማራም፣ መገለጫው የመንፈስ ለዕልና፣ ያገር ፍቅር ናቸው።
ካርባ አመታት በፊት፣ በአሜሪካው ግሬይሃውንድ/ ግራጫ ውሻ/ ፣ በተባለ አገር አቋራጭ አውቶቡስ ተሳፍሬ ስጓዝ ፣ ጎኔ ከተቀመጡ አዛውንት አሜሪካዊ፣ ጭውውት ጀመረን ። ከምስራቅ አሜሪካ ወደ ምዕራቡ ፣ ካሊፎርኒያ ለቀናት ስንጓዝ ፣ የመጀመርያው በግንባር ያገኙት ኢትዮጵያዊ መሆኔን ነግረውኝ፣ አገሬ በአድዋና በፋሽስት ዳግም የኢጣልያን ወረራ ድል በመምታቷ፣ የሚያደነቋት መሆኑን ሲንግሩኝ ፈነደቅሁ። አሜሪካኖችን ከመሰሉ ደናቁርት ዜጎች፣ አዋቂ ስላጋጠመኝ። በወጣትነት ዘመናቸውም፣ በእስፔናውያን የርስበርስ ጦርነት፣ ፍራንኮ የተባለውን ያገሪቱ ፋሽስት አምባ ገነን መሪ ለመዋጋት፣ አህጉር አቋርጠው አውሮጳ መሄዳቸውንም ገለጹልኝ።። በርዕዮተ~አለም እንጂ
በምንም ከማይተዋወቁዋቸው እስፔናውያን ጎን ተፋልመው ቢሸነፍና በሁለት ጥይት ቢቆስሉም፣ በኩራት ነበር ያወሱኝ።
’ ‘’ወርች ( የፊት እግር) የመታውን፣ እግር አይስተው ‘’
ይህን የማነሳው፣ ላለፉት 30 አመታት፣ ያልጠረጠረው፣ ያልተደራጀው አማራ፣ በወያኔና ኦነግ መንግስት የሚደርስበት ግፍ፣ እንደ ታዲዎስ ታንቱን ፣ ገበረመድህን አርአያ፣ ጌታቸው ረዳን (የአሜሪካው) ከመሰሉ ጥቂት ወገኖች በቀር፣ ተቆርቋሪነቱን የገለጸ ባላመስማታችን ነው። አዎ፣ አብዲ ኢሌ ከወያኔ ጋር በኦጋዴን፣ ያስፈጸመው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ባይዘነጋም፣ የዛሬ 30 አመት፣ ጀግናው ኢሳ ( የድሬዳዋ አካባቢ ሶማሌ ጎሳ) ነበር፣ የአማራን ፍጅት ያስቆመው። በድፍን ሃረርጌ፣ ከ200 ሺህ በላይ ያልታጠቀ፣ ያልጠረጠረ አማራን ኦነግ ፈጅቷል። ድሬደዋም 69 እንደገደለ፣ ያማራን ጀግንነት የሚይውቀው ጀግናው ኢሳ ነበር በቃ ያላቸው። የአፋር ህዝብም፣ ለወገኑ ለአማራ ህዝብ መቆሙን ደጋግሞ የገለጸ ታላቅ ያገር ቤዛ አርበኛ ነው። የአማራው ሰቆቃ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹን ያላስጨነቀው፣ ምናልባት፣ ‘’ወርች የመታውን፣ እግር አይስተው ‘’ እንዲሉ፣ የወያኔና ኦነግ ህገ~መንግስት በሚሉት መተዳደርያ ሰነዳቸው፣ አማራ በጠላትነት የፈተፈርጀ ስለሆነም ነው።
‘’መሪ የሌለው ህዝብ፣ አውራ የሌለው ንብ’’
እርግጥ ነው 45 ሚሊዎን በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ መስራች ስልጡን እና በጀግንነቱ ወደር የሌለው ህዝብ ፣ በመናኞች ለውርደት፣ ለጥፋት መዳረጉ፣ ጉድ የሚያሰኝ ነው። ባጭሩ ‘’መሪ የሌለው ህዝብ፣ አውራ የሌለው ንብ’’ ሆኖ ስለተገኘ ነው። በአጽመርስቱ በሃጣዬ በቁሙ የጋየውና 300 000 ዱር የተደደው። ‘’ዱቄት’’ የሆነውም ወያኔም ፣ ዳግም ወሎን፣ በጌምድርና አፋርን ወሮ፣ ሺዎችን ገድሎ፣ ከ 350 000 የሚበልጡ አማራና ኣፋሮችን ለስደት የዳረገው፣ አማራ አውራ ስላልነበረው ነው።
ትግሬ ወያኔ፣ የኢትዮጵያ ሰራዊት በተኛበት ጨፍጭፎ፣ ማይካድራ ከሁለት ሺህ በላይ አማራ ፣ በስለት ቀረጣጥፎ፣ ፣ በፋኖና የአማራ ልዩ ኃይል እንዲሁም በሰራዊቱ ጥምር ዘመቻ ተንበርክኮ ነበር። ሆኖም የኢትዮጵያ ሰራዊት ፣ ከባድ መሳርያ ሳይቀር ትቶላቸው እንዲወጣ ስለታዘዘ፣ ወያኔ ነፍስ ዘርቶ፣ አማራን መውረሩ ይታወቃል። ታድያ የማይካድራውም ፍጅት ሆነ፣ የእለት ዕለት ያማራ፣ በወለጋና ጉሙዝ መታረድ፣ ከ 60 ሺህ በላይ የማራ ተማሪዎች ኦሮምያ ከሚባለው ክልል ዩኒቨርሲትዎች መባረር፣ የታገቱት አማራ ሴት ተማሪዎች ጉዳይ፣ ወዘተ ተድበስብሶ፣ ውያኔም ከፍርድ ለማምለጥ መፍጨርጨር፣ አማራው ድርጅት አልባ ስለሆነ ነው።
ቢዘገይም ግፍ የወለደው፣ በአማርነት የተፈተኑ ወጣቶች ፣ የተፈተነውን የአበው ህዝባዊ ኃይል፣ በፋኖ አማካይነት መቋቋም፣ ይበል የሚያሰኝ ነው። ሁነኛ የአማራ ድርጅት ቢኖር ኖሮ፣ አማራው ባቆማት፣ ባጸናት አገር፣ በባንዳና በወራሪዎች ፣ እንደጎመን በቁሙ ባልተቀረደደ፣ ምዕመናኑና ቤተ~እመነቶቹ ፣ ቤተ~ክርስቲያናቱና፣ መስጊዶቹ ባልጋዩ ፣ በሚሊዎኖች ባልተሰደዱ፣ ሃብት ንብረታቸው ባልወደመ ።
ኢትዮጵያን ዝንተአለም ከጠላት ይታደግ የነበረው ፋኖ እንደነበር ታሪክ ምስክሩ ነው። የፋሽስት ጣልያኖች ሰነድ እንደሚያመለክተው፣ በ 1930 ዐመተ ምህረት፣ ከ 25 000 አርበኞች 23 500 የአማራ ፋኖ ነበር። ይህም ከ 20 ው 19 ኝ ያህል ነበር። በ 1933 ዐመተ ምህረት ደግሞ፣ የበላይ ዘለቀ አርበኞች ቁጥር ብቻ፣ 44 000 ይበልጥ እንደነበር ተጠቅሷል። ስለዚህ ፣ በአማርነት በተፈተኑ ወጣት ፋኖዎች፣ በነዘመና ማስረሻ አማካይነት፣ በተፈተነው የአበው የፋኖ አደረጃጀት፣ ወጥ ህዝባዊ የአማራ ኃይል መመስረት፣ ያማራና የኢትዮጵያን ህልወናውና መታደጉ እሙን ነው። እሰይ የሚያሰኝ ነው። ስለዚህ እንኳን ጦር የተሰበቀበት አማራ ቀርቶ፣ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ፣ ሊደግፈው ይገባል። ያገር አድባርና አውጋር የሆነው አማራ፣ ለድፍን ኢትዮጵያ፣ የጎራ ባላ እንደመሆኑ መጠን፣ ፋኖውም ደጀኑ ነው። የፍትህ አማላክም ፣ ከፋኖ ጋር ነው። ሰልፍ የጀግና፣ ድል የዕግዚአብሄር ነውና ።
__
በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com